በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን
ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን
ሚኒያፕለስ, ሜኒሶታ, ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ
የሰባኬ ወንጌል አገልጋይ ለመቅጠር የወጣ ማስታወቂያ
የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በሰሜን አሜሪካ ሜኒሶታ ግዛት ሚኒያፕለስ ከተማ የሚገኝ በግዛቱ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ሲሆን በሺዎች ለሚቆጠሩ በስደት ላሉ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ምእመናንን በርካታ መንፈሳዊ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ ታላቅ ቤተክርስቲያን ነው። ከዚህ አንፃር የቤተክርስቲያናችን አገልግሎት እና የምእመናንን ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ እየሰፋና እያደገ በመምጣቱ አንድ ተጨማሪ የስብከተ ወንጌል አገልጋይ መምህር መቅጠር አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።
የቅጥር መስፈርቶች
- ክህነት ያለው (የቅስና ወይንም የዲቁና ማዕረግ ያለው)
- ከታወቀ የአንድምታ ትርጏሜ ጉባኤ ቤት የተመረቀ እና የስብከተ ወንጌል ችሎታ ያለው
- ከአብነት ትምህርት ቤት የተመረቀ ወይንም የሥስነ መለኮት ኮሌጅ ምሩቅ የሆነ
- በስብከተ ወንጌል አገልግሎት ቢያንስ የአምስት ዓመት ልምድ ያለው
- ዘመናዊ ትምህርት ቢያንስ 12ኛ ክፍልን ያጠናቀቀ
- ልጆች በማስተማር በቂ ልምድ ያለው
- በእግሊዝኛ ቋንቋ መግባባት የሚችል እና ቢቻል በዚህ ቋንቋ ማስተማር የሚችል
- መልካም ጠባይና ሥነ ምግባር ያለው
የቅጥር ማስታወቂያውን ለማንበብ ይህን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ
ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አገልጋዮች እዚህ ማስፈንጠሪያ ላይ የሚገኘውን የማመልከቻ ቅፅ በመሙላት በኢሜል ወይንም በፖስታ ወይንም በሚያውቁት ሰው በኩል ማመልከቻውን እና ማስረጃዎቻቸውን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከዛሬ ከግንቦት 11, 2016 (May 19, 2024) ጀምሮ በ60 ቀን ውስጥ መላክ ይችላሉ::
የስራ ማመልከቻውን ቅፅ ለማግኘት ይህንን ይጫኑ
ማሳሰቢያ:–
- አመልካቾች ያሉዋቸውን የትምህርት: የስራ ልምድ እና 2 የፓስፖርት መጠን ያለው ፎቶግራፍ ከማመልከቻችው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- አመልካቾች የማስተማር ልምዳቸውን የሚያሳይ የተንቀሳቃሽ ምስል ማስረጃ (ቪዲዮ ናሙና) ከማመልከቻችው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
ማመልከቻዎን በኢሜል ለመላክ:-
dsmachurch@gmail.com
subject line: Hiring Team
ማመልከቻዎን በፖስታ ለመላክ:-
To: Hiring Team
Debre Selam Medhanealem Ethiopian Orthodox Tewahdo Church
4401 Minnehaha Avenue South
Minneapolis, MN 55406
U.S.A
ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን,
ሚኒያፕለስ, ሜኒሶታ, ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ
ግንቦት 11, 2016 (May 19, 2024)
አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406, U.S.A.
ስልክ: +1(612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/