ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ በመምህር ምሕረተአብ አሰፋ
በሚኒያፖሊስ፣ ሴይንት ፖል እና አካባቢው ለምትኖሩ ምዕመናን በሙሉ
በጉባኤው ላይ ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ዳንኤል የድሬደዋና የአካበቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ተገኝተው ቡራኬያቸውን ይሰጡናል ።
በኢትዮጵያ እና በመላው አለም በስባኪ ወንጌልነቱ ታላቅ ዝናና ያተረፈው ወንድማችን መምህር ምሕረተአብ አሰፋ ከፊታችን ኃሙስ ጀምሮ ታላቅ የወንጌል ዘር ሊዘራ ተዘጋጅቷል። ዕለቱም ጥቅምት 26 እና 27, 2008 ሐሙስ እና አርብ ከ400PM ጀምሮ (Nov 5 & 6) ሲሆን ቦታውም በMinnehaha Academy “3100 West River PKWY Minneapolis MN 55406″ ሚኒሶታም በወንጌል ስትናወጽ ታመሻለች – ወንጌል እንዳይሰበክ የሚቅበዘበዘው ዲያቢሎስም ድል ይመታል። ቅድስት እናታችን እመብርሃንም ከፈ ከፍ ትላለች። ታዲያ በዚህን ዕለት እንኳን መቅረት ማርፈድ ያስቆጫል።
ቦታ
Minnehaha Academy
3100 West River PKWY
Minneapolis MN 55406
ከሚኒያፖሊስ
Lake Streetን ይዘው ወደ ሴይንት ፖል ሲጓዙ 46ኛው ጐዳና ላይ ወደ ቀኝ ታጥፈሁ አስከ 32ኛው መንገድ ይሁዱ፤ Minnehaha Academyን 46 እና 32 ላይ ያገኙታል
ከሴይንት ፖል
Lake Streetን ይዘው ወደ ሚኒያፖሊስ ሲጓዙ 46ኛው ጐዳና ላይ ወደ ግራ ታጥፈሁ አስከ 32ኛው መንገድ ይሁዱ፤ Minnehaha Academyን 46 እና 32 ላይ ያገኙታል
ብፅዕ አቡነ አትናቴዎስ እና መምህር ምሕረተአብ አሰፋ ጉዞ ወደ ደብረሰላም መድኃኔዓለም
ብፅዕ አቡነ አትናቴዎስ እና መምህር ምሕረተአብ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ሽኝት ሲደረግላቸው የሚያሳይ ፎቶ ግራፍ
ታላቅ የምስራች“እግዚአብሔር ስለእናንተ ይዋጋል እናንተም ዝም ትላላችሁ።” ዘጸ.14፥14
ሁሉንም ነገር በጊዜው የሚያከናውን የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃዱ ሆኖ አባታችን ብጹእ አቡነ አትናቴዎስ የደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሊባርኩንና ቃለ ምእዳን ሊሰጡን ለሁለተኛ ጊዜ በደብራችን ይገኛሉ። እንዲሁም መምህር ምሕረተአብ አሰፋ በቤተክርስቲያናችን ለመጀመርያ ጊዜ ተገኝተው ሰፊ የወንጌል አገልግሎት ሊሰጡን ከብጹእ አባታችን ጋር ከቅድስት ሃገር ኢትዮጵያ ጉዟቸውን ጀምረዋል።እንደ እግዚአብሔር ፈቃድም ብጹእ አባታችን እና መምህር ምሕረተአብ ማክሰኞ ኦክቶበር 27/2015 ዓ.ም ከምሽቱ 6፡30PM ላይ በቤተክርስቲያናችን ደማቅ አቀባበል የሚደረግላቸው ስለሆነ ይህን መልእክት ያነበባችሁ የሚኒያፖሊስና አካባቢዋ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን ሁላችሁም በደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን በመገኘት ከብጹእ አባታችን በረከትን እንድታገኙ ስንል ይህን አስደሳች ዜና በደስታ እናስተላልፋለን።የመጀመርያ ቀን የወንጌል ትምሕርት መርሐግብርም የፊታችን ሐሙስ ኦክቶበር 29/2015 ዓ.ም ከቀኑ 4፡30PM ጀምሮ በደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢ/ኦ/ተ/ቤ ክርስቲያን በመምህር ምሕረተአብ አሰፋ የሚሰጥ መሆኑን ከወዲሁ እናስውቃለን።“እግዚአብሔር ተዋጊ ነው፤ ስሙም እግዚአብሔር ነው።” ዘጸ 15፥ 3
የነሐሴ ኪዳነምሕረት ምስሎች – 2007 (August Kidanemheret Pictures – 2015)
የደመራ በዓል የፊታችን ቅዳሜ መስከረም 15 (September 26) በደማቅ ሁኔታ ይከበራል።
የአዲስ ዓመት ቅዳሴ – መስከረም ፩ ፳፻፰ (September 12, 2015)
ደብረ ታቦር በደብረሰላም
የኪዳነ ምህረት ንግስ ነሐሴ 16, 2007(August 22, 2015)
የቅዱስ ገብርኤል በዓለ ንግስ – ሐምሌ 19, 2007
የቅዱስ ገብርኤል በዓለ ንግስ እና የ5K ሩጫ/እርምጃ (St. Gebrael Celebration and 5K Run/Walk)
Saturday
7:30 – 11:30 5K Run/Walk
3:00PM – 6:00PM Eve
Sunday
Religious Hymn: 2AM – 7AM
Liturgy: 7AM – 10AM
Psalm, Sermon & Tabote Audet: 10AM – 12PM
በሰሞነ ህማማት ያውም በፀሎተ ኃሙስ ማውገዝ የቤተክርስቲያንን አስተምህሮት የጣሰና ኢቂኖናዊ ነው ተባለ
የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳትሆን በከፍተኛ ደረጃ ኢትዮጵያዊነት የሚንጸባረቅባት የኃይማኖት ተቋም በመሆኗ፣ በዘር፣ በቋንቋ ፣ እንዲሁም በጐጥ ያልተከፋፈለች ስለነበረች በኃይማኖት ሽፋን ለረዥም አመታት አብሮ የኖረን ህዝብ በዕለተ ሆሳዕና ለምን ቀደሳችሁ ብሎ በካህናቱ ላይ በሰሞነ ህማማት ያውም በፀሎተ ኃሙስ በአባ ዘካሪያስ የተላለፈው ውግዘት የቤተክርስቲያንን አስተምህሮት የጣሰና ኢቂኖናዊ መሆኑን መልአከ ምህረት ቆሞስ አባ ምህረት ዘውዴ ፍትሃ ነጋስትን በማጣቀስ እስተምረዋል። በመቀጠልም በሰሞነ ህማማት እንኳን ውግዘት ማውገዝ ይቅርና ይፍቱህ መባል እንኳን በተከለከለበት ጊዜ ያውም በፀሎተ ሀሙስ ለካህናቱ የውግዘት ደብዳቤ መስጠት የቤክርስቲያንን ህግ የጣሰ፣ ታይቶም ሆነ ተሰምቶ የማይታወቅ፣ ወደፊትም የማይታይ መሆኑን ለተሰበሰበው ምዕመናን አስረድተዋል። የምስልና የድምጽ ዝርዝር መልዕክቱን ከቪዲዮው ይመልከቱ
በሰሞነ ህማማት የተላለፈው ውግዘት ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የጣሰ ነው ተባለ
የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትላንትናው ዕለት የቅዱስ ሚካኤልን በዓለ ንግስ ተጋባዥ እንግዳ መልአከ ምህረት ቆሞስ አባ ምህረት ዘውዴ በተገኙበት በደመቀና ባማረ መልኩ ያከበረ ሲሆን፤ በዕለቱም በደብረ ሰላም ካህናት ላይ ለምን በዕለተ ሆሳዕና ቀደሳችሁ ፣ ለምን ህዝበ ክርስቲያኑን አሳልፋችሁ ለተኩላ አልሰጣችሁም በማለት በአባ ዘካርያስ የተላለፈው የሰሞነ ህማማት ውግዘት ኢቀኖናዊ መሆኑን አስተምረዋል።
መልአከ ምህረት ቆሞስ አባ ምህረት ዘውዴ በመቀጠልም በሰሞነ ህማማት እንኳን ውግዘት ማውገዝ ይቅርና ይፍቱህ መባል እንኳን በተከለከለበት ጊዜ ያውም በፀሎተ ሀሙስ ለካህናቱ የውግዘት ደብዳቤ መስጠት የቤክርስቲያንን ህግ የጣሰ መሆኑን ለተሰበሰበው ምዕመናን አስረድተዋል። የምስልና የድምጽ እንዲሁም ዝርዝር ዘገባውን ይዘን እንመለሳለን።
የቤተ ክርስቲያኗ ምዕመናን የመልአከ ምህረት ቆሞስ አባ ምህረት ዘውዴ ስብከት በዲቪዲ ተባዝቶ አንዲቀርብላቸው በጠየቁት መሰረት በትላንትናው ዕለት ማለትም እሁድ ነሐሴ 28 2007 ወይንም July 5, 2015 የመጀመሪያውን ዙር ያከፋፈልን ሲሆን በተከታታይ ሳምንታትም ሁሉም ምዕመን እስኪዳረስ ድረስ አቅርቦቱ የሚቀጥል መሆኑን በታላቅ አክብሮት እንገልፃለን።
የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን
St. Micheal Celebration and Appreciation Day June 20 & 21, 2015
የሚካኤል በዓለ ንግስና የምስጋና ቀን June 20 & 21, 2015
Candlelight Vigil and Prayer Services in State Capitol and DSMA
ባለፈው ኃሙስ በእስቴት ካፒቶል በሊቢያ በሰማዕትነት ላለፉት፣ በደቡብ አፍሪካና በየመን በግፍ ለተገደሉት ወገኖቻችን አስር የእምነት ተቋማት መሪዎች በተገኙበት በሚኒሶታ ውስጥ ለመጀመሪያ ግዜ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያኖች ተገኝተው የጸሎትና የሻማ ማብራት መርኃ ግብር የከወኑ ሲሆኑ ሁሉም የእምነት አባቶች ለህዝባችን አንድነት ለሀገራች ሰላምን ተመኝተዋል። እንዲሁም እሁድ በደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ ክርስቲያን በመቶዎች የሚቆጠሩ የቤ/ ክርስቲያኗ ምዕመናን በተገኙበት ከቅዳሴ በኃላ ፀሎተ ፍትኃት እና የጧፍ ማብራት መርኃ ግብር ተካሒዷል። ፀሎተ ፍትኃቱም እንደተጠናቀቀ በተደረገው የገንዘብ ማሰባሰብ ከ$20,000.00 በላይ ሊሰበሰብ ችሏል። ገንዘቡም በዓለም ዙሪያ በስቃይ ላይ ላሉ ኢትዮጵያዊያኖች መርጃ ይውላል።
Candlelight Vigil and Prayer ልዩ የሻማ ማብራት እና የጸሎት ምሽት በሚኒሶታ – ሐሙስ ኤፕሪል 23, 2015
Please join us for Candlelight Vigil for Ethiopian Martyrs killed in Libya
THURSDAY April 23 , 2015 @ 5PM
የጸሎት አገልግሎት (Prayer Services)
የፀሎተ ፍትኃት መርኃ ግብር በሊቢያ ለተሰውት ሰማዕታት
እሁድ April 26 2015 ከጠዋቱ 5AM – 10 AM በፀሎትና በቅዳሴ
ከ10AM ጀምሮ በፀሎተ ፍትኃት ይታሰባሉ
ወቅታዊ መግለጫ:- የሚኒሶታ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሊቢያ በሚገኙ የእምነታችን ተከታዮች ላይ ራሱን አይ ኤስ እያለ በሚጠራው አሸባሪ ቡድን የተፈጸመባቸውን ዘግናኝ እና አሳዛኝ ግድያ በጽኑ ታወግዛለች። በቀደሙት ዘመናት አባቶቻችን ቅዱሳን ሰማእታት ስለ እምነታቸው ሲሉ፣ ስለ ክረስቶስ ፍቅር ሲሉ፣ ስለ ቤተክርስቲያን ሲሉ በአላውያን ነገሥታት እና አሕዛብ መከራን ተቀብለዋል፣በመጋዝ ተሰንጥቀዋል፣ በእሳት ተቃጥለዋል፣ በፈላ ውኃ ተቀቅለዋል። ደማቸውንም ስለመንግሥተ ሰማያት ሲሉ አፍስሰዋል። ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ
ዳግመ ትንሳኤ
የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢ/ኦ/ተ ቤተ ክርስቲያን ከሆሳዕናና ከመድኃኔዓለም ንግስ ጀምሮ ፣ በሰመነ ህማማት፣ በጸሎተ ሐሙስ፣ በስቅለትና ከትንሳኤው ዋዜማ ጀምሮ በጣም ብዙ ህዝብ በተገኘበት በዓላቱን በደመቀ መልኩ አክብሯል፤ እነሆ አሁንም ዳግመ ትንሳኤን ዘንድሮ ለመጀመሪያ ግዜ ከጠዋቱ 4AM ጀምሮ በማህሌት፣ በቅዳሴና በስብከተ ወንጌል ሊያከብር ስላሰበ እርሶም መጥተው የበረከቱ ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።
Easter 2015 Video (የትንሳኤ አገልግሎት ቪዲዮ)
ድንግል ሆይ በኃጢአት በፍትወት የተጸነስሽ አይደለሽም
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!
እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ “መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው” ብሎ ልበ አምላክ ዳዊት በመዝሙሩ ስለዘመረላት፤ ዳግመኛም ቅዱስ ያሬድ “ማርያምሰ ተኀቱ እምትካት ውስተ ከርሱ ለአዳም ከመ ባሕርይ ጸዓዳ- ማርያምስ ከጥንት ጀምሮ በአዳም ባሕርይ ውስጥ እንደ ነጭ ዕንቁ ታበራለች (በደፈረሰው ዓለም በንጽሕና በቅድስና በድንግልና ታበራለች)” Continue reading ድንግል ሆይ በኃጢአት በፍትወት የተጸነስሽ አይደለሽም