ጾመ ነቢያት (የገና ጾም): ከህዳር 15, 2018 አስከ ታህሳስ 29, 2018

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

የተከበራችሁ የቤተክርስትያናችን አባላት እና ቤተሰቦች በሙሉ፤
እንኳን ለጾመ ነቢያት (የገና ጾም) በሠላም አደረሳችሁ።

የኢትዮያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰባት የአዋጅ አጽዋማት ያሏት ሲሆን ከእነዚህ የአዋጅ አጽዋማት መካከል አንዱ የነቢያት ጾም ነው። ጾሙን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ ከመገለጡና ሰው ከመሆኑ በፊት ነቢያት የጌታን መምጣት በናፍቆት በጾምና በጸሎት ሲጠባበቁ ነበር። ስለዚህ የነቢያትን የጾም ድካም ለማሰብና እንደ ነቢያት መንፈስ ኃይልን ለመልበስ በእምነት ለመጽናት ኃጢአትን ለመዋጋት ሲባል ይህን ጾም እኛ እንጾመዋለን።

ይህንን ጾም በተመለከተ በፍትሐ ነገሥት (ፍትሕ መንፈሳዊ) አንቀጽ ፲፭፥፭፻፷፬ ጀምሮ ተጽፏል። በፍትሕ መንፈሳዊ በአንቀጽ ፲፭፥፭፻፷፰ ላይ እንደተገለጸው ከኅዳር እኩሌታ እስከ ልደት የሚጾመው ጾም ነው። “መጀመርያው የኅዳር እኩሌታ፡ ፋሲካው፡ የልደት በዓል ነው።” ተብሎ የጾመ ነቢያት መነሻውና መድረሻውን ፍትሐ ነገስት ላይ ተገልጿል። ይህም ማለት በሦስቱ ወንጌላውያን ማለትም በዘመነ ማቴዎስ፣ በዘመነ ማርቆስና በዘመነ ሉቃስ የገና ጾም ከኅዳር ፲፭ ጀምሮ  በታኅሳስ ፳፱ ይፈሰካል።

ጾሙን የበረከት ያድርግልን!

ጾመ ነቢያት (የገና ጾም) :-
ከህዳር 15,2018 አስከ ታህሳስ 29, 2018
( Nov 24, 2025 – Jan 7, 2026)

ጽሁፉን ያዘጋጀችው ወይዘሮ ሐና ስዩም ነች::

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc
/