
አዲስ አመት እንደመሆኑም የአመታዊ፣ የንግሥ በዓላት እና የአጿማት ቀን አቆጣጠሩ ላይ ብዙ ማወቅ የምትፈልጉት እንዳሉ እንገነዘባለን:: ለምሳሌም ያህል የጾም ቀኖች እና ወራቶች የትኞቹ ናቸዉ? የአመታዊ እና የንግሥ በዓላት የሚዉሉባቸዉ ቀኖችስ የትኞቹ ናቸዉ? በዩኤስ ባንክ ስታዲየም ለአዲስ ቤተክርስቲያን ማሰሪያ የሚውል የበጎፈቃደኝነት የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ቀኖች እና ወራቶችስ የትኞቹ ናቸዉ? የቤዛ ኩሉ ስንበት ት/ቤት የህጻናት ታዳጊዎችና ወጣቶች አገልግሎት መርኃ ግብሮች መቼ መቼ ሊውሉ እንደሚችሉ እቅድ እና ፕሮግራም ወጥቶላቸዋል ወይ? ይህ የቀን መቁጠሪያ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልሰ ይሰጣል:: ስለሆነም ከወዲሁ በመዘጋጀት ከመላዉ ቤተሰብ፣ ከዘመድ እና ከወዳጅ ጋር በመምጣት የበረከቱ ተካፊይ እንዲሆኑ የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።
- ማሕሌተ ጽጌ / ወርሃ ጽጌ (የፍቃድ ጾም ነው):- ከመስከረም 26, 2018 እሰከ ህዳር 6, 2018 ( Oct 6, – Nov 15, 2025)
- ጥቅምት መድኃኔዓለም :- በዓለ ንግስ:- ጥቅምት 30, 2018 ( Nov 9, 2025)
- የበጎፈቃደኝነት አገልግሎት በዩኤስ ባንክ ስታዲየም :- Sunday Nov 9, 2025.
- የበጎፈቃደኝነት አገልግሎት በዩኤስ ባንክ ስታዲየም :- Sunday Nov 16, 2025.
- ኅዳር ሚካኤል :- በዓለ ንግስ መርኃ ግብር የሚከናወንበት ቀን : ህዳር 14, 2018 ( Nov. 23, 2025) / Hidar St. Michael
- ጾመ ነቢያት (የገና ጾም) :- ከህዳር 15,2018 አስከ ታህሳስ 29, 2018 (Nov 24 – Jan 7, 2026)
- የበጎፈቃደኝነት አገልግሎት በዩኤስ ባንክ ስታዲየም :- Sunday Dec 7, 2025.
- የበጎፈቃደኝነት አገልግሎት በዩኤስ ባንክ ስታዲየም :- Thursday Dec 25, 2025.
- የታኅሳስ ገብርኤል :- በዓለ ንግስ:- ታኅሳስ 19, 2018 (Dec. 28, 2025) / Tahisas St. Gabriel
- የቤዛ ኩሉ ስንበት ት/ቤት የልጆች የገና በዓል ዝግጅት :- ታኅሳስ 25 , 2017 ( Jan 3, 2026)
- የበጎፈቃደኝነት አገልግሎት በዩኤስ ባንክ ስታዲየም :- Sunday Jan 4, 2026.
- የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት (ገና) :- ታኅሳስ 28, 2018 ( Jan 7, 2026) The Birth of Christ
- የጥምቀት ጾም (ጾመ ጋድ) :- ጥር 10, 2018 ( Jan 18, 2026)
- ጥምቀት:- ጥር 11, 2018 (Jan 19, 2026)
- ቃና ዘገሊላ:- ጥር 12, 2018 (Jan 20, 2026) / The Baptism of Christ (Epiphany).
- ጾመ ነነዌ :- ጥር 25, 2018 (Feb 2, 2026)
- የዓብይ ጾም (ጾመ ሁዳዴ ) :- የካቲት 9 አስከ ሚያዝያ 4, 2018( FEB.16, 2026 – APR.12, 2026)
- የካቲት ኪዳነምሕረት በዓለ ንግስ :- የካቲት 15, 2018 ( Feb. 22, 2026) / The Covenant of Virgin Mary.
- ደብረ ዘይት :- መጋቢት 6, 2018 (MAR. 15, 2026) / Debrezeit
- የቤዛ ኵሉ ሰንበት ት/ቤት የልጆች የበገና ምሽት :- መጋቢት 12, 2018 (March 21, 2026) Begna night
- የመጋቢት መድኃኔዓለም በዓለ ንግስ :- መጋቢት 27, 2018 (Apr. 5, 2026) / Megabit Medhanealem
- ሆሳዕና :- ሚያዝያ 27, 2018 ( April 5, 2026) / Hosanna
- ሰሙነ ሕማማት :- መጋቢት 28, እስከ ሚያዝያ 2, 2018 (April 6- APR 10, 2025) / Holy/Passion week.
- ጸሎተ ሐሙስ :- ሚያዝያ 1, 2018 (April 9, 2026) / Maundy Thursday
- ስቅለት :- ሚያዝያ 2, 2018 (April 10, 2026) / Good Friday (Crucifixion)
- ትንሣኤ :- ሚያዝያ 4, 2018 ( April 12, 2026) / Easter
- የእመቤታችን ልደት በአል :- ግንቦት 1, 2018 ( May 9, 2026) / The Birthday of Virgin Mary
- እርገት :- ግንቦት 13, 2018 ( May 21, 2026) / Ascension. The day of Holy Spirit
- ጰራቅሊጦስ :- ግንቦት 23, 2018 (May 31, 2026) / Peraklitos
- ጾመ ሐዋርያት (የሰኔ ጾም) :- ግንቦት 24, እሰከ ሀምሌ 5, 2018 (June 1, – July 12, 2026)
- ጾመ ድህነት (ጾመ ሐዋርያት) :- ግንቦት 26, 2018 ( June 3, 2026)
- የቤዛ ኵሉ ሰንበት ት/ቤት 29ነኛ የምስረታ በዓል :- ከሰኔ 28, 2018 ( JUN 5, 2026)
- ሰኔ ሚካኤል :- ሰኔ 14, 2018 (June 21,2026) Sene St. Michael.
- በአለ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ( አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ) :- ሐምሌ 5, 2018 (July 12, 2026) / The Martyrdom of Peter and Pau
- የሐምሌ ገብርኤል :- ሐምሌ 19, 2018 ( July 26, 2026) / Hamle St. Gabriel.
- ጾመ ፍልሰታ :- ከነሀሴ 1 – 16, 2018 ( August 7 – 22, 2026)
- የቤዛ ኵሉ ሰንበት ት/ቤት የልጆች ደብረ ታቦር በዓል ዝግጅት :- ነሐሴ 9, 2018 ( August 15, 2026)
- ደብረ ታቦር :- ነሐሴ 13, 2018 ( August 19, 2026) Transfiguration (Debre Tabor)
- ነሐሴ ኪዳነምሕረት :- ነሐሴ 16, 2018 ( August 22, 2026) The assumption of Virgin Mary.
ቀን መቁጠሪያውን ያዘጋጀችልንን ወ/ሮ ሀና ስዩምን እናመሰግናለን!
በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የስበካ ጉባኤ;;
አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ኢሜይል: membersservice@dsmachurch.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/