7ኛው ሳምንት፦ ኒቆዲሞስ

ስያሜው የቅዱስ ያሬድ ነው። በዚህ ዕለት የፈሪሳውያን አለቃ ኒቆዲሞስ በሌሊት ወደ ጌታ መጥቶ ሲማር ጌታም ምስጢረ ጥምቀትን  ዳግም ልደትን ለኒቆዲሞስ እንዳስተማረው እየጠቀሰ ቅዱስ ያሬድ በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ሦስት ላይ ያለውን ስለዘመረው የዕለቱ ስያሜ ኒቆዲሞስ ተብሏል።

የስብሰባ ጥሪ/General Assembly Meeting

የፊታችን እሁድ March 22, 2015 ከቅዳሴ በኋላ የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ስለምናደርግ በዕለቱ ተገኝተው የስብሰባው ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች። በዕለቱም ቤተ ክርስቲያኗ ምሳ አዘጋጅታ ትጠብቅዎታለች፤ የሰማ ላልሰማ ያሰማ፤ “ትቀሩና ማርያምን እንጣላችኋለን” ይላሉ የሰበካ ጉባኤው አባላት። (Debreselam Ethiopian orthodox Tewhaedo Church will be holding a General Assembly Meeting on Sunday March 22, 2015 right after a Church Service (Liturgy).

የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የአስተዳደር ቦርድ (DSMA Board of Trustees)

5ኛው ሳምንት፦ ደብረ ዘይት

ይህ ዕለት ደብረ ዘይት ይባላል። ስያሜው እንደቀደሙት ሰንበታት ሁሉ የቅዱስ ያሬድ ስያሜ ሲሆን በዚህ ቀን መድኃኒታችን ሁለተኛ በግርማ መለኮት በክበበ ትስብእት (በመለኮታዊ ግርማው በሰው መጠን) እንደሚመጣ የዓለምም ፍጻሜው እንዴት እንደሚሆን ለሐዋርያት በደብረ ዘይት ማስተማሩን እንዲሁም በክብር ያረገው ጌታን ለሚጠባበቁት ዋጋቸውን ላልተቀበሉትም ፍዳቸውን ሊከፍል የምድርን ሥርዓት ሊሽር ሰማይና ምድርን አሳልፎ ለወዳጆቹ መንግስቱን ሊያወርስ የቅዱሳንንም እንባ ከዓይናቸው ሊያብስ ኃጥአንን ሊወቅስ ጻድቃንን ሊያወድስ (ብሩካን ብሎ) መምጣቱን እያሰበች ቤተ ክርስቲያን ፈጣሪዋን ታመልካለች። ቅዱስ ያሬድም ይህንኑ ትምህርት በመዝሙሩ ጠቅሶ ስለዘመረውና በዚህ ቀንም እንዲዘመር ስለተደረገ ዕለቱ በባለዜማው ይትበሃል ደብረ ዘይት ይባላል።

4ኛው ሳምንት፦ መፃጉዕ

ይህ ዕለት የዓቢይ ጾም አራተኛ ሰንበት ነው። ስሙም እንደ ቅዱስ ያሬድ የዜማ ስያሜ «መፃጉዕ» ይባላል። በዚህ ዕለት ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሽተኞችን ስለማዳኑ፣ ተአምራትን ስለማድረጉ፣ ጎባጣዎችን ስለማቅናቱ፣ ለምጻሞችን ስለማንጻቱ፣ ስለ መለኮታዊ ማዳኑ እና ታምራት ይመለካል።  To Read More

3ኛው ሳምንት፦ ምኩራብ

ይህ የሦስተኛው ሰንበት ስያሜ ሲሆን በዚህ ዕለት ጌታ በመዋዕለ ትምሕርቱ በምኩራብ ገብቶ እንዳስተማረ የሚታሰብበት ዕለት ነው።

ምኩራብ ምንድን ነው? የአይሁድ የጸሎት ቤት ነው። በብሉይ ዘመን የአይሁድ አምልኮ በኢየሩሳሌም በነበረዉ ቤተ መቅደስ በሥርዐቱ የተመሠረተ ነበር ። ናቡከደነፆር  ግን ቤተ መቅደሱን አፈረሰ ፤ ሕዝቡን ወደ ባቢሎን አፈለሰ፤  ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አይሁድ በሚገኙባቸው ስፍራዎች ሁሉ ለጸሎትና ለማሕበርተኛነት ልዪ ቤት መስራት እንደጀመሩ ይገመታል ። ሕዝ 11፣16 በክርስቶስ ጊዜ በእስራኤል ሐገር በየቦታው በኢየሩሳሌምም ብዙ ሙክራቦች ነበሩ።

ሐዋርያትም አይሁድ በተበተኑባቸዉ ቦታዎች ሲዘዋወሩ አስቀድመው ወደ ምኩራብ ገብተዉ ወንጌልን ያስተምሩ ነበር። ማቴ 4፣23 ሐዋ 6፣9  13፤5-14 Continue reading 3ኛው ሳምንት፦ ምኩራብ

የኪዳነ ምሕረት ንግስ ዝማሬ


የኪዳነ ምሕረት ንግስ በደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢ/ኦ/ተ ቤ/ክርስቲያን February 22, 2015

Medhanialem church Minnesota kidaneኪዳን የሚለው ቃል ተካየደ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ተማማለ፣ ተስማማ፣ ውል ገባ ማለት ነው፡፡ ኪዳነ ምሕረት ማለትም ደግሞ የምሕረት ቃል ኪዳን ማለት ነው፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ስለሰው ልጆች ይቅርታ የገባላት ቃል ኪዳን ነው፡፡ እግዚአብሔርን ለሚፈሩት፣ ለሚያከብሩት፣ ለሚወዱትና ለሚወዳቸው ሁሉ በተለያዩ ጊዜያት ብዙ ኪዳናትን ሰጥቷል እና፡፡

ዐብይ ጾመ

እንኳን እግዚአብሔር አምላክ ለዚህ ታላቅ ጾም በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!

ይህንን ጾም በእስር ቤት ላሉት ለታመሙት ለተጨነቁት ወገኖቻችን እግዚአብሔር  የቸርነቱን ሥራ ይሰራላቸው ዘንድ በፀሎት ፤በሐሳብ ከእነሱ ጋር እንድንሆን እግዚአብሔር ይርዳን ጾሙንም የኀጢአት መደምሰሻ የዲያብሎስ ድል መንሻ የመንግስተ ሰማያት መውረሻ ያድርግልን።

ዐቢይ የሚለው ቃል ዐብየ ከፍ ከፍ አለ ከሚለዉ የግዕዝ ግስ የወጣ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ታላቅ ማለት ነው፤ ይህንን ጾም አባቶቻችን በተለያየ ስያሜ ጠርተውታል፣ ጌታ እራሱ የጾመው ስለሆነ የጌታ ጾም በመባል ይጠራል በጾሙም ወቅት ሦስቱ የሰይጣን ፈተናዎች ማለትም ትዕቢት፣ ስስት፣ ፍቅረ ነዋይ ድል ተመተውበታል ጾሙም ብዙ መንፈሳዊ በረከት ስለምናገኝበት ጾመ ሁዳዴ በመባልም ይጠራል።

ጾሙ በድምሩ 55 ቀን ይጾማል ጌታ የጾመው 40 ቀን አይደል? ለምን 55 ሆነ ቢሉ Continue reading ዐብይ ጾመ

ጾመ ነነዌ /Tsome Nenewe((The fast of Nineveh)

ጾመ ነነዌ – ሰኞ ጥር 25, 2007 ይጀምራል Tsome Nenewe (The fast of Nineveh): 3 days fasting which starts on the Monday proceeding before Abye Tsome (Lent) – Start on Monday February 02, 2015 – 04, 2015

Abye Tsome or Hudade (Lent): 55 days Fasting before Easter which is divided in to the following three categories: – Lent start on February 16, 2015

  • Tsome Hirkal: 8 days fasting which starts 8 days proceeding before Tsome Arba.
  • Tsome Arba: 40 days fasting which starts immediately after Tsome Hirkan up to Palm Sunday.
  • Tsome Himamat: 7 days fasting which starts on the Monday after Palm Sunday until Easter

የጥምቀት በዓል በደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በደመቀ መልኩ ተከበረ

Video 1 

Video 2

ጥር 11 ቀን 2007 ዓ.ም

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን።

Timket5የ2007 ዓ.ም የጥምቀት በአል በሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ቁጥሩ በመቶዎች የሚገመት ምእመን በተገኘበት እጅግ ደማቅ በሆነ ኃይማኖታዊ ሥነ ሥርአት ተከበሮ ዋለ። Continue reading የጥምቀት በዓል በደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በደመቀ መልኩ ተከበረ

ጥምቀት ምንድን ነው? ለምንስ እንጠመቃለን?

TimketHannaጥምቀት “አጥመቀ” ከሚለው የግእዝ ቃል/ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም በውኃ ውስጥ መዘፈቅ ወይንም መነከር ማለት ነው። ጥምቀት ከጌታችን እና ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት በፊትም የነበረ ሰዎች ከህመማቸው ፈውስ የሚያገኙበት ማለትም የሥጋ ድህነት ከሚገኝበት የፈውስ መንገዶች አንዱ ነበረ። Continue reading ጥምቀት ምንድን ነው? ለምንስ እንጠመቃለን?

Epiphany/በዓለ ጥምቀት

Gehad Fasting – የጥምቀት ፆመ ገሃድ(ጋድ) – January 18, 2015 (ጥር 10, 2007) – This fasting is observed on the eve of Epiphany.

Epiphany Celebration On January 17, 2015 starting @ 3PM , Sunday Service Start @ 2AM –  (የጥምቀትን በዓል በደመቀ ሁኔታ በ2007 (2015) ለመጀመሪያ ግዜ  እናከብራለን )

Timket

ቅዳሜ – ስብከተ ወንጌል እና ዝማሬ – በተጋበዥ ሰባኪ መንጌል እና በተጋበዥ ዘማሪ ከ 5PM ጀምሮ 

እሁድ ከ 2AM – 7AM ማኅሌት 

ከ7AM – 10AM ቅዳሴ

ከ10AM – 12AM ስብከተ ወንጌልና ታቦታቱን ማክበር 

የበዓለ ጥምቀቱን በረከት መጥተሁ ይካፈሉ ዘንድ ቤ/ክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች

የልደት ዝማሬ

የጌታችን እና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደተ በዓል አከባበር በሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ

Christmas2015_6የዘንድሮው የ2007 ዓ.ም የልደት በአል በደብራችን ከመቼውም ጊዜ ለየት ባለና በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል። ለበአሉ ልዩ ድምቀት ከሰጡት ጉዳዮች አንደኛው በቀርቡ ደብራችንን የተቀላቀሉ አዳዲስ ካህናት የቤተክርስቲያንን ትምህርት በተለይም የማኅሌት አገልግሎት ሙያ ያላቸውና ሁለገብ እውቀትን የተላበሱ መሆናቸው ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ምንም እንኳን በእለቱ ከባድ የአየር ቅዝቃዜ የነበረ ቢሆንም የቤተክርስቲያናችን አባላት ምእመናን ብርዱን ሳፈሩና ሳይሳቀቁ የጌታችንን የልደት በረከት ለመካፈል ቤተክርስቲያኗን አጨናንቀው መገኘታቸው ለበአሉ ልዩ ድምቀት ሰጥቶት አምሽቷል። Continue reading የጌታችን እና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደተ በዓል አከባበር በሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ

ልደተ ክርስቶስ

 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አኃዱ አምላክ፤ አሜን።

የሰው ልጅ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ተላልፎ በሐጢያት ከወደቀ በኋላ እግዚአብሔር ወደ ቀደመ ክብሩና ቦታው ይመልሰው ዘንድ በንሰሐ ወደፈጣሪው ቀረበ። አዳም እና ሔዋን ከገነት ከወጡ በኋላ ለአርባ ቀናት ያህል ሱባዔ ገብተው ሳለ በ35 ኛው ቀን ከግማሽ ላይ ቀድሞ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ እንዲያፈርሱ ያደረጋቸው ሰይጣን ዳግመኛ ወደ ሔዋን ቀርቦ ሔዋን ሆይ ጸሎታችሁ ተሰማ አዳምን ይዘሽ ወደዚህ ነይ አላት። Continue reading ልደተ ክርስቶስ

የገብርኤል ንግስ በደብረሰላም

 St. Gabriel Annual Celebration – December 28, 2014