እናስተዋዉቅዎት! የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት የ፪ሺ፲፭ ዓ.ም. መርኃ ግብር

በቸርነትህ ዓመታትን ታቀዳጃለህ መዝ.64፥11

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

እግዚአብሔር አምላካችን በቸርነቱ ዓመታትን ለሁሉም ያቀዳጃል ከዓመት ወደ ዓመት በቸርነቱ ያሸጋግረናል። ያለፈው ዓመትን አሳልፎ አዲሱን ዓመት ስንቀበል ለሰራናቸው መልካም ስራዎች እውቅና ሰጥተን ጀምረን ያልጨረስናቸውን ደግሞ ለከርሞ ጨርሰን ልንሰራ ያሰብናቸውን ደግሞ እግዚአብሔርን አጋዥ አርገን እንሰራለን።

ከተመሰረተ 27 አመት ያስቆጠረዉ የቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት በደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያናችን ውስጥ ዓመት በዓመት ብዙ እንቅሳቃሴ እያደረገ እንዳለ የሚታወቅ ነዉ:: የቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት በውስጡ ታዳጊ እና ወጣቶችን አቅፎ የሚንቀሳቀስ ለቤተክርስቲያናች ተጠሪ ተቋም ነው። ሰንበት ትምህርት ቤታችን 9 የአገልግሎቶች ክፍሎች አሉት:: ከነዚህም ዉስጥ የልጆች ትምህርት ክፍል አገልግሎት ዘርፈ ብዙ የሆኑ ልዩ ልዩ ትምህርታዊ እና ማህበራዊ አገልግሎቶች ይሰጡበታል:: የደብረሰላም መድኃኔአለም የልጆች ክፍል አገልግሎቶችን በዝርዝር የሚገልፅ ፅሑፍ ከዚህ ቀደም አቅረበናል:: ለማንበብ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ::

የቤዛ ኩሉ ስንበት ት/ቤት መርኃ ግብር እና እንቅስቃሴ ሃይማኖታዊ የበጎ አድራጎት እና ማህበራዊ አገልግሎቶችን ይጨምራል::

  1. በ፪ሺ፲፭ ዓ.ም. በኢትዮጵያ የሚገኘው ሜሪጆይ በሚባል የእርዳታ ድርጅት ስር ካሉ ልጆች መካከል የቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት 20 ልጆችን ይረዳል::
  2. የሰንበት ትምህርት ቤት አባላትን በማስተባበር በካሊፎርኒያ ለሚገኘው ኆኅተ ሰማይ መጥምቀ መለኮት ዮሐንስ ወቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም የ $3000 ዶላር እርዳታ አበርክቷል።
  3. የቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት አባላት በማህሌት አገልግሎት ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ::
  4. የቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት አባላት በዓመቱ መጀመሪያ ላይ በቤተክርስቲያናችን ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6 ለ6 ሳምንታት በሚደረገው ጽጌ ማህሌት ላይ በመገኘት አገልግሎቱ እንዲጠነክር ጉልህ አስተዋጾ ያደርጋሉ::
  5. የቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት አባላት በበዓለ ንግስ ላይ በዝማሬ ያገለግላሉ::
  6. የደብረ ታቦር በዓልን የኢትዮጵያን ቱፊት ሳይለቅ፣ ሃይማኖታዊ ይዘቱን እንደያዘ፣ ለትውልድ ለማስተላለፍ ሆያ ሆዬ በመዘመር እና የችቦ ማብራት መርኃ ግብር በማዘጋጀትና በመምራት የቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት የበኩሉን አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል።
  7. አዲስ ዓመትን የኢትዮጵያን ቱፊት ለቅ፣ ሃይማኖታዊ ይዘቱን እንደያዘ፣ እንኳን አደረሳችሁ በማለት እና አበባይሆሽ በመዘመር ወግና ስርአቱን ለትውልድ ለማስተላለፍ የቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት የበኩሉን አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል።
  8. በተለያዩ ጊዜያት ከሌሎች የደብራችን አባላትና ቤተሰቦች ጋር በመሆን በዩኤስ ባንክ ስታዲየም ለአዲስ ቤተክርስቲያን ማሰሪያ የሚውል የበጎፈቃደኝነት የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ላይ የቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት አባላት አስተዋጽኦ ሲያደርጉ ቆይቷል።

የ፪ሺ፲፭ ዓ.ም. ልዩ ልዩ ተጨማሪ ክንዋኔዎችን በሚመለከት:-

ከዚህ በታች ያለዉ የሚያሳየዉ የቤዛ ኵሉ ሰንበት ተማሪዎች በማህሌት አገልግሎት ላይ ነዉ::

ከዚህ በታች ያለዉ የሚያሳየዉ የቤዛ ኵሉ ሰንበት ተማሪዎች በኪዳነ ምህረት በዓለ ንግስ ላይ በዝማሬ ሲያገለግሉ ነዉ::

ከዚህ በታች ያለዉ የሚያሳየዉ የቤዛ ኵሉ ሰንበት ተማሪዎች በበገና ምሽት መርኃ ግብር ላይ በበገና ዝማሬ ሲያቀርቡ ነዉ::

በ፪ሺ፲፭ ዓ.ም. ከተዘጋጁት እና ስኬታማ ከሚባሉት መርኃ ግብር መካከል አንዱ የቤዛ ኩሉ ስንበት ትምህርት ቤታችን የ27ተኛ ዓመት የምስረታ በዓል ነበር። ክብረ በዓሉ በተጋባዥ መምህራን ቃለ እግዚአብሔር የተሰጠበት ደማቅ እና የማይረሳ ነበር። በዚህ መርኃግብር ላይ የቤዛ ኩሉ ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ሆነው 2ተኛ ክፍልን ላጠናቀቁ ልጆች የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል።

ከዚህ በታች ያለዉ የሚያሳየዉ የቤዛ ኩሉ ስንበት ት/ቤት ነሐሴ 13 የደብረ ታቦርን በዓል በማስመልከት ፈቃደኛ በሆኑ ምእመናን መኖሪያ ቤቶች ድረስ በመሄድ ሆያ ሆዬ በመዘመር ለአዲስ ቤተክርስቲያን ሕንጻ ማሰሪያ የሚሆን የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ላይ ነዉ።

የደብረ ታቦር በዓልን የኢትዮጵያን ቱፊት ሳይለቅ፣ ሃይማኖታዊ ይዘቱን እንደያዘ፣ ለትውልድ ለማስተላለፍ ሆያ ሆዬ በመዘመር እና የችቦ ማብራት መርኃ ግብር በማዘጋጀትና በመምራት የቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት የበኩሉን አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል:: ከዚህ በታች ያለዉ የሚያሳየዉ የቤዛ ኩሉ ስንበት ት/ቤት ተማሪዎች የደብረ ታቦር (ቡሔ) የችቦ ማብራት መርኃ ግብር ላይ ሲዘምሩ ነዉ ::

የቤዛ ኵሉ ሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች አዲስ ዓመትን እንኳን አደረሳችሁ በማለት የኢትዮጵያን ቱፊት ስይለቅ፣ ሃይማኖታዊ ይዘቱን እንደያዘ ለትውልድ ለማስተላለፍ የበኩሉን አስተዋጾ እያደረገ ይገኛል። በመሆኑም ከዚህ በታች ያለዉ የሚያሳየዉ የቤዛ ኵሉ ሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች ፈቃደኛ በሆኑ ምእመናን መኖሪያ ቤቶች ድረስ በመሄድ አበባይሆሽ በመዘመር ለአዲስ ቤተክርስቲያን ሕንጻ ማሰሪያ የሚሆን የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ተከናውኗል።

አዲሱ ዘመን የደስታ የሰላም የፍቅር የይቅርታ የንስሀ ይሁንልን
የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት ዘወትር እሁድ ከቅዳሴ በኋላ 11፡30 AM ጀምሮ እስከ 1 PM ተከታታይ ትምህርት እንዲሁም በአባታችን በሊቀ ጠበብት መራዊ እና በወንድማችን አጋፋሪ ብርሃኑ ያሬዳዊ ዜማ እና ልዩ ልዩ መርኃግብሮች ይሰጣሉ:: መጥተው አብረን በአገልግሎት እንጠንክር።

እንድናገለግለው የፈቀደልን እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን
የእመቤታችን የድንግል ማርያም ምልጃ አይለየን

ይህን ጽሁፍ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ያዘጋጀችው እህታችን ወይዘሮ ሐና ስዩም ነች:: እባካችሁ አመሰግኑልኝ!

ለተጨማሪ ማብራሪያ?
• አቶ ዮሐንስ ከበደ 612-707-5212
• ወ/ት ማርታ 952-437-4312
• ወ/ት ማህሌት ተፈራ 651-442-3738
• አቶ ይገርማል ፈጠነ 651-332-6098
• አቶ እርስት መኮንን 952-221-6668
• አቶ ደባልቄ ገበየሁ 612-203-7745

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ኢሜይል: membersservice@dsmachurch.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
Facebook: https://www.facebook.com/Debreselameotc/