በሰሞነ ህማማት ያውም በፀሎተ ኃሙስ ማውገዝ የቤተክርስቲያንን አስተምህሮት የጣሰና ኢቂኖናዊ ነው ተባለ

የቤተ ክርስቲያኗ ምዕመናን የመልአከ ምህረት ቆሞስ አባ ምህረት ዘውዴ ስብከት በዲቪዲ ተባዝቶ ለወደፊትም ለታሪክ ማጣቀሻ ይረዳ ዘንድ አንዲቀርብላቸው በጠየቁት መሰረት ከእሁድ ነሐሴ 28 2007 ወይንም July 5, 2015 ጀምሮ ለደብሩ መዕመናን ያከፋፈልን ሲሆን፤ ከዚህ በኋላ እውነታውን በአለም ላይ የተበተነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ ይረዳው ዘንድ በደብሩ ድረ ገጽ፣ ፊስቡክ አካውንት አንዲሁም በሌሎች ድረ ገጾች እንለቃለን።

የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳትሆን በከፍተኛ ደረጃ ኢትዮጵያዊነት የሚንጸባረቅባት የኃይማኖት ተቋም በመሆኗ፣ በዘር፣ በቋንቋ ፣ እንዲሁም በጐጥ ያልተከፋፈለች ስለነበረች በኃይማኖት ሽፋን ለረዥም አመታት አብሮ የኖረን ህዝብ በዕለተ ሆሳዕና ለምን ቀደሳችሁ ብሎ በካህናቱ ላይ በሰሞነ ህማማት ያውም በፀሎተ ኃሙስ በአባ ዘካሪያስ የተላለፈው ውግዘት የቤተክርስቲያንን አስተምህሮት የጣሰና ኢቂኖናዊ መሆኑን መልአከ ምህረት ቆሞስ አባ ምህረት ዘውዴ ፍትሃ ነጋስትን በማጣቀስ እስተምረዋል። በመቀጠልም በሰሞነ ህማማት እንኳን ውግዘት ማውገዝ ይቅርና ይፍቱህ መባል እንኳን በተከለከለበት ጊዜ ያውም በፀሎተ ሀሙስ ለካህናቱ የውግዘት ደብዳቤ መስጠት የቤክርስቲያንን ህግ የጣሰ፣ ታይቶም ሆነ ተሰምቶ የማይታወቅ፣ ወደፊትም የማይታይ መሆኑን ለተሰበሰበው ምዕመናን አስረድተዋል። የምስልና የድምጽ ዝርዝር መልዕክቱን ከቪዲዮው ይመልከቱ