ዜና ቤተክርስቲያን

dsma3rdgubeበታላቁና በአንጋፋው በሚኒሶታ ደብረ ሰላም መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያ 3ኛው ዙር የመጀመሪያው ቀን መንፈሳዊ ጉባዔ ልዩ መንፈሳዊነት በያዘ መልኩ ትላንት በደብሩ ካህናቶች በጸሎት ተከፍቷል። ይህ ለ3 ተከታታይ ቀን የሚቆየው ጉባዔ ላይ ቤተክርስቲያን ካፈራቻቸው የወንጌል ሰባክያን መሀከል ለመናፍቃን በቂ መልስ በመስጠት የሚታወቀው መምህር ምሕረተአብ አሰፋ የወንጌል አገልግሎት ሰጥተዋል። መምህር ምሕረተአብ መቀመጫቸውን በሚኒሶታ ደብረ ሰላም መድኃኒዓለም በማድረግ በተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች በሲያትል፣ በዳላስ ፣ በአትላንታ፣ በዴንቨር  ያደረጉት አገልግሎት በእግዚአብሔር ፈቃድ የተሳካ ሆኗል። በትላንትናው እለት በደብራችን የተጀመረው የሶስተኛውን ዙር ጉባዔ በመምህር ምሕረተአብ የስብከተ ወንጌል እና የዝማሬ አገልግሎት የተሰጠ ሲሆን  በዚህ ጉባዔ ላይ ተጋባዥ እንግዳ የሆኑት  ወንድማችን ጥላሁን (ከዲሲ) ዝማሬውን በክራር በማጀብ ጉባዔውን ልዩ እንዲሆን አድርገውታል። በመጨረሻም ስለ ሀገራችን ኢትዮጵያ ጸሎተ ምህላ ተደርጎ የትላንትናው መርሃ ግብር በጸሎት ተዘግቷል። ይህ ጉባዔ ቅዳሜና እሁድ የሚቀጥል ሲሆን በዚህ አጋጣሚ አገልግሎቱ ላይ ተገኝተሁ የበረከቱ ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን ታቀርባለች።

ክብር እና ምስጋና ለድንግል ማርያም ልጅ ለእርሱ ለሀያሉ አምላካችን ይሁን።