እንኳን እግዚአብሔር አምላክ ለዚህ ታላቅ ጾም በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!
ይህንን ጾም በእስር ቤት ላሉት ለታመሙት ለተጨነቁት ወገኖቻችን እግዚአብሔር የቸርነቱን ሥራ ይሰራላቸው ዘንድ በፀሎት ፤በሐሳብ ከእነሱ ጋር እንድንሆን እግዚአብሔር ይርዳን ጾሙንም የኀጢአት መደምሰሻ የዲያብሎስ ድል መንሻ የመንግስተ ሰማያት መውረሻ ያድርግልን።
ዐቢይ የሚለው ቃል ዐብየ ከፍ ከፍ አለ ከሚለዉ የግዕዝ ግስ የወጣ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ታላቅ ማለት ነው፤ ይህንን ጾም አባቶቻችን በተለያየ ስያሜ ጠርተውታል፣ ጌታ እራሱ የጾመው ስለሆነ የጌታ ጾም በመባል ይጠራል በጾሙም ወቅት ሦስቱ የሰይጣን ፈተናዎች ማለትም ትዕቢት፣ ስስት፣ ፍቅረ ነዋይ ድል ተመተውበታል ጾሙም ብዙ መንፈሳዊ በረከት ስለምናገኝበት ጾመ ሁዳዴ በመባልም ይጠራል።
ጾሙ በድምሩ 55 ቀን ይጾማል ጌታ የጾመው 40 ቀን አይደል? ለምን 55 ሆነ ቢሉ Continue reading ዐብይ ጾመ