በሰሞነ ህማማት የተላለፈው ውግዘት ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የጣሰ ነው ተባለ

የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትላንትናው ዕለት የቅዱስ ሚካኤልን በዓለ ንግስ ተጋባዥ እንግዳ መልአከ ምህረት ቆሞስ አባ ምህረት ዘውዴ በተገኙበት በደመቀና ባማረ መልኩ ያከበረ ሲሆን፤ በዕለቱም በደብረ ሰላም ካህናት ላይ ለምን በዕለተ ሆሳዕና ቀደሳችሁ ፣ ለምን ህዝበ ክርስቲያኑን አሳልፋችሁ ለተኩላ አልሰጣችሁም በማለት በአባ ዘካርያስ የተላለፈው የሰሞነ ህማማት ውግዘት  ኢቀኖናዊ መሆኑን አስተምረዋል።

መልአከ ምህረት ቆሞስ አባ ምህረት ዘውዴ በመቀጠልም በሰሞነ ህማማት እንኳን ውግዘት ማውገዝ ይቅርና ይፍቱህ መባል እንኳን በተከለከለበት ጊዜ ያውም በፀሎተ ሀሙስ ለካህናቱ የውግዘት ደብዳቤ መስጠት የቤክርስቲያንን ህግ የጣሰ መሆኑን ለተሰበሰበው ምዕመናን አስረድተዋል። የምስልና የድምጽ እንዲሁም ዝርዝር ዘገባውን ይዘን እንመለሳለን።

cdlabelየቤተ ክርስቲያኗ ምዕመናን የመልአከ ምህረት ቆሞስ አባ ምህረት ዘውዴ ስብከት በዲቪዲ ተባዝቶ አንዲቀርብላቸው በጠየቁት መሰረት በትላንትናው ዕለት ማለትም እሁድ ነሐሴ 28 2007 ወይንም July 5, 2015 የመጀመሪያውን ዙር ያከፋፈልን ሲሆን በተከታታይ ሳምንታትም ሁሉም ምዕመን እስኪዳረስ ድረስ አቅርቦቱ የሚቀጥል መሆኑን በታላቅ አክብሮት እንገልፃለን።

                            የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን