Category Archives: News

እንዳያመልጣችሁ! የበገና ምሽት ቅዳሜ ኤፕሪል 13, 2024 በሚኒስታ ደብረስላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አዳራሽ

ታላቅ የበገና ምሽት

በሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት ታዳጊ እና ወጣቶችተዘጋጅቶ ይቀርባል::

መቼ : ሚያዝያ 5, 2016 ዓ.ም. (April 13, 2024) ከቀኑ 4:00 ፒ.ኤም. ጀምሮ

እንዳያመልጣችሁ!
አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/

በአብይ ጾም ውስጥ ያሉ ሳምንታት ስያሜ

የተከበራችሁ የቤተክርስትያናችን አባላት እና ቤተሰቦች በሙሉ፤
እንኳን ለ2016 ዐብይ ጾም አደረሰን!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለጾም ሥርዓት እና ደንብ አውጥታ በዓመት ውስጥ ሰባት የአዋጅ አጽዋማት እንዳሉና ማንኛውም ክርስቲያን እነኝህን አጽዋማት እንዲጾሙ ታዛለች። ከነዚህም አንዱ እና ታላቁ ጾም ዛሬ ሰኞ መጋቢት 2/2016 (March 11, 2024) የጀመርነው የአብይ ጾም ነው:: ለዚህም ቤተክርስቲያናችን እንኳን አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቷን ትገልጻለች።

ዐቢይ ጾም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለእኛ የጾመው ጾም እና ለእኛ አራያ የሆነበት ጾም ነው። እኛም እንድንጾማቸው በቤተ ክርስቲያናችን ከታዘዝናቸው ሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት አንዱ ነው። እኛ ምእመናን ጌታችን ያደረገውን ምሳሌ ተከትለን ጾሙን በየዓመቱ እንጾመዋለን። ዐቢይ ጾም ስምንት ሳምንታት (፶፭ ቀኖች) ሲኖሩት በውስጡ ስምንት ቅዳሜዎች፣ ሰባት እሑዶች ይገኛሉ።እነዚህም ዐሥራ አምስት ቀናት ሲሆኑ በእነዚህ ቀናት ከጥሉላት እንጂ ከእህል ውኃ ስለማይጦሙ እነዚህ ቀናት ሲቀነሱ የጦሙ ወራት ዐርባ ቀን ብቻ ይሆናል።

ዓብይ ጾም የተባለበት ምክንያት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው ስለሆነና ታላላቅ የሰይጣን ፈተናዎችን ድል የተነሱበት በመሆኑ ዛሬም ክርስቲያኖች የአምላካችንን አርአያ ተከትለን ሰይጣንን ድል የምንነሳበት ጾም ስለሆነ ነው።

የዐብይ ጾም በተለያዩ ስሞችም ይጠራል

  • ሁዳዴ ጾም ይባላል። ይህም የመንግሥት እርሻ ወይም ማንኛውም የሕዝብ ብዛት ያለበት ሥፍራ ሁዳድ ይባላል። በመሆኑም ዐቢይ ጾምም ከአጽዋማት ሁሉ ብዙ ቀናት ስለሚጾምና ክርስቲያኖች የሆኑ ምዕመናን ሁሉ ስለሚጾሙት የሁዳዴ ጾም ተባለ።
  • ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው ፵ ቀን ስለሆነ ጾመ ዐርባ ም ይባላል /ማቴ.፬፥፩/

በአብይ ጾም ውስጥ ያሉ ሳምንታት ስያሜ

  • ዘወረደ
  • ቅድስት
  • ምኵራብ
  • መጻጕዕ
  • ደብረዘይት
  • ገብርኄር
  • ኒቆዲሞስ
  • ሆሳዕና
  • ትንሳኤ ናቸው ::

የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በአብይ ጾም ያላት የአገልግሎት መርኃ ግብር

  • ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋቱ 6 ኤ.ኤም እስከ 10 ኤ.ኤም የኪዳን ፀሎት አገልግሎት ይሰጣል።
  • ዘወትር ቅዳሜ ከጠዋቱ 6 ኤ.ኤም እስከ 8 ኤ.ኤም የኪዳን ፀሎት ይደርሳል።
  • ዘወትር እሁድ ከንጋቱ 3 ኤ.ኤም ጀምሮ የፀሎት፣ የክርስትና፣ የቅዳሴ አገልግሎቶች ይሰጣል::

ከዘመድ እና ከወዳጅ ጋር በመምጣት የበረከቱ ተካፊይ እንዲሆኑ የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የአገልግሎት ቀን መቁጠሪያ ::

  • የዓብይ ጾም (የሁዳዴ ጾም) :- ከመጋቢት 2 አስከ ሚያዝያ 27 (Monday March 11, 2024 – Sunday May 5, 2024)
  • መጋቢት መድሐኔዓለም :- በዓለ ንግሱ መርኃ ግብር የሚከናወንበት ትክክለኛ ቀን : መጋቢት 29, 2016 (Sunday Apr. 7, 2024) / Megabit Medhanealem / The original Crucifixion.
  • ደብረ ዘይት :- መጋቢት 29, 2016 (Sunday April 7, 2024) / Debrezeit
  • ሀሳዕና :- ሚያዝያ 20, 2016 (Sunday April 28, 2024) / Hosanna
  • ሰሙነ ሕማማት :- ሚያዝያ 21, 2016 እስከ ሚያዝያ 26, 2016 (Monday April 29, 2024 to Friday May 3, 2024) / Holy/Passion week.
  • ጸሎተ ሐሙስ :- ሚያዝያ 25, 2016 (Thursday May 2, 2024) / Maundy Thursday
  • ስቅለት :- ሚያዝያ 26, 2016 (Friday May 3, 2024) / Good Friday (Crucifixion)
  • ትንሣኤ :- ሚያዝያ 27, 2016 (Sunday May 5, 2024) / Easter Sunday

በዚህ አብይ ጾም ሁላችም ስለሀገራችን እና ስለ ቅድስት ቤተክርስትያናችን አብዝተን የምንጸልይበት እኛም በረከት የምናገኝበት በስጋ ወደሙ የምንከብርበት ያድርግልን::

ጽሁፉን ያዘጋጀችው ወይዘሮ ሐና ስዩም ነች::

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/

የየካቲት ኪዳነምሕረትን የዋዜማ አገልግሎት እና በዓለ ንግስ በሚኒሶታ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ያክብሩ!

በሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን እንኳን ለየካቲት ኪዳነምሕረት በዓለ ንግስ በስላም አደረሳችሁ እያለች፣ የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 16, 2016 ከቀኑ 4:00ፒ.ኤም. ጀምሮ (Saturday Feb. 24, 2024 from 4:00 pm) በዋዜማ፣ ቀጥሎም እሁድ የካቲት 17, 2016 ከ2:00 ኤ.ኤም. ጀምሮ (Sunday Feb. 25, 2024 from 2:00 am) በማህሌት የየካቲት ኪዳነምሕረትን በዓለ ንግስ በደመቀ ሁኔታ ታከብራለች:: በእለቱም ከቤተሰብ፣ ከዘመድ እና ከወዳጅ ጋር በመምጣት የበረከቱ ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ ቤተክርስቲያናችን ጥሪዋን ታቀርባለች::

መቼ? / When?
የዋዜማ አገልግሎት፣
ቅዳሜ የካቲት 16, 2016 ከ4:00 ፒ.ኤም. ጀምሮ (Saturday Feb. 24, 2024 from 4:00 pm)
በዓለ ንግስ
እሁድ የካቲት 17, 2016 ከ2:00 ኤ.ኤም. ጀምሮ (Sunday Feb. 25, 2024 from 2:00 am)

ፎቶግራፉ የሚያሳየዉ በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የቤዛ ኩሉ የሰንበት ት/ቤት ታዳጊና ወጣቶች በዚህ አመት የጥምቀት በአል አከባበር መርኃግብር ላይ ነዉ::

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net

በፌስቡክ እንዲከተሉን ይህን ይጫኑ

Click Here to Follow Us On Facebook

የስባተኛው አመት የበጎፈቃደኝነት የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ በሰላም ተጠናቀቀ!

የተከበራችሁ የቤተክርስትያናችን አባላት እና ቤተሰቦች በሙሉ፤

እንደወትሮው ሁሉ የሚኒሶታ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አባላት እና ቤተሰቦቻቸው አዲስ የቤተክርስቲያን ሕንፃ ለመገንባት የሚያስፈልገውን የገንዘብ ወጪ በከፊል ለመሸፈን ያስችል ዘንድ ከኪሳችን ከምናዋጣው በተጨማሪ በ2023 ዓ.ም. የበጎፈቃደኝነት የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ላይ በዩኤስ ባንክ ስታዲየም እና በሚኔሶታ ስቴት ፌር ተስማርተን ነበር :: እንደምታስታውሱት ሁሉ የመጨረሻው የበጎአድራጎት የስራ ቀን የተጠናቀቀው ያለፈዉ ወር እሁድ December 31, 2023 በዩኤስ ባንክ ስታዲየም ውስጥ በተደረገው የቫይኪንግ እና የግሪን ቤይ ፓከርስ ቡድኖች ጨዋታ ቀን ነበር:: ይህን የስራ ዘርፍ ከጀመርን እነሆ ሰባት አመታትን አአስቆጥረናል! ስለሆነም ባለፈው አመት ውስጥ ስለተከናወኑት የበጎአአድራጎት ስራዎች እና ስለተስበስበው የገንዘብ መጠን ለግንዛቤ ይረዳል ተብሎ በበጎአድራጎት ስራ አስተባባሪዎቹ በኩል የተዘጋጀ አጭር ሪፖርት ከዚህ በታች ባለው መልኩ ቀርቧል::

በ2023 ዓ.ም. ስንት የበጎፈቃድ አገልግሎት ሰራ ቀኖች ነበሩ?

በአመቱ በጠቅላላው 27 የበጎፈቃድ አገልግሎት ሰራ ቀኖች ነበሩ:: እነሱም 11 የቫይኪንግ ጨዋታዎች  ፣ 10 በሚኒሶታ ስቴት ፌር የመክና ማቆሚያ ማስተናገድ ስራ እና 6 በዩእስ ባንክ ስታዲየም በተደረጉ የሙዚቃ ኮንስርቶች እና ሞንስተር ጃም ትእይንቶች ነበሩ:: በ2023 በተደረጉት ስራዎች አንድ የበጎአድራጎት የስራ ቀን በአማካይ ከ 7 እስክ 9 ሰአቶች ይፈጅ ነበር::

በ2023 ዓ.ም. የበጎፈቃድ አገልግሎት ሰራ ላይ ስንት አባላት ቤተስቦችና ወዳጆች ነበሩ?

በዚህ አመት በጠቅላላው 111 የደብራችን አባላት ቤተስቦችና ወዳጆች በበጎአድራጎት ሰራ ላይ ተስማርተው ነበር:: ከ 7-14 ቀኖች የስሩ 10 እባላት  ፣ ከ4-5 ቀኖች የሰሩ ሌሎች 10 እባላት  ፣ ከ 2-3 ቀኖች የስሩ 36 አ ባላት  ፣ እንዲሁም አንድ ቀን ብቻ የስሩ 55 አባላት ነበሩ::

የስሩበት ቀኖች ብዛት የስሩ አባላት ብዛት%
7 – 14109%
4 – 5109%
2 – 3 3632%
15550%
ጠቅላላ 111100%

በ2023 ዓ.ም. የበጎፈቃድ አገልግሎት ሰራ ላይ እነማን ነበሩ?

በ2023ዓ.ም በተደረገው የበጎአድራጎት ስራ ወቅት ከ4 እስከ 14 ቀኖች ያገለገሉ 20 አባላት ስም ዝርዝር እና የስሩባቸው ቀኖች ብዛት በሚከተለው ሰንጠረዥ ላይ ተቀምጧል:: በዚህ አመት ብቻ 14 የበጎአድራጎት የስራ ቀኖችን በመስራት ከፍተኛውን ደረጃ የወሰደው የፕሮግራሙ አስተባባሪ ዶ/ር አሻርግሬ አትሬ ነው::

አባል ስም የስሩበት ቀኖች ብዛት
ዶ/ር አሻግሬ አትሬ14
ወ/ሮ በስልፍዋ መንገሻ11
ወ/ሮ አባይነሽ ደበላ10
ዶ/ር ብርሀኑ በለጠ10
አቶ ዳንኤል ከህሉ9
ዶ/ር መስፍን ተስፋዬ ገባያው9
አቶ አለምሰገድ ተስፋዬ8
አቶ እሸቱ ባዱንጋ8
አቶ ኤልያስ ጥላሁን7
አቶ ግርማ መኮንን7
አቶ አማረ በርሄ5
አቶ አሸናፊ ቡልቶ5
አቶ ፀጋ በዛብህ5
አቶ አበራ በርጃ4
አቶ ደረጀ አለሙ4
አቶ ደረስ ገ /ጊዬርጊስ4
ወ/ሮ እጅጋየሁ ይርጉ4
አቶ ገዛኸኝ ዳምጤ4
ወ/ሮ ራሄል ባልቻ4
ወ/ሮ ትእግስት መለሴ4

በ2021ዓ.ም. ፣ በ2022 ዓ.ም.  እንዲሁም በ2023 ዓ.ም. የበጎአድራጎት ስራ የስሩትን አባላት ስም ዝርዝር እና የስሩባቸውን ቀኖች ብዛት ለማየት የሚከተለዉን ሊንክ ይጫኑ! https://mesfinbcc.pythonanywhere.com/

በ2023 ዓ.ም. የበጎአድራጎት ስራ ምን ያህል ገንዘብ ተስበስበ?

በዚህ 2023 ዓ.ም. በበጎአድራጎት ስራ ለቤተክርስቲያን ማስሪያ የተስበስበው $56,166 ነበር :: በዚህ አመት በበጎአድራጎት ስራ ያስገባነው የገንዘብ መጠን ካለፉት ሁለት አመታት ስርተን ካገኘነው ጋር ሲነጻጸር እጅግ ያንሳል:: ክዚህ በታች ያለው ግራፍ እንደሚያሳየው በ2022 ዓ.ም. $199,950 እና በ2021 ዓ.ም. $223,558 አስባስበን ነበር::

በሰባት አመታት የበጎአድራጎት ስራ ለቤተክርስቲያን ማስሪያ የተስበስበው ጠቅላላ የገንዘብ መጠን ስንት ደረስ?

እስከአሁን ድረስ ለቤተክርስቲያን ማስሪያ በበጎአድራጎት ስራ የተስበስበው ጠቅላላ የገንዘብ መጠን $811,312 ነው:: ዝርዝሩ ከዚህ በታች ተቀምጧል::

እንደምታዉቁት ሁሉ ትልቁ ጉልበታችንና እቅማችን በሁሉም መስክ የተጠናከረ እና የተሳተፈ የአባላት ጥንካሬ ሲኖረን ነው:: ስለዚህም 2024ዓ.ም. ሁላችንም በምንችለው እውቀት ጊዜ ጉልበት እና ገንዘብ በመረባረብና በመደጋገፍ አዲሱን ቤተክርስትያን አስርተን ለመገኘት ያበቃን ዘንድ እንትጋ: : በዚህ አጋጣሚ ሁላችሁም እከአሁን እና ወደፊትም ለምታደርጉት ትብብርና እርዳታ ሁሉ በረከቱ ይብዛላችሁ::

በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን
January 30, 2024
Minneapolis, Minnesota, U.S.A.

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/

የዘንድሮው የከተራ እና ጥምቀት በዓል አከባበር እና የሃያ ሰባት አመቱ ቤዛኩሉ

በዚህ አመት የከተራ እና ጥምቀት በዓላት  ቅዳሜ ጥር 11, 2016 (Saturday Jan 20, 2016) እና እሁድ ጥር 12, 2016 (Sunday Jan 21, 2016) Bloomington Road, Fort Snelling, St. Paul, MN 55111 በሚገኘው ቦታ እንደወትሮው በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል:: የዘንድሮውን የጥምቀት በአል አከባበር ደማቅ እና ልዩ ያደረገው ነገር ቢኖር የሀገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ለመጀመሪያ ጊዜ በመሀከላችን ተገኝተው ቡራኬ መስጠታቸው እንዲሁም የቤዛ ኩሉ የሰንበት ት/ቤት ታዳጊና ወጣቶች በብዛት ሆኖ በመሳተፍና ያቀረቧቸው ልዩ ልዩ መዝሙራት እና ሌሎች መንፈሳዊ ዝግጅቶች በልዩ ሁኔታ የሚጠቀሱ ናቸው ::

በተለያዩ ምክንያቶች የበዓሉን አከባበር መርኃግብር በቦታው በመገኘት የበረከቱ ተሳታፊ ለመሆን ላልቻላችሁ ሁሉ ይጠቅማል በማለት የቤዛ ኩሉ ሰንበት ት/ቤት ታዳጊና ወጣቶች የሚዲያ ዝግጅት ክፍል ያካፈለንን ፎቶግራፎች ከዚህ በታች አቅርበናል::

የደብራችንን ታላቅነት ባገናዘበ መልኩ የቤዛ ኩሉ የሰንበት ት/ቤት ታዳጊና ወጣቶችም ላቀረቧቸው መዝሙራት ፣ ልዩ መንፈሳዊ እና ትምህርታዊ ዝግጅቶች በተጨማሪም ላሳያችሁት መልካም አርአያዊነት ተግባር እያመሰገንን የደከማችሁበት ሁሉ ስለተሳካላችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ እንላለን:: በዚህ አጋጣሚም  በደብራችን ውስጥ ለሚከናወኑት የሰንበ ት/ቤትና የልጆች ፕሮግራም ተሳታፊዎች: ካህናት: ፕሮግራም መሪዎች: አስተማሪዎች እና ወላጆች ሁሉ እንኳን ደስ ያላችሁ እንላለን። በተጨማሪም የቤዛ ኩሉ የሰንበት ት/ቤት ታዳጊና ወጣቶች የሚዲያ ዝግጅት ክፍልን ለፎቶግራፎቹ እጅግ በጣም እናመሰግናለን::

በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን
January 24, 2024
Minneapolis, Minnesota, U.S.A.

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/

እንኳን ለ2016 ዓ.ም. ከተራ እና ለብርሀነ ጥምቀቱ በስላም አደረሳችሁ!

እንኳን ለ2016 ዓ.ም. ከተራ እና ለብርሀነ ጥምቀቱ በስላም አደረሳችሁ እያለች የፊታችን ቅዳሜ ጥር 11, 2016 (Saturday Jan 20, 2016) ከቀኑ 3 ፒኤም ጀምሮ የከተራ ጉዞ ወደ 6202 Bloomington Road, Fort Snelling, St. Paul, MN 55111 ይደረጋል:: ቀጥሎም እሁድ ጥር 12, 2016 (Sunday Jan 21, 2016) ከቀኑ 1 ኤኤም ጀምሮ በማህሌት: ከቀኑ 5 ኤኤም በቅዳሴ እና ቀጥሎም በታቦት ሽኝት የብርሀነ ጥምቀት በአልን በደመቀ ሁኔታ ቤተክርስቲያናችን ታከብራለች::

በእለቶቹም ከቤተሰብ፣ ከዘመድ እና ከወዳጅ ጋር በመምጣት የበረከቱ ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

የጥምቀት በአል የሚከበርበት አድራሻ: 6202 Bloomington Road, Fort Snelling, St. Paul, MN 55111
ስለ ከተራ እና ጥምቀት አከባበር መርኃ ግብር የሚከተለዉን ይመልከቱ!

የጥምቀት ጾም (የጋድ ጾም) :- ጥር 10, 2016 (Friday Jan 19, 2024)
ከተራ :- ጥር 11, 2016 (Saturday Jan 20, 2016)
ጥምቀት :- ጥር 12, 2016 (Sunday Jan 21, 2016) / The Baptism of Christ (Epiphany).

በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የአስተዳደር ቦርድ
January 14, 2024
Minneapolis, Minnesota, U.S.A.

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/

እንኳን ለብርሀነ ልደቱ በስላም አደረሳችሁ!

በሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን እንኳን ለብርሀነ ልደቱ በስላም አደረሳችሁ እያለች የፊታችን ቅዳሜ ታህሳስ 27, 2016 (Saturday January 6, 2024) ከቀኑ 5 ፒኤም ጀምሮ በማህሌት: ቀጥሎም ከምሽቱ 11 ፒኤም ጀምሮ በቅዳሴ የእየሱሰ ክርስቶስን የልደት በአል በደመቀ ሁኔታ ታከብራለች:: በእለቱም ከቤተሰብ፣ ከዘመድ እና ከወዳጅ ጋር በመምጣት የበረከቱ ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ ቤተክርስቲያናችን ጥሪዋን ታቀርባለች::

መቼ: ቅዳሜ ታህሳስ 27, 2016 ከ 5 ፒኤም ጀምሮ
When: Saturday January 6, 2014 from 5pm

ከዚህ በታች ያሉት ፎቶግራፎች የሚያሳዩት የቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች የ2016 ዓ.ም. የእየሱሰ ክርስቶስ የልደት በአልን በደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያናችን ውስጥ ሲያከብሩ ነዉ::

የቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት በሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ውስጥ ከተመሰረተ 27 አመት አስቆጥሯል::

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/

ጾመ ነቢያት (የገና ጾም): ቅዳሜ ኅዳር 15 ለሚጀመረው እና በረከት ለምናገኝበት ጾመ ነቢያት እንኳን አደረሰን!

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

የተከበራችሁ የቤተክርስትያናችን አባላት እና ቤተሰቦች በሙሉ፤
እንኳን ለጾመ ነቢያት (የገና ጾም) በሠላም አደረሳችሁ።

የኢትዮያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰባት የአዋጅ አጽዋማት ያሏት ሲሆን ከእነዚህ የአዋጅ አጽዋማት መካከል አንዱ የነቢያት ጾም ነው። ጾሙን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ ከመገለጡና ሰው ከመሆኑ በፊት ነቢያት የጌታን መምጣት በናፍቆት በጾምና በጸሎት ሲጠባበቁ ነበር። ስለዚህ የነቢያትን የጾም ድካም ለማሰብና እንደ ነቢያት መንፈስ ኃይልን ለመልበስ በእምነት ለመጽናት ኃጢአትን ለመዋጋት ሲባል ይህን ጾም እኛ እንጾመዋለን።

ይህንን ጾም በተመለከተ በፍትሐ ነገሥት (ፍትሕ መንፈሳዊ) አንቀጽ ፲፭፥፭፻፷፬ ጀምሮ ተጽፏል። በፍትሕ መንፈሳዊ በአንቀጽ ፲፭፥፭፻፷፰ ላይ እንደተገለጸው ከኅዳር እኩሌታ እስከ ልደት የሚጾመው ጾም ነው።
“መጀመርያው የኅዳር እኩሌታ፡ ፋሲካው፡ የልደት በዓል ነው።” ተብሎ የጾመ ነቢያት መነሻውና መድረሻውን ፍትሐ ነገስት ላይ ተገልጿል። ይህም ማለት በሦስቱ ወንጌላውያን ማለትም በዘመነ ማቴዎስ፣ በዘመነ ማርቆስና በዘመነ ሉቃስ የገና ጾም ከኅዳር ፲፭ ጀምሮ  በኅዳር ፳፱ ይፈሰካል። በዚህ በያዝነዉ በዘመነ ዮሐንስ ደግሞ የገና ጾም ቅዳሜ ኅዳር ፲፭  ተጀምሮ እሁድ ኅዳር ፳፰
ይፈሰካል።

ጾሙን የበረከት ያድርግልን!

ጾመ ነቢያት (የገና ጾም) :-
ከህዳር 15,2016 አስከ ታህሳስ 28, 2016
(Saturday Nov 25, 2023 – Sunday Jan 7, 2024)

ጽሁፉን ያዘጋጀችው ወይዘሮ ሐና ስዩም ነች::

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/

ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ይደረጋል!

  • መንፈሳዊ ጉባኤ :- ጥቅምት 17, 2016 (Saturday Oct 28, 2023) ከ3:00 ፒ.ኤም. ጀምሮ. በጉባኤ አዳራሽ 1040 Osborne Road NE, Fridley MN 55432
  • መንፈሳዊ ጉባኤ :- ጥቅምት 18, 2016 (Sunday Oct 29, 2023) ከ4:00 ኤ.ኤም. ጀምሮ በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን
  • መንፈሳዊ ጉባኤ :-ጥቅምት 22, 2016 (Thursday Nov 2, 2023) ከ5:00 ፒ.ኤም.. ጀምሮ በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን
  • መንፈሳዊ ጉባኤ ;_ ጥቅምት 24, 2016 (Saturday Nov 4, 2023) ከ4:00 ፒ.ኤም. ጀምሮ በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን
  • ጥቅምት መድሐኔዓለም :- ጥቅምት 25, 2016 (Sunday Nov 5, 2023) ከ2:00 ኤ.ኤም. ጀምሮ በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን

ከዘመድ እና ከወዳጅ ጋር በመምጣት የበረከቱ ተካፊይ እንዲሆኑ የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የአስተዳደር ቦርድ
October 15, 2023
Minneapolis, Minnesota, U.S.A.

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ኢሜይል: membersservice@dsmachurch.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/

እንኳን ለ፳፻፲፮ ጽጌ ማሕሌት በሠላም አደረሳችሁ። /October 7, 2023 – November 16, 2023/

የተከበራችሁ የቤተክርስትያናችን አባላት እና ቤተሰቦች በሙሉ፤
እንኳን ለማሕሌተ ጽጌ በሠላም አደረሳችሁ።
ፅጌ ማለት አበባ ማለት ሲሆን ፀገየ ከሚለው የግዕዝ ቃል የመጣ ነው። ጽጌ ማሕሌት በየአመቱ ከመስከረም ፳፮ እስከ ህዳር ፮ (Oct 7, 2023 – Nov 16, 2023)
፵ ቀናት ወይም ፩ ወር ከ ፲ ቀን የሚቆይ ነው። ጽጌ ማሕሌት እመቤታችን ጌታችንን ይዛ መሰደዷን መራቧን መጠማቷን በማሰብ ነው

በማሕሌተ ጽጌ ወቅት ያሉት ሳምንታት ውብ ናቸው ምክንያቱም :-
☞እማምላክን ከነልጇ እንለምንበታለን ስደቷን እናስብበታለን፣
☞ የእመቤታችንን ፍቅሯን እናትነቷን አማላጅነቷን ከሊቃውንቱ ጋር ሆነን በዝማሬ እናወድስበታለን ፣

ጽጌ ማሕሌት የፈቃድ ፆም ስትሆን ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎች ብቻ ይፆሟታል። ምንም እንኳን ፆመ ፅጌ ከ ፯ ቱ የአዋጅ አፅዋማት መካከል ባትሆንም እና እንድንፆማት በአዋጅ ባንታዘዝም በፈቃዳችን በመፆማችን ከፆሟ ረድኤት በረከት የምናገኝባት ነች።

ሰንበትን ከጌታ ከኢየሱስ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋር ሌሊቱን በምስጋና በያሬዳዊ ዜማ ሳምንቱን ደግሞ በፈቃዳችን ማንም ሳያዘን የድንግል ማርያም ፍቅሯ አክብረን እንጾማለን።

እንኳን ለዚህ ጊዜ አደረሰን አደረሳችሁ !!!
የእመቤታችን ፍቅሯ ይብዛልን::

ጽሁፉን ያጠናቀረዉ አቶ ኤልያስ ወርቅህ ነዉ::

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ኢሜይል: membersservice@dsmachurch.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/

የቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ለአዲስ ቤተክርስቲያን ማሰሪያ የሚውል $15,490 አሰባስቡ!

ቀደም ብሎ እንደተገለፀው በቅርቡ ተከብረው ያለፉትን የደብረታቦር እና የአዲስ እመት በአላትን ምክንያት በማድረግ የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤዛ ኩሉ ሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ሆያ ሆዬ እና አበባይሆሽ ፈቃደኛ በሆኑ ምእመናን መኖሪያ ቤቶች እና በቤተክርስቲያናችን ዉስጥ ዘምረዋል:: እቅዳቸው ሁለት መልኮች ነበሩት::

አንደኛው እቅድ ሃይማኖታዊ ይዘቱን እንደያዘ ፣ ወግና ስርአቱን ለትውልድ ለማስተላለፍ ሲሆን ሁለተኛው እቅድ ደግሞ ለለአዲስ ቤተክርስቲያን ሕንጻ ማሰሪያ የሚሆን ገንዘብ ለማሰባሰብ የበኩላቸዉን ጥረት ለማድረግ ነበር:: በጥረታቸው የተስበስበውም የገንዘብ መጠንን በሚመለከት፣ ከሆያ ሆዬ መርኃ ግብር $4,439 ሲሆን ከ አበባይሆሽ ወይም እንቁጣጣሽ መርኃ ግብር ደግሞ $11,0051 ነው:: ከሁለቱ ዝግጅቶች የተስበስበው ጠቅላላ የገንዘብ መጠን በድምሩ $15,490 ደርሷል::

የቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች የሰበሰቡትን $15,490 በሙሉ ለአዲስ የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ማሰሪያ አገልግሎት ይውል ዘንድ በህንፃ አሰሪ ኮሚቴ በኩል ደረስኝ ተቆርጦለት ለቤተክርስቲያናችን ገቢ አድርገዋል::

ከዚህ በታች ያለዉ የሚያሳየዉ የቤዛ ኩሉ ስንበት ት/ቤት ነሐሴ 13 የደብረ ታቦርን በዓል በማስመልከት ፈቃደኛ በሆኑ ምእመናን መኖሪያ ቤቶች ድረስ በመሄድ ሆያ ሆዬ በመዘመር ለአዲስ ቤተክርስቲያን ሕንጻ ማሰሪያ የሚሆን የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ላይ ነዉ።

ከዚህ በታች ያለዉ የሚያሳየዉ የቤዛ ኵሉ ሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች ፈቃደኛ በሆኑ ምእመናን መኖሪያ ቤቶች ድረስ በመሄድ አበባይሆሽ በመዘመር ለአዲስ ቤተክርስቲያን ሕንጻ ማሰሪያ የሚሆን የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ላይ ነዉ።

ከዚህ በታች ያለዉ የሚያሳየዉ የቤዛ ኵሉ ሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች በቤተክርስቲያናችን ዉስጥ አበባይሆሽ በመዘመር ለአዲስ ቤተክርስቲያን ሕንጻ ማሰሪያ የሚሆን የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ላይ ነዉ።

የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችን እናመሰግናለን ! በረከቱን አብዝቶ ይስጥልን !

መረጃው የተገኘው ከደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የአዲስ ህንፃ አሰሪ ኮሚቴ ነዉ::

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ኢሜይል: membersservice@dsmachurch.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/

በ፪ሺ፲፭ ዓ.ም. የልጆች ትምህርት አገልግሎት በሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን

በሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የሰንበት ት/ቤት የልጆች ትምህርት ክፍል አገልግሎት ዘርፈ ብዙ የሆኑ ልዩ ልዩ ትምህርታዊ እና ማህበራዊ አገልግሎቶች ይሰጣሉ:: ለመጥቀሰም ያህል:-
ዘወትር ቅዳሜ ከ1.00pm-6.00pm ለልጆች የበገና ትምህርት፣ የወንጌል ትምህርት፣ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት እና የአብነት (የድቁና) ትምህርት ይሰጣል።

የቅዳሜ ክፍለ ግዜ በአራት የትምህርት ዘርፍ አገልግሎት ያተኩራል::
1.00pm-3.00pm የበገና ትምህርት
1.00pm-3.00pm የወንጌል ትምህርት ልጆች በየእድድሜያቸው በሁለት ክፍሎች::
4.00pm-5.00pm የአማርኛ ቋንቋ ማንበብ: የአማርኛ ቋንቋ መፃፍ: የአማርኛ ቋንቋ መስማትና መናገርን ያካተተ ትምህርት ይሰጣል::
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርቱም ለጀማሪ የሀሁ ፊደል ትምህርት, ለመሀከለኛ የቃላት ምስረታ ትምህርት, የመጨረሻ የንባብ እና የዓረፍተ ነገር ትምህርት::
5.00pm-6.00pm የአብነት (የድቁና ) ትምህርት

ዘወትር እሁድ ከቅዱስ ቁርባን በኋላ ለሕፃናትና ወጣቶች በ3 የእድሜ ክፍል (ከ5 እስከ 7 ዓመት፣ ከ8 እስከ 12 ዓመት፣ ከ13 ዓመት በላይ) መንፈሳዊ እና የመዝሙር ትምህርት ይሰጣል።
10.00am-10.30am የመፅሀፍ ቅዱስ ትምህርት
10.30am-11.00am የመዝሙር ትምህርት

ዘወትር እሁድ ከሰንበት አገልግሎት በኋላ ማኅበረ ካህናት እና የሰንበት ት/ቤት መዘምራን የየሰንበቱን እና የየበአላቱን ወረቦት/መዝሙሮች የማኅበር ቀለም ይሰማሉ/ያጠናሉ::

ሰመር ኮርስ:- ከሰኞ እስከ አርብ ለሁለት ተከታታይ ሳምንት የሚቆይ ሰመር ኮርስ ሰለ መሰረታዊ የሀይማኖት (የዶግማ) ትምህርት ይሰጣል:: ተማሪዎቹም በሶስት የዕድሜ ክፍል (ከ5ዓመት እስከ 8 ዓመት፣ ከ9 ዓመት እስከ 12 ዓመት፣ እና ከ13 ዓመት በላይ) ተመድበዉ ትምህርቱ ሙሉ ለሙሉ በእንግሊዘኛ ቋንቋ የሚሰጥ ፕሮግራም ነዉ::
በዚሁ በተጠናቀቀው በ፪ሺ፲፭ ዓ.ም. ለሁለት ሳምንት የቆዬ (June 12 – June 23) የልጆች ሰመር ኮርስ (summer courses) በሰላም ተጠናቋል::

ሰመር ካምፕ:- በዚሁ በተጠናቀቀው በ፪ሺ፲፭ ዓ.ም. ለህጻናት ታዳጊዎችና ወጣቶች ለአንድ ሳምንት የቆዬ የሰመር ካምፕ (ከJuly 17- July 21 ከጠሗት 9:00am – 2:30pm) ዝግጅ በጥሩ ውጤት እና በሰላም ተጠናቋል:: የሰመር ካምፑ የተለያዩ ልጆችን የሚያስተምሩ እና የሚያዝናኑ ዝግጅቶች ነበሩት::

የመዝናኛ እና የሽርሽር ጉዞ (field Trip):- በዚሁ በተጠናቀቀው በ፪ሺ፲፭ ዓ.ም. ለታዳጊ ወጣቶች ከዶ/ር ሲራክ በተገኘ የበጎፈቃደኝነት የገንዘብ እርዳታ ታዳጊዎችና ወጣቶችን ያሳተፈ የመዝናኛ አገልግሎት በ Valley Fair እንዲያገኙ ተደርጓል።

የመዝናኛ እና የሽርሽር ጉዞ (field Trip):- በዚሁ በተጠናቀቀው በ፪ሺ፲፭ ዓ.ም. ከዶ/ር ሲራክ በተገኘ የበጎፈቃደኝነት የገንዘብ እርዳታ ህጻናት ታዳጊዎችና ወጣቶችን ያሳተፈ በበንከር የውሀ ዳርቻ (Bunker beach) የመዝናኛ እና የሽርሽር ጉዞ (field Trip) በደመቀ መልኩ ተጠናቋል::

በዚሁ በተጠናቀቀው በ፪ሺ፲፭ ዓ.ም. የቤዛ ኩሉ ሰንበት ትምህርት ቤት የ27ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ውስጥ በድምቀት ተከብሯል።

አዲሱ ዘመንም የሰላም እና የጤና እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን:: በ፪ሺ፲፮ዓ.ም ቃለ እግዚአብሔር ለመማር፣ ንስሐ ለመግባት፣ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለመቀበል ያብቃን።

ለተጨማሪ ማብራሪያ ጥያቄ ካለዎት?
• ወ/ሮ ቀለም ደጀኔ 651-332-1544
• አቶ ጌታቸው ደበበ 651-366-1650
• ወ/ት ማህሌት ተፈራ 651-442-3738
• አቶ ይገርማል ፈጠነ 651-332-6098
• አቶ ዮሐንስ ከበደ 612-707-5212
• ወ/ት ማርታ 952-437-4312

ነሐሴንና ጳጉሜን የአዲስ የቤተክርስቲያን አባላት የትውውቅ ጊዜ እና የነባር የደብራችን አባላት የእንቅስቃሴ ወሮች እንዲሆኑ ስለማቀድ

በኢትዮጵያ አቆጣጠር የ2015 ዓ.ም.ን መገባደጃ በመንተራስ በቀሪዎቹ የነሐሴና ጳጉሜ ወሮች የአዲስ የቤተክርስቲያን አባላት የትውውቅ ጊዜ እና የነባር የቤተክርስቲያን አባላት እንቅስቃሴ መርኅግብሮች እንዲታቀዱ የአስተዳደር ቦርዱ ወስኖ የሚከተሉት መርኅግብሮች እንዲከናወኑ ይሆናል:: አዲስ የቤተክርስቲያን አባል ማለት በኢትዮጵያ አቆጣጠር የ2015 ዓ.ም የደብራችን አባል የሆኑ ማለት ነው::

የአዲስ አባላት የትውውቅ መርኅግብር:-

  1. እሁድ እሁድ ከቅዳሴ አገልሎት ፍፃሜ በሗላ እታች አዳራሽ ውስጥ አዲስ የቤተክርስቲያን አባሎቻችንን የእንኳን የደብራችን አባል ሆናችሁ በማለት የካህናት የአስተዳደር ቦርድ እና የአባላት ማኅበራት ተወካዮች ጋር ትዉዉቅ ይደረጋል::
  2. የእዲስ አባላት ስም ዝርርዝም እታች አዳራሽ ውስጥ በሚገኘው ቴሌቪዥን ስኪሪን ላይ ይተላለፋል::
  3. የቤተክርስቲያን አባልነት መታወቂያ ካርድ ላልወስዱ በእለቱ የቤተክርስቲያን አባልነት መታወቂያ ካርድ እንዲያወጡ ይደረጋል::
  4. በእለቱም ለ ዲስ አባላት ቡና ሻይና ዳቦ ካለ ይቀርባል::

የነባር የደብራችን አባላት እንቅስቃሴ መርኅግብር:-

  1. ነባር የቤተክርስቲያን አባሎች እሁድ እሁድ አታች አዳራሽ ውስጥ በሚገኘው የቦርድ አባላት የጠረጴዛ ቢሮ ድረስ በመሄድ የአባላት መዝገብ ላይ ያለው አድራሻችሁ ስልክ ቁጥራችሁና ኢሜል ትክክል እንደሆነ እንድታረጋግጡልን በአክብሮት እንጠይቃለን::
  2. የደብራችን አባልነት አዲስ መታወቂያ ካርድ ያላወጡ በእለቱ የቤተክርስቲያን አባልነት መታወቂያ ካርድ እንዲያወጡ ይደረጋል::
  3. የየደብራችን አባልነት የወርሀዊ መዋጮአችሁ መጠናቀቁን የቦርድ አባላትን መጠየቅና ውዝፍ ካለ በወቅቱ እንዲጠናቀቅ መሞከር
  4. የደብራችን አባል ያልህኑ ዘመዶች ጏደኞች እና ወዳጆችን የቤተክርስቲያኗ አባል እንዲሆኑ ማነቃቃትና ማበረታታት
  5. የቤተክርስቲያናችን የመረዳጃ ማህበር አባል ለመሆን መሞከር
  6. ገቢው ለአዲስ ቤ.ክ. ማስሪያ የሚውል የበጎፍቃድ ስራ አገልግሎት ላይ ለመሳተፍ ከፕሮግራሙ እስተባባሪ ከዶ/ር አሻግሬ መረጃ መጠየቅ

መርኅግብሮቹ ከመጪው እሁድ የቅዳሴ አገልሎት ፍፃሜ በሗላ ለአምስት ተከታታይ እሁዶች የምንከታተላቸው ይሆናል:: ቀኖቹም ነሐሴ7(Sug 13), ነሐሴ14(Aug 20), ነሐሴ21(Aug 27), ነሐሴ28(Sep 3), ጳጉሜ5(Sep 10) ናቸው::

ያቀድናቸውና ያሰብናቸው እንዲሳኩ ውድ የደብራችን ነባርና አዲስ የቤተክርስቲያን አባላት ከምንጊዜውም በበለጠ ሁኔታ የሰበካ ጉባዔውን እንድትተባበሩት በትህትና እንጠይቃለን:: በፅሁፍም ሆነ የመረጡትን የሰበካ ጉባዔ አባል በግል በመቅረብ አዳዲስ የአሰራር ሃሳቦችን እንድታካፍሉን ይሁን::

የደብራችን 2023 ተመራቂ ተማሪዎች እና ቤተሰቦች እንኳን ደስ ያላችሁ ! / Congratulations to 2023 Grads & Families!

“ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናችሁ” መዝ.118:26

በዘንድሮው የ2023 ዓ.ም. የ12ኛ ክፍልን እና የከፍተኛ ትምህርትን ላጠናቀቁ የቤተክርስቲያናችን ወጣቶች የእንኳን ደስ ያላችሁ የምስክር ወረቀት ቤተክርስቲያናችን ባለፈው እሁድ ሐምሌ 30 (Aug 6, 2023) አበርክታለች:: የሚቀጥለው የትምህርትና የመደበኛ ስራ ዘመናቸውም የተቃና እንዲሆንላቸውም ከእግዚያብሔር ቤት ተመርቀዋል::

Congratulations to 2023 grads and families. Graduates were handed out congratulating certificates by our church during the Sunday church services on Aug 6, 2023.

የደብራችን 2023 ተመራቂ ተማሪዎች እና ቤተሰቦች በድጋሚ እንኳን ደስ ያላችሁ !

ጾመ ፍልሰታ / የነሐሴ ቅዳሴ አገልግሎት ቀኖች እና የበጎፈቃደኝነት አገልግሎት ቀኖች / DSMA Calendar of Activities in August 2023

ከነሐሴ 1 እስከ ነሐሴ 16 (Aug 7 – Aug 22) ጾመ ፍልሰታ ሙሉ ቅዳሴ አለ

የንግሥ በአላት ፀሎት እና ቅዳሴ አገልግሎቶች / Annual Holidays and Celebrations with Liturgical services ነሐሴ 13 (Aug 19) – ደብረ ታቦር (Transfiguration- Debre Tabor)
ነሐሴ 16 (Aug 22) የነሐሴ ኪዳነምህረት ንግስ (The assumption of Virgin Mary)


የአዘቦት ቅዳሴ አገልግሎት ቀኖች ( Covenant prayer services)
ነሐሴ 12, ነሐሴ 19, ነሐሴ 21, ነሐሴ 27 (Aug 18, Aug 25, Aug 27, Sep 2)

የበጎፈቃደኝነት አገልግሎት ቀኖች / Volunteer Services dates for fundraising
. At the US Bank Stadium : Aug, 12, Aug 19 & Aug 26
. At the State Fair Parking : Aug 26 & Aug 27, Sep 2 to Sep 4

July 29, 2023 ልናደርገው የነበረው የገንዘብ ማሰባስብ እቅዳችንን ለመሰረዝ ተገደናል / BCC FUNDRAISER AT THE ETHIOPIA DAY IN MINNESOTA IS CANCELLED

የቤተክርስትያናችን የህንጻ ግንባታ ኮሚቴ አባላት July 29, 2023 በሚኒሶታ የኢትዮጵያ ቀን አከባበር ሜዳ ላይ ተገኝተዉ ምግብ መጠጥ እና ሌሎች ቁሳቁሶችን በመቨጥ ለአዲስ ቤተክርስቲያን ሕንፃ ግንባታ የሚዉል ገንዘብ እንደሚያሰባስቡና እናንተም እንድትጐቦኟቸው የሚል ማስተወቂያ በዚህ ገጽ ላይ መለጠፋችን ይታወሳል::

ነገር ግን ከዚህ በፊት ባልታዩ ምክኒያቶች ብቻ በሚኒሶታ የኢትዮጵያ ቀን አከባበር ሜዳ ላይ ተገኝተን ልናደርገው የነበረው የገንዘብ ማሰባስብ እቅዳችንን ለመሰረዝ ተገደናል:: ከይቅርታ ጋር!

Due to unforeseen circumstances, the upcoming BCC grill fundraiser event at the Minnesota Ethiopia Day celebration on July 29, 2023 is cancelled. Please accept our apology.

የዘንድሮዉ ዓመት የቅዱስ ገብርኤል በዓለ ንግስ እና የዋዜማ አገልግሎት፣ ሐምሌ 15 እና ሐምሌ 16, 2015 በሚኒሶታ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ይከበራል:: The annual Hamle Gebriel celebration will be on July 22 & July 23, 2023.

የዋዜማዉ አገልግሎት በመጪዉ ቅዳሜ ሐምሌ 15, 2015 (Saturday July 22, 2023) ከ 4pm ጀምሮ ይከበራል::

የማኅሌት አገልግሎት በመጪዉ እሁድ ሐምሌ 16, 2015 (Sunday July 23, 2023) ከንጋቱ 2 am ጀምሮ ይሰጣል::

ከቤተሰብ፣ ከዘመድ እና ከወዳጅ ጋር በመምጣት የቅዱስ ገብርኤልን በረከት ይካፈሉ ዘንድ ቤተክርስቲያናችን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN
55406

የዘንድሮዉ ዓመት የ5,000 ሜትር ርቀት ሩጫና እርምጃ መርኃ ግብር በደመቀ መልኩ በሰላም ተጠናቀቀ / This year’s 5K run and walk was a successful event

የሚኒሶታ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አባላት እና ቤተሰቦቻቸው ቅዳሜ ሰኔ 24 2015 (July 1st, 2023) በፌለን መናፈሻ ውስጥ ለዘጠነኛ ጊዜ የተዘጋጀውን የ5,000 ሜትር ሩጫና እርምጃ መርኃ ግብር በደመቀ መልኩ ተሳትፈው መርኃ ግብሩ በሰላም ተጠናቋል::

Members, families and friends of Debre Selam Medhanealem Ethiopian Orthodox Tewahedo Church in Minnesota came out in large numbers at the 9th annual 5K run and walk on July 1st, 2023 at Phalen Park, St Paul, Minnesota.

በእለቱም አሸናፊዎች የተዘጋጀላቸውን ሜዳልያና ምስክር ወረቀት ከደብራችን አስተዳዳሪ ከመልአከ ጽዮን ቀሲስ አዲስ ሞላው እና ከመርኃ ግብሩ አዘጋጆች ተቀብለዋል::
5K run and walk winners were recognized with medals and certificates from the head priest, Meleake Tsion Kesis Addis Molaw and event organizers.

Class of 2023 5K Run/Walk Winners

Females: 15 – 30 years old Group
1st. Yeabsra Berhanu / የብስራ ብርሃኑ
2nd. Mena Feleke / መና ፈለቀ
3rd. Lia Lantyderu / ሊያ ላንተይደሩ

Males: 15 – 30 years old Group
1st. Bisrat Gebre / ብሰራት ገብሬ
2nd. Kaleab Assefa / ካሌብ አሰፋ
3rd. Nathan Yohannes / ኔተን ዮሐንስ
4th. Naom Ewinetu / ናኦም እውነቱ

Females: 30+ years old Group
1st. Yeshi Getahun / የሺ ጌታሁን
2nd. Yeshiwork Zenebe / የሺወርቅ ዘነበ
3rd. Tigist Mengistu / ትእግስት መንግስቱ
4th. Genet Gebremichael / ገነት ገብረሚካኤል

Males: 30+ years old Group
1st. Kinfe Ashu / ክንፈ ኣሹ
2nd. Mitiku Desalegn / ምትኩ ደሳለኝ
3rd. Ephrem Ghida / ኤፍሬም ጊዳ
4th. Tewodros Desta / ቴዎድሮስ ደስታ
5th. Estefanos / እስጢፋኖስ
6th. Dawit Worku / ዳዊት ወርቁ
7th. Ashebir / አሸብር

ከቤተሰብ፣ ከዘመድ እና ከወዳጅ ጋር በመምጣት በመርኃ ግብሩ ተካፊይ ለሆኑ እና ለመርኃ ግብሩ አዘጋጆች በሙሉ ቤተ ክርስቲያን ምሰጋናዋን ታቀርባለች::

Thank you to the church members, families and event organizers who made the 9th 5K run and walk a success!.

በሰሞነ ህማማት የተላለፈው ውግዘት ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የጣሰ ነው ተባለ

የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትላንትናው ዕለት የቅዱስ ሚካኤልን በዓለ ንግስ ተጋባዥ እንግዳ መልአከ ምህረት ቆሞስ አባ ምህረት ዘውዴ በተገኙበት በደመቀና ባማረ መልኩ ያከበረ ሲሆን፤ በዕለቱም በደብረ ሰላም ካህናት ላይ ለምን በዕለተ ሆሳዕና ቀደሳችሁ ፣ ለምን ህዝበ ክርስቲያኑን አሳልፋችሁ ለተኩላ አልሰጣችሁም በማለት በአባ ዘካርያስ የተላለፈው የሰሞነ ህማማት ውግዘት  ኢቀኖናዊ መሆኑን አስተምረዋል።

መልአከ ምህረት ቆሞስ አባ ምህረት ዘውዴ በመቀጠልም በሰሞነ ህማማት እንኳን ውግዘት ማውገዝ ይቅርና ይፍቱህ መባል እንኳን በተከለከለበት ጊዜ ያውም በፀሎተ ሀሙስ ለካህናቱ የውግዘት ደብዳቤ መስጠት የቤክርስቲያንን ህግ የጣሰ መሆኑን ለተሰበሰበው ምዕመናን አስረድተዋል። የምስልና የድምጽ እንዲሁም ዝርዝር ዘገባውን ይዘን እንመለሳለን።

cdlabelየቤተ ክርስቲያኗ ምዕመናን የመልአከ ምህረት ቆሞስ አባ ምህረት ዘውዴ ስብከት በዲቪዲ ተባዝቶ አንዲቀርብላቸው በጠየቁት መሰረት በትላንትናው ዕለት ማለትም እሁድ ነሐሴ 28 2007 ወይንም July 5, 2015 የመጀመሪያውን ዙር ያከፋፈልን ሲሆን በተከታታይ ሳምንታትም ሁሉም ምዕመን እስኪዳረስ ድረስ አቅርቦቱ የሚቀጥል መሆኑን በታላቅ አክብሮት እንገልፃለን።

                            የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን 

Candlelight Vigil and Prayer Services in State Capitol and DSMA

LibyaMartyersPrayer2
Click on the image for more pictures

ባለፈው ኃሙስ በእስቴት ካፒቶል በሊቢያ በሰማዕትነት ላለፉት፣ በደቡብ አፍሪካና በየመን በግፍ ለተገደሉት ወገኖቻችን አስር የእምነት ተቋማት መሪዎች በተገኙበት በሚኒሶታ ውስጥ ለመጀመሪያ ግዜ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያኖች ተገኝተው የጸሎትና የሻማ ማብራት መርኃ ግብር የከወኑ ሲሆኑ ሁሉም የእምነት አባቶች ለህዝባችን አንድነት ለሀገራች ሰላምን ተመኝተዋል። እንዲሁም እሁድ በደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ ክርስቲያን በመቶዎች የሚቆጠሩ የቤ/ ክርስቲያኗ ምዕመናን በተገኙበት ከቅዳሴ በኃላ ፀሎተ ፍትኃት እና የጧፍ ማብራት መርኃ ግብር ተካሒዷል። ፀሎተ ፍትኃቱም እንደተጠናቀቀ በተደረገው የገንዘብ ማሰባሰብ ከ$20,000.00 በላይ ሊሰበሰብ ችሏል። ገንዘቡም በዓለም ዙሪያ በስቃይ ላይ ላሉ ኢትዮጵያዊያኖች መርጃ ይውላል።