እንኳን ለ፳፻፲፮ ጽጌ ማሕሌት በሠላም አደረሳችሁ። /October 7, 2023 – November 16, 2023/

የተከበራችሁ የቤተክርስትያናችን አባላት እና ቤተሰቦች በሙሉ፤
እንኳን ለማሕሌተ ጽጌ በሠላም አደረሳችሁ።
ፅጌ ማለት አበባ ማለት ሲሆን ፀገየ ከሚለው የግዕዝ ቃል የመጣ ነው። ጽጌ ማሕሌት በየአመቱ ከመስከረም ፳፮ እስከ ህዳር ፮ (Oct 7, 2023 – Nov 16, 2023)
፵ ቀናት ወይም ፩ ወር ከ ፲ ቀን የሚቆይ ነው። ጽጌ ማሕሌት እመቤታችን ጌታችንን ይዛ መሰደዷን መራቧን መጠማቷን በማሰብ ነው

በማሕሌተ ጽጌ ወቅት ያሉት ሳምንታት ውብ ናቸው ምክንያቱም :-
☞እማምላክን ከነልጇ እንለምንበታለን ስደቷን እናስብበታለን፣
☞ የእመቤታችንን ፍቅሯን እናትነቷን አማላጅነቷን ከሊቃውንቱ ጋር ሆነን በዝማሬ እናወድስበታለን ፣

ጽጌ ማሕሌት የፈቃድ ፆም ስትሆን ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎች ብቻ ይፆሟታል። ምንም እንኳን ፆመ ፅጌ ከ ፯ ቱ የአዋጅ አፅዋማት መካከል ባትሆንም እና እንድንፆማት በአዋጅ ባንታዘዝም በፈቃዳችን በመፆማችን ከፆሟ ረድኤት በረከት የምናገኝባት ነች።

ሰንበትን ከጌታ ከኢየሱስ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋር ሌሊቱን በምስጋና በያሬዳዊ ዜማ ሳምንቱን ደግሞ በፈቃዳችን ማንም ሳያዘን የድንግል ማርያም ፍቅሯ አክብረን እንጾማለን።

እንኳን ለዚህ ጊዜ አደረሰን አደረሳችሁ !!!
የእመቤታችን ፍቅሯ ይብዛልን::

ጽሁፉን ያጠናቀረዉ አቶ ኤልያስ ወርቅህ ነዉ::

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ኢሜይል: membersservice@dsmachurch.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/