የጌታችን እና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደተ በዓል አከባበር በሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ

Christmas2015_6የዘንድሮው የ2007 ዓ.ም የልደት በአል በደብራችን ከመቼውም ጊዜ ለየት ባለና በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል። ለበአሉ ልዩ ድምቀት ከሰጡት ጉዳዮች አንደኛው በቀርቡ ደብራችንን የተቀላቀሉ አዳዲስ ካህናት የቤተክርስቲያንን ትምህርት በተለይም የማኅሌት አገልግሎት ሙያ ያላቸውና ሁለገብ እውቀትን የተላበሱ መሆናቸው ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ምንም እንኳን በእለቱ ከባድ የአየር ቅዝቃዜ የነበረ ቢሆንም የቤተክርስቲያናችን አባላት ምእመናን ብርዱን ሳፈሩና ሳይሳቀቁ የጌታችንን የልደት በረከት ለመካፈል ቤተክርስቲያኗን አጨናንቀው መገኘታቸው ለበአሉ ልዩ ድምቀት ሰጥቶት አምሽቷል።

ከሁሉም በላይ ግን ምእመናንን እጅግ ያስደሰተውና ያጽናናው ብጹዕ አቡነ አትናቴዎስ የደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በአሉን አስመልክተው ለደብራችን ምእመናን በቀጥታ የስልክ መልእክት ያስተላለፉት ቡራኬ እና ቃለ ምእዳን ነው። ብጹእነታቸው በሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የሚሰጠው መንፈሳዊ አገልግሎት ፍጹም የሚያስደስትና የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ሕግና ሥርአት የጠበቀ መሆኑንን ገልጸው ባለፉት ጊዚያት ቤተክርስቲያኑ የሚሰጠውን መንፈሳዊ አገልግሎት አስመልክቶ ብጹእ አቡነ ዘካርያስ የኒዎዮርክና አካባቢው ሊቀጳጳስ የሰጡት አስተያየትም ሆነ የውግዘት ቃል ፈጽሞ የተሳሳተና ተቀባይነት የሌለው በቂምና በኃይለኝነት የተደረገ እንደሆነ ገልጽዋል።

ይህን አስመልክቶም የቤተክርስቲያኗ ሕግ የማይቀበለው መሆኑን በቀጥታ ከቤተክርስቲያኗ የሕግጋት ምንጭ ከሆነው ከፍትህ መንፈሳዊ አንቀጽና ቁጥር ጠቅሰው በማንበብ በብጹእ አቡነ ዘካርያስ የተደረገው ሁሉ ከሕግ የወጣ ድርጊት መሆኑን አስረድተዋል። የደብራችን ምእመናንም በእምነታቸው እንዲጸኑና ምንም መሸበር እንዳያገኛቸው ብጹእነታቸው የማጽናናት ምክር ሰጥተዋል። በቅርቡም ወደ ደብራችን በመምጣት ምመናንን ለመጎብኘት እያሰቡ እንደሆነም ገልጸዋል። እናንተ ለቤተክርስቲያን አንድነትና ሰላም የቆማችሁ ስለሆነ በዚህ አቋማችሁ ልትወቀሱ አይገባችሁም ብለዋል። ብጹእ አቡነ አትናቴዎስ ለምእመናን በቀጥታ በማንበብ ያስተላለፉት የፍትህ መንፈሳዊ ሕግ ክፍልም እንደሚከተለው ይነበባል። ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 5 ቁ. 182-184

FetheMenfesaw