ብፅዕ አቡነ አትናቴዎስ እና መምህር ምሕረተአብ አሰፋ ጉዞ ወደ ደብረሰላም መድኃኔዓለም

AbuneAtnatios ብፅዕ አቡነ አትናቴዎስ እና መምህር ምሕረተአብ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ሽኝት ሲደረግላቸው የሚያሳይ ፎቶ ግራፍ

ታላቅ የምስራች

“እግዚአብሔር ስለእናንተ ይዋጋል እናንተም ዝም ትላላችሁ።” ዘጸ.14፥14

ሁሉንም ነገር በጊዜው የሚያከናውን የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃዱ ሆኖ አባታችን ብጹእ አቡነ አትናቴዎስ የደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሊባርኩንና ቃለ ምእዳን ሊሰጡን ለሁለተኛ ጊዜ በደብራችን ይገኛሉ። እንዲሁም መምህር ምሕረተአብ አሰፋ በቤተክርስቲያናችን ለመጀመርያ ጊዜ ተገኝተው ሰፊ የወንጌል አገልግሎት ሊሰጡን ከብጹእ አባታችን ጋር ከቅድስት ሃገር ኢትዮጵያ ጉዟቸውን ጀምረዋል።
እንደ እግዚአብሔር ፈቃድም ብጹእ አባታችን እና መምህር ምሕረተአብ ማክሰኞ ኦክቶበር 27/2015 ዓ.ም ከምሽቱ 6፡30PM ላይ በቤተክርስቲያናችን ደማቅ አቀባበል የሚደረግላቸው ስለሆነ ይህን መልእክት ያነበባችሁ የሚኒያፖሊስና አካባቢዋ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን ሁላችሁም በደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን በመገኘት ከብጹእ አባታችን በረከትን እንድታገኙ ስንል ይህን አስደሳች ዜና በደስታ እናስተላልፋለን።
የመጀመርያ ቀን የወንጌል ትምሕርት መርሐግብርም የፊታችን ሐሙስ ኦክቶበር 29/2015 ዓ.ም ከቀኑ 4፡30PM ጀምሮ  በደብረሰላም መድኃኔዓለም  የኢ/ኦ/ተ/ቤ ክርስቲያን በመምህር ምሕረተአብ አሰፋ የሚሰጥ መሆኑን ከወዲሁ እናስውቃለን።
“እግዚአብሔር ተዋጊ ነው፤ ስሙም እግዚአብሔር ነው።”  ዘጸ 15፥ 3