All posts by Admin

በሰሞነ ህማማት የተላለፈው ውግዘት ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የጣሰ ነው ተባለ

የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትላንትናው ዕለት የቅዱስ ሚካኤልን በዓለ ንግስ ተጋባዥ እንግዳ መልአከ ምህረት ቆሞስ አባ ምህረት ዘውዴ በተገኙበት በደመቀና ባማረ መልኩ ያከበረ ሲሆን፤ በዕለቱም በደብረ ሰላም ካህናት ላይ ለምን በዕለተ ሆሳዕና ቀደሳችሁ ፣ ለምን ህዝበ ክርስቲያኑን አሳልፋችሁ ለተኩላ አልሰጣችሁም በማለት በአባ ዘካርያስ የተላለፈው የሰሞነ ህማማት ውግዘት  ኢቀኖናዊ መሆኑን አስተምረዋል።

መልአከ ምህረት ቆሞስ አባ ምህረት ዘውዴ በመቀጠልም በሰሞነ ህማማት እንኳን ውግዘት ማውገዝ ይቅርና ይፍቱህ መባል እንኳን በተከለከለበት ጊዜ ያውም በፀሎተ ሀሙስ ለካህናቱ የውግዘት ደብዳቤ መስጠት የቤክርስቲያንን ህግ የጣሰ መሆኑን ለተሰበሰበው ምዕመናን አስረድተዋል። የምስልና የድምጽ እንዲሁም ዝርዝር ዘገባውን ይዘን እንመለሳለን።

cdlabelየቤተ ክርስቲያኗ ምዕመናን የመልአከ ምህረት ቆሞስ አባ ምህረት ዘውዴ ስብከት በዲቪዲ ተባዝቶ አንዲቀርብላቸው በጠየቁት መሰረት በትላንትናው ዕለት ማለትም እሁድ ነሐሴ 28 2007 ወይንም July 5, 2015 የመጀመሪያውን ዙር ያከፋፈልን ሲሆን በተከታታይ ሳምንታትም ሁሉም ምዕመን እስኪዳረስ ድረስ አቅርቦቱ የሚቀጥል መሆኑን በታላቅ አክብሮት እንገልፃለን።

                            የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን 

የሚካኤል በዓለ ንግስና የምስጋና ቀን June 20 & 21, 2015

St_MichaelJune 20
ከ3 – 5PM የቅዱስ ሚካኤል ዋዜማ
ከ5 – 9PM የምስጋና ዝግጅት (ቸሩ አባታችን በMay 11, 2014 በቤቱ ስላቆየን)

June 21
ከ3AM – 7AM ማኅሌት
ከ7AM – 10AM ስርዓተ ቅዳሴ
ከ10 AM – 12PM  መዝሙር፣ ስብከተ ወንጌል፣ ስርዓተ ንግስ
መጥተሁ ከቅዱስ ሚካኤል በረከት ይካፈሉ ዘንድ ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

Candlelight Vigil and Prayer Services in State Capitol and DSMA

LibyaMartyersPrayer2
Click on the image for more pictures

ባለፈው ኃሙስ በእስቴት ካፒቶል በሊቢያ በሰማዕትነት ላለፉት፣ በደቡብ አፍሪካና በየመን በግፍ ለተገደሉት ወገኖቻችን አስር የእምነት ተቋማት መሪዎች በተገኙበት በሚኒሶታ ውስጥ ለመጀመሪያ ግዜ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያኖች ተገኝተው የጸሎትና የሻማ ማብራት መርኃ ግብር የከወኑ ሲሆኑ ሁሉም የእምነት አባቶች ለህዝባችን አንድነት ለሀገራች ሰላምን ተመኝተዋል። እንዲሁም እሁድ በደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ ክርስቲያን በመቶዎች የሚቆጠሩ የቤ/ ክርስቲያኗ ምዕመናን በተገኙበት ከቅዳሴ በኃላ ፀሎተ ፍትኃት እና የጧፍ ማብራት መርኃ ግብር ተካሒዷል። ፀሎተ ፍትኃቱም እንደተጠናቀቀ በተደረገው የገንዘብ ማሰባሰብ ከ$20,000.00 በላይ ሊሰበሰብ ችሏል። ገንዘቡም በዓለም ዙሪያ በስቃይ ላይ ላሉ ኢትዮጵያዊያኖች መርጃ ይውላል።

የጸሎት አገልግሎት (Prayer Services)

Ethiopia

የፀሎተ ፍትኃት መርኃ ግብር በሊቢያ ለተሰውት ሰማዕታት

እሁድ April 26 2015 ከጠዋቱ 5AM  – 10 AM በፀሎትና በቅዳሴ

ከ10AM ጀምሮ በፀሎተ ፍትኃት ይታሰባሉ

 

ወቅታዊ መግለጫ:-       የሚኒሶታ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሊቢያ  በሚገኙ የእምነታችን ተከታዮች ላይ ራሱን አይ ኤስ እያለ በሚጠራው አሸባሪ ቡድን የተፈጸመባቸውን ዘግናኝ እና አሳዛኝ ግድያ በጽኑ ታወግዛለች።  በቀደሙት ዘመናት አባቶቻችን ቅዱሳን ሰማእታት ስለ እምነታቸው ሲሉ፣ ስለ ክረስቶስ ፍቅር ሲሉ፣ ስለ ቤተክርስቲያን ሲሉ በአላውያን ነገሥታት እና አሕዛብ መከራን ተቀብለዋል፣በመጋዝ ተሰንጥቀዋል፣ በእሳት ተቃጥለዋል፣ በፈላ ውኃ ተቀቅለዋል። ደማቸውንም ስለመንግሥተ ሰማያት ሲሉ አፍስሰዋል። ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

ዳግመ ትንሳኤ

PalmSunday30የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢ/ኦ/ተ ቤተ ክርስቲያን ከሆሳዕናና ከመድኃኔዓለም ንግስ ጀምሮ ፣ በሰመነ ህማማት፣ በጸሎተ ሐሙስ፣ በስቅለትና ከትንሳኤው ዋዜማ ጀምሮ በጣም ብዙ ህዝብ በተገኘበት በዓላቱን በደመቀ መልኩ አክብሯል፤ እነሆ አሁንም ዳግመ ትንሳኤን ዘንድሮ ለመጀመሪያ ግዜ ከጠዋቱ 4AM ጀምሮ በማህሌት፣ በቅዳሴና በስብከተ ወንጌል ሊያከብር ስላሰበ እርሶም መጥተው የበረከቱ ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

Easter 2015 Video (የትንሳኤ አገልግሎት ቪዲዮ)

ድንግል ሆይ በኃጢአት በፍትወት የተጸነስሽ አይደለሽም

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!

እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ “መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው” ብሎ ልበ አምላክ ዳዊት በመዝሙሩ ስለዘመረላት፤ ዳግመኛም ቅዱስ ያሬድ “ማርያምሰ ተኀቱ  እምትካት ውስተ ከርሱ ለአዳም ከመ ባሕርይ ጸዓዳ- ማርያምስ ከጥንት ጀምሮ በአዳም ባሕርይ ውስጥ እንደ ነጭ ዕንቁ ታበራለች (በደፈረሰው ዓለም በንጽሕና በቅድስና በድንግልና ታበራለች)” Continue reading ድንግል ሆይ በኃጢአት በፍትወት የተጸነስሽ አይደለሽም

የህማማት አገልግሎት

Click the video for Good Friday’s Service 

Passed Recorded Live Services (ያለፉትን ዕለታት አገልግሎት ለማየት)

የፀሎተ ሐሙስ አገልግሎት April 9 ከጠዋቱ 5AM ይጀምራል (Maundy Thursday Services Start April 9th @ 5AM) ጸሎተ ሐሙስ፣ ሕፅበተ ሐሙስ፣ የምስጢር ቀንና የሐዲስ ኪዳን ይባላል። ጸሎተ ሐሙስ የተባለው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአርአያነት በጌታ ሴማኒ ሲጸልይ በማደሩ ነው(ማቴ 26፥36)።  ሕፅበተ ሐሙስ መባሉም የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠቡ ነው፤ የምስጢር ቀን መባሉ ከሰባቱ ምስጢረ ቤተ ክርስቲያን አንዱ ምስጢረ ቁርባን የተመሰረተበት ዕለት በመሆኑ ነው። የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ መባሉም መሥዋዕተ ኦሪት አልፎ የሐዲስ ኪዳኑ መስዋዕት ሊሰዋ በመሆኑ ነው። ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው። (ሉቃ 22፥20)

የስቅለት አገልግሎት April 10 ከጠዋቱ 5AM ይጀምራል (Good Friday Services Start April 10th @ 5AM)

የመድኃኔዓለም ንግስና የሆሳዕና በዓል (Palm Sunday and our Savior’s Celebration)

PalmSunday30የመድኃኔዓለም ንግስና የሆሳዕና በዓል ብዙ ህዝብ በተገኘበት በደብረ ሰላም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በደመቀ ሁኔታ ተከበረ፤ አነሆ ስዕላዊ መግለጫውንና፤ ተስቀሳቃሽ ምስላዊ መግለጫውን  (Palm Sunday and our Savior’s Celebration at Debre Selam Medhanealem Ethiopian Orthodox Tewahedo Church, here is the pictures &  video – 2015)

 

የመድኃኔዓለም ዓመታዊ ንግስና የሆሳዕና በዓል April 5, 2015

April 4, 2015 ዋዜማና ስብከት በተጋባዣ እንግዳ ከ3PM ጀምሮ፤ እሁድ April 5 ማኅሌት፣ ቅዳሴና ስብከት ከ3:00AM ጀምሮ።

 ሆሣዕና ከስምንቱ የዐቢይ ጾም እሑዶች አንዱና የመጨረሻው ሳምንት ተብሎ የሚጠራው ከትንሣኤ ቀድሞ የሚገኝ የሕማማት መግቢያ ዋዜማ ነው። ሆሣዕና አስቀድሞ ካለው ረቡዕ ጀምሮ የሚታሰብ ታላቅ የቤተክርስቲያን የበዓል ቀን Continue reading የመድኃኔዓለም ዓመታዊ ንግስና የሆሳዕና በዓል April 5, 2015

7ኛው ሳምንት፦ ኒቆዲሞስ

ስያሜው የቅዱስ ያሬድ ነው። በዚህ ዕለት የፈሪሳውያን አለቃ ኒቆዲሞስ በሌሊት ወደ ጌታ መጥቶ ሲማር ጌታም ምስጢረ ጥምቀትን  ዳግም ልደትን ለኒቆዲሞስ እንዳስተማረው እየጠቀሰ ቅዱስ ያሬድ በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ሦስት ላይ ያለውን ስለዘመረው የዕለቱ ስያሜ ኒቆዲሞስ ተብሏል።

የስብሰባ ጥሪ/General Assembly Meeting

የፊታችን እሁድ March 22, 2015 ከቅዳሴ በኋላ የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ስለምናደርግ በዕለቱ ተገኝተው የስብሰባው ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች። በዕለቱም ቤተ ክርስቲያኗ ምሳ አዘጋጅታ ትጠብቅዎታለች፤ የሰማ ላልሰማ ያሰማ፤ “ትቀሩና ማርያምን እንጣላችኋለን” ይላሉ የሰበካ ጉባኤው አባላት። (Debreselam Ethiopian orthodox Tewhaedo Church will be holding a General Assembly Meeting on Sunday March 22, 2015 right after a Church Service (Liturgy).

የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የአስተዳደር ቦርድ (DSMA Board of Trustees)

5ኛው ሳምንት፦ ደብረ ዘይት

ይህ ዕለት ደብረ ዘይት ይባላል። ስያሜው እንደቀደሙት ሰንበታት ሁሉ የቅዱስ ያሬድ ስያሜ ሲሆን በዚህ ቀን መድኃኒታችን ሁለተኛ በግርማ መለኮት በክበበ ትስብእት (በመለኮታዊ ግርማው በሰው መጠን) እንደሚመጣ የዓለምም ፍጻሜው እንዴት እንደሚሆን ለሐዋርያት በደብረ ዘይት ማስተማሩን እንዲሁም በክብር ያረገው ጌታን ለሚጠባበቁት ዋጋቸውን ላልተቀበሉትም ፍዳቸውን ሊከፍል የምድርን ሥርዓት ሊሽር ሰማይና ምድርን አሳልፎ ለወዳጆቹ መንግስቱን ሊያወርስ የቅዱሳንንም እንባ ከዓይናቸው ሊያብስ ኃጥአንን ሊወቅስ ጻድቃንን ሊያወድስ (ብሩካን ብሎ) መምጣቱን እያሰበች ቤተ ክርስቲያን ፈጣሪዋን ታመልካለች። ቅዱስ ያሬድም ይህንኑ ትምህርት በመዝሙሩ ጠቅሶ ስለዘመረውና በዚህ ቀንም እንዲዘመር ስለተደረገ ዕለቱ በባለዜማው ይትበሃል ደብረ ዘይት ይባላል።

4ኛው ሳምንት፦ መፃጉዕ

ይህ ዕለት የዓቢይ ጾም አራተኛ ሰንበት ነው። ስሙም እንደ ቅዱስ ያሬድ የዜማ ስያሜ «መፃጉዕ» ይባላል። በዚህ ዕለት ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሽተኞችን ስለማዳኑ፣ ተአምራትን ስለማድረጉ፣ ጎባጣዎችን ስለማቅናቱ፣ ለምጻሞችን ስለማንጻቱ፣ ስለ መለኮታዊ ማዳኑ እና ታምራት ይመለካል።  To Read More

3ኛው ሳምንት፦ ምኩራብ

ይህ የሦስተኛው ሰንበት ስያሜ ሲሆን በዚህ ዕለት ጌታ በመዋዕለ ትምሕርቱ በምኩራብ ገብቶ እንዳስተማረ የሚታሰብበት ዕለት ነው።

ምኩራብ ምንድን ነው? የአይሁድ የጸሎት ቤት ነው። በብሉይ ዘመን የአይሁድ አምልኮ በኢየሩሳሌም በነበረዉ ቤተ መቅደስ በሥርዐቱ የተመሠረተ ነበር ። ናቡከደነፆር  ግን ቤተ መቅደሱን አፈረሰ ፤ ሕዝቡን ወደ ባቢሎን አፈለሰ፤  ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አይሁድ በሚገኙባቸው ስፍራዎች ሁሉ ለጸሎትና ለማሕበርተኛነት ልዪ ቤት መስራት እንደጀመሩ ይገመታል ። ሕዝ 11፣16 በክርስቶስ ጊዜ በእስራኤል ሐገር በየቦታው በኢየሩሳሌምም ብዙ ሙክራቦች ነበሩ።

ሐዋርያትም አይሁድ በተበተኑባቸዉ ቦታዎች ሲዘዋወሩ አስቀድመው ወደ ምኩራብ ገብተዉ ወንጌልን ያስተምሩ ነበር። ማቴ 4፣23 ሐዋ 6፣9  13፤5-14 Continue reading 3ኛው ሳምንት፦ ምኩራብ

የኪዳነ ምሕረት ንግስ ዝማሬ


የኪዳነ ምሕረት ንግስ በደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢ/ኦ/ተ ቤ/ክርስቲያን February 22, 2015

Medhanialem church Minnesota kidaneኪዳን የሚለው ቃል ተካየደ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ተማማለ፣ ተስማማ፣ ውል ገባ ማለት ነው፡፡ ኪዳነ ምሕረት ማለትም ደግሞ የምሕረት ቃል ኪዳን ማለት ነው፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ስለሰው ልጆች ይቅርታ የገባላት ቃል ኪዳን ነው፡፡ እግዚአብሔርን ለሚፈሩት፣ ለሚያከብሩት፣ ለሚወዱትና ለሚወዳቸው ሁሉ በተለያዩ ጊዜያት ብዙ ኪዳናትን ሰጥቷል እና፡፡