3ኛው ሳምንት፦ ምኩራብ

ይህ የሦስተኛው ሰንበት ስያሜ ሲሆን በዚህ ዕለት ጌታ በመዋዕለ ትምሕርቱ በምኩራብ ገብቶ እንዳስተማረ የሚታሰብበት ዕለት ነው።

ምኩራብ ምንድን ነው? የአይሁድ የጸሎት ቤት ነው። በብሉይ ዘመን የአይሁድ አምልኮ በኢየሩሳሌም በነበረዉ ቤተ መቅደስ በሥርዐቱ የተመሠረተ ነበር ። ናቡከደነፆር  ግን ቤተ መቅደሱን አፈረሰ ፤ ሕዝቡን ወደ ባቢሎን አፈለሰ፤  ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አይሁድ በሚገኙባቸው ስፍራዎች ሁሉ ለጸሎትና ለማሕበርተኛነት ልዪ ቤት መስራት እንደጀመሩ ይገመታል ። ሕዝ 11፣16 በክርስቶስ ጊዜ በእስራኤል ሐገር በየቦታው በኢየሩሳሌምም ብዙ ሙክራቦች ነበሩ።

ሐዋርያትም አይሁድ በተበተኑባቸዉ ቦታዎች ሲዘዋወሩ አስቀድመው ወደ ምኩራብ ገብተዉ ወንጌልን ያስተምሩ ነበር። ማቴ 4፣23 ሐዋ 6፣9  13፤5-14

ዐሥር የጎለመሱ ወንዶች ሲገኙ ምኩራብን መስራት ይፈቀድላቸው ነበር። በምኩራብ ውስጥ ሕግና ነቢያት የተፃፈባቸው የብራና ጥቅልሎች በአንድ ሳጥን ውስጥ ይቀመጡ ነበር። የእግዚአብሔር ቃል ሲነበብ አንባቢው በተዘጋጀው ከፍተኛ ቦታ ይቆም ነበር።ማቴ 23፤6

ወንዶችና ሴቶች ለየብቻቸው ይቆሙ ነበር።

ምኩራብ ለአምልኮና ለትምሕርት ለሕብረተሰቡም መገልገያ ይውል ነበር።ምኩራብ በአለቆቹ ይመራ ነበር። ማር 5፤22  ሐዋ 13፤15

ጉባዔውን የሚመሩት የምኩራቡ አለቆች ነበሩ ሐዋ 13፤15

ጥፋተኛ ሰዉ  ካለ  እስከ 39 ግርፋት በመግረፍ ከምኩራብ በማስወጣት ሊቀጡ ሥልጣን ነበራቸው። ዮሐ 9፤34    2ቆሮ 11፤24

በየሰንበቱ ሁሉ በምኩራብ ይሰበሰቡ ነበር። ሉቃ 4፤16   ሐዋ ሥራ 15፤21

በአምልኮታቸው ውስጥ ጸሎት ከሕግ እና ከነቢያት ንባብ የዳዊት መዝሙራት ስብከትና ቡራኬም ነበር።

የዕለቱ መልዕክታት

ቁላስ 2፤16-ፍ:ም  ዋናው ዲያቆን

ያዕቆብ 2፤14-ፍ:ም  ንፍቅ ዲያቆን

ግብ:ሐዋ 10፤1-9 ንፍቅ ካሕን

ምስባክ

እስመ ቅንዐተ ቤትከ በልዐኒ

ትዕይርቶሙ ለእለ ይትዔየሩከ ወድቀ ላዕሌየ

ወቀፃዕክዋ በጾም ለነፍስየ

መዝ ፹፹፤፱ 88፤9

ወንጌል

ዮሐንስ 2፤12 ፍ:ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *