የቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ለአዲስ ቤተክርስቲያን ማሰሪያ የሚውል $15,490 አሰባስቡ!

ቀደም ብሎ እንደተገለፀው በቅርቡ ተከብረው ያለፉትን የደብረታቦር እና የአዲስ እመት በአላትን ምክንያት በማድረግ የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤዛ ኩሉ ሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ሆያ ሆዬ እና አበባይሆሽ ፈቃደኛ በሆኑ ምእመናን መኖሪያ ቤቶች እና በቤተክርስቲያናችን ዉስጥ ዘምረዋል:: እቅዳቸው ሁለት መልኮች ነበሩት::

አንደኛው እቅድ ሃይማኖታዊ ይዘቱን እንደያዘ ፣ ወግና ስርአቱን ለትውልድ ለማስተላለፍ ሲሆን ሁለተኛው እቅድ ደግሞ ለለአዲስ ቤተክርስቲያን ሕንጻ ማሰሪያ የሚሆን ገንዘብ ለማሰባሰብ የበኩላቸዉን ጥረት ለማድረግ ነበር:: በጥረታቸው የተስበስበውም የገንዘብ መጠንን በሚመለከት፣ ከሆያ ሆዬ መርኃ ግብር $4,439 ሲሆን ከ አበባይሆሽ ወይም እንቁጣጣሽ መርኃ ግብር ደግሞ $11,0051 ነው:: ከሁለቱ ዝግጅቶች የተስበስበው ጠቅላላ የገንዘብ መጠን በድምሩ $15,490 ደርሷል::

የቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች የሰበሰቡትን $15,490 በሙሉ ለአዲስ የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ማሰሪያ አገልግሎት ይውል ዘንድ በህንፃ አሰሪ ኮሚቴ በኩል ደረስኝ ተቆርጦለት ለቤተክርስቲያናችን ገቢ አድርገዋል::

ከዚህ በታች ያለዉ የሚያሳየዉ የቤዛ ኩሉ ስንበት ት/ቤት ነሐሴ 13 የደብረ ታቦርን በዓል በማስመልከት ፈቃደኛ በሆኑ ምእመናን መኖሪያ ቤቶች ድረስ በመሄድ ሆያ ሆዬ በመዘመር ለአዲስ ቤተክርስቲያን ሕንጻ ማሰሪያ የሚሆን የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ላይ ነዉ።

ከዚህ በታች ያለዉ የሚያሳየዉ የቤዛ ኵሉ ሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች ፈቃደኛ በሆኑ ምእመናን መኖሪያ ቤቶች ድረስ በመሄድ አበባይሆሽ በመዘመር ለአዲስ ቤተክርስቲያን ሕንጻ ማሰሪያ የሚሆን የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ላይ ነዉ።

ከዚህ በታች ያለዉ የሚያሳየዉ የቤዛ ኵሉ ሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች በቤተክርስቲያናችን ዉስጥ አበባይሆሽ በመዘመር ለአዲስ ቤተክርስቲያን ሕንጻ ማሰሪያ የሚሆን የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ላይ ነዉ።

የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችን እናመሰግናለን ! በረከቱን አብዝቶ ይስጥልን !

መረጃው የተገኘው ከደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የአዲስ ህንፃ አሰሪ ኮሚቴ ነዉ::

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ኢሜይል: membersservice@dsmachurch.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/