እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤ አደረሳችሁ!

ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃህ እምንዋም
እግዚአብሔር ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ (መዝሙረ ዳዊት ፸፰ ቁጥር ፷፭)

የተከበራችሁ የቤተክርስትያናችን አባላት እና ቤተሰቦች በሙሉ፤

ቅዳሜ ሚያዝያ 26, 2016 ዓ.ም. (Saturday May 4, 2024) ከ 5 ፒ.ኤም. ጀምሮ የትንሳኤን በአል በደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በመገኘት በማህሌት እና በቅዳሴ እብረን እናክብር!

የመድኃኔዓለም ቤተሰቦች ፣ ከዚህ በላይ ፎቶው የሚታየው የቤተክርስቲያናችን ተተኪ መምህር ዲያቆን ቃለ አብ አብይ ነዉ::

ከቤተሰብ፣ ከዘመድ እና ከወዳጅ ጋር በመምጣት የበረከቱ ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ ቤተክርስቲያናችን ጥሪዋን ታቀርባለች::

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/

የቤዛ ኩሉ የስንበት ት/ቤት 28ተኛ ዓመት ክብረ በአል ዝግጅት ሂደት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

እንኳን ለዚህች ታላቅ እለት ለእለተ ሆሣዕና በሰላም በጤና አደረሰን አደረሳችሁ::

ክርስቶስ የቤተክርስቲያን እራስ እንደሆነ ምእመናን ደግሞ የቤተክርስትያን አካል ናቸው::እንዲሁም ካህናት አባቶች ለቤተክርስትያን አገልግሎት ራስ እንደሆኑ ሰንበት ትምህርት ቤት ደግሞ ለቤተክርስትያን አገልግሎት አካላቶች ነን::

እኛ የደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስትያን የቤዛ ኲሉ ሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች ሰንበት ት/ቤታችን የተመሰረተበትን 28ተኛ ዓመቱን ከበአለ ትንሳኤ በኃላ በታላቅ ድምቀት ለማክበር ዝግጅቶችን እያዘጋጀን እንገኛለን::

ስለሆነም በየአመቱ እንደተለመደው የሰንበት ት/ቤታችንን ለማጠናከርና አገልግሎታችንን ለማሳደግ ይረዳን ዘንድ ከወዲሁ ገቢ ማስገኛ የሚሆኑ :-

  • የተለያዩ ስጦታ ያላቸው የዕጣ ትኬቶች (የመሸጫ ዋጋ $10)
  • ቲሸርቶች (የመሸጫ ዋጋ $15)
  • ከ8 ዓመት በታች ላሉ ልጆች ነጠላ (የመሸጫ ዋጋ $25)
  • ለአዋቂዎች የሚሆኑ ነጠላዎች (የመሸጫ ዋጋ $35)

አዘጋጅተን በጎግል ፎርም በቤተክርስትያኑ ለአገልግሎት በምንጠቀምባቸው ዌብሳይት ላይ በቫይበርና በዋትሳፕ እንዲሁም በቴሌግራም ግሩፕ ላይ አስቀምጠናል። ሁላችሁም ለዚህ አገልግሎት መሳካት የምትችሉትን ለሽያጭ ያቀረብናቸዉን በመግዛት ትተባበሩን ዘንድ በሰንበት ት/ቤታችን ስም ጥያቄአችንን እናቀርባለን::

እግዚአብሔር አምላክ ለዚህች ዕለት በሰላም በጤና ጠብቆ እንዳደረሰን ሁሉ ለበዓለ ትንሳኤው ከቁጥር ሳያጎድል በሰላም ያድርሰን::ከሁሉ በላይ ደግሞ በሰማያዊት እየሩሳሌም ሰብስቦ እንድናመሰግነው እርሱ ይፍቀድልን።

ወስበሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!

ጎግል ፎርም ማዘዢያ ፎርም ሊንክ

የሆሳዕና በዓልን እና የሰሙነ ሕማማት መርኃ ግብርን በሚኒሶታ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አብረን እናክብር!

የተከበራችሁ የቤተክርስትያናችን አባላት እና ቤተሰቦች በሙሉ፤

የሆሳዕና በአል

ማህሌት እሁድ ሚያዝያ 20, 2016 ከ 3 ኤ.ኤም. ጀምሮ (Sunday, April 28, 2024, from 3 am)

የሰሙነ ሕማማት መርኃ ግብር / Holy/Passion week.

ከስኞ ሚያዝያ 21, 2016 እስከ እስከ ረቡዕ ሚያዝያ 23, 2016, በየቀኑ ከ 6 ኤ.ኤም እስከ 2 ፒ .ኤም (Monday Apr 29, 2024 – May 1, 2024, 6 am – 2pm daily)

ጸሎተ ሐሙስ :- ሀሙስ ሚያዝያ 24, 2016 ከ 5 ኤ.ኤም. እስከ 2 ፒ.ኤም. (Thursday May 2, 2024, 5am – 2pm ) / Maundy Thursday

ስቅለት :- አርብ ሚያዝያ 25, 2016 ከ 6 ኤ.ኤም እስከ 6 ፒ.ኤም 6am – 6pm (Friday May 3, 2024) / Good Friday (Crucifixion)

ከቤተሰብ፣ ከዘመድ እና ከወዳጅ ጋር በመምጣት የበረከቱ ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ ቤተክርስቲያናችን ጥሪዋን ታቀርባለች::

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/

እንዳያመልጣችሁ! የበገና ምሽት ቅዳሜ ኤፕሪል 13, 2024 በሚኒስታ ደብረስላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አዳራሽ

ታላቅ የበገና ምሽት

በሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት ታዳጊ እና ወጣቶችተዘጋጅቶ ይቀርባል::

መቼ : ሚያዝያ 5, 2016 ዓ.ም. (April 13, 2024) ከቀኑ 4:00 ፒ.ኤም. ጀምሮ

እንዳያመልጣችሁ!
አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/