ጾመ ነቢያት (የገና ጾም): ቅዳሜ ኅዳር 15 ለሚጀመረው እና በረከት ለምናገኝበት ጾመ ነቢያት እንኳን አደረሰን!

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

የተከበራችሁ የቤተክርስትያናችን አባላት እና ቤተሰቦች በሙሉ፤
እንኳን ለጾመ ነቢያት (የገና ጾም) በሠላም አደረሳችሁ።

የኢትዮያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰባት የአዋጅ አጽዋማት ያሏት ሲሆን ከእነዚህ የአዋጅ አጽዋማት መካከል አንዱ የነቢያት ጾም ነው። ጾሙን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ ከመገለጡና ሰው ከመሆኑ በፊት ነቢያት የጌታን መምጣት በናፍቆት በጾምና በጸሎት ሲጠባበቁ ነበር። ስለዚህ የነቢያትን የጾም ድካም ለማሰብና እንደ ነቢያት መንፈስ ኃይልን ለመልበስ በእምነት ለመጽናት ኃጢአትን ለመዋጋት ሲባል ይህን ጾም እኛ እንጾመዋለን።

ይህንን ጾም በተመለከተ በፍትሐ ነገሥት (ፍትሕ መንፈሳዊ) አንቀጽ ፲፭፥፭፻፷፬ ጀምሮ ተጽፏል። በፍትሕ መንፈሳዊ በአንቀጽ ፲፭፥፭፻፷፰ ላይ እንደተገለጸው ከኅዳር እኩሌታ እስከ ልደት የሚጾመው ጾም ነው።
“መጀመርያው የኅዳር እኩሌታ፡ ፋሲካው፡ የልደት በዓል ነው።” ተብሎ የጾመ ነቢያት መነሻውና መድረሻውን ፍትሐ ነገስት ላይ ተገልጿል። ይህም ማለት በሦስቱ ወንጌላውያን ማለትም በዘመነ ማቴዎስ፣ በዘመነ ማርቆስና በዘመነ ሉቃስ የገና ጾም ከኅዳር ፲፭ ጀምሮ  በኅዳር ፳፱ ይፈሰካል። በዚህ በያዝነዉ በዘመነ ዮሐንስ ደግሞ የገና ጾም ቅዳሜ ኅዳር ፲፭  ተጀምሮ እሁድ ኅዳር ፳፰
ይፈሰካል።

ጾሙን የበረከት ያድርግልን!

ጾመ ነቢያት (የገና ጾም) :-
ከህዳር 15,2016 አስከ ታህሳስ 28, 2016
(Saturday Nov 25, 2023 – Sunday Jan 7, 2024)

ጽሁፉን ያዘጋጀችው ወይዘሮ ሐና ስዩም ነች::

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/