የዘንድሮው የከተራ እና ጥምቀት በዓል አከባበር እና የሃያ ሰባት አመቱ ቤዛኩሉ

በዚህ አመት የከተራ እና ጥምቀት በዓላት  ቅዳሜ ጥር 11, 2016 (Saturday Jan 20, 2016) እና እሁድ ጥር 12, 2016 (Sunday Jan 21, 2016) Bloomington Road, Fort Snelling, St. Paul, MN 55111 በሚገኘው ቦታ እንደወትሮው በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል:: የዘንድሮውን የጥምቀት በአል አከባበር ደማቅ እና ልዩ ያደረገው ነገር ቢኖር የሀገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ለመጀመሪያ ጊዜ በመሀከላችን ተገኝተው ቡራኬ መስጠታቸው እንዲሁም የቤዛ ኩሉ የሰንበት ት/ቤት ታዳጊና ወጣቶች በብዛት ሆኖ በመሳተፍና ያቀረቧቸው ልዩ ልዩ መዝሙራት እና ሌሎች መንፈሳዊ ዝግጅቶች በልዩ ሁኔታ የሚጠቀሱ ናቸው ::

በተለያዩ ምክንያቶች የበዓሉን አከባበር መርኃግብር በቦታው በመገኘት የበረከቱ ተሳታፊ ለመሆን ላልቻላችሁ ሁሉ ይጠቅማል በማለት የቤዛ ኩሉ ሰንበት ት/ቤት ታዳጊና ወጣቶች የሚዲያ ዝግጅት ክፍል ያካፈለንን ፎቶግራፎች ከዚህ በታች አቅርበናል::

የደብራችንን ታላቅነት ባገናዘበ መልኩ የቤዛ ኩሉ የሰንበት ት/ቤት ታዳጊና ወጣቶችም ላቀረቧቸው መዝሙራት ፣ ልዩ መንፈሳዊ እና ትምህርታዊ ዝግጅቶች በተጨማሪም ላሳያችሁት መልካም አርአያዊነት ተግባር እያመሰገንን የደከማችሁበት ሁሉ ስለተሳካላችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ እንላለን:: በዚህ አጋጣሚም  በደብራችን ውስጥ ለሚከናወኑት የሰንበ ት/ቤትና የልጆች ፕሮግራም ተሳታፊዎች: ካህናት: ፕሮግራም መሪዎች: አስተማሪዎች እና ወላጆች ሁሉ እንኳን ደስ ያላችሁ እንላለን። በተጨማሪም የቤዛ ኩሉ የሰንበት ት/ቤት ታዳጊና ወጣቶች የሚዲያ ዝግጅት ክፍልን ለፎቶግራፎቹ እጅግ በጣም እናመሰግናለን::

በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን
January 24, 2024
Minneapolis, Minnesota, U.S.A.

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/