All posts by Admin

የጌታችን እና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደተ በዓል አከባበር በሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ

Christmas2015_6የዘንድሮው የ2007 ዓ.ም የልደት በአል በደብራችን ከመቼውም ጊዜ ለየት ባለና በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል። ለበአሉ ልዩ ድምቀት ከሰጡት ጉዳዮች አንደኛው በቀርቡ ደብራችንን የተቀላቀሉ አዳዲስ ካህናት የቤተክርስቲያንን ትምህርት በተለይም የማኅሌት አገልግሎት ሙያ ያላቸውና ሁለገብ እውቀትን የተላበሱ መሆናቸው ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ምንም እንኳን በእለቱ ከባድ የአየር ቅዝቃዜ የነበረ ቢሆንም የቤተክርስቲያናችን አባላት ምእመናን ብርዱን ሳፈሩና ሳይሳቀቁ የጌታችንን የልደት በረከት ለመካፈል ቤተክርስቲያኗን አጨናንቀው መገኘታቸው ለበአሉ ልዩ ድምቀት ሰጥቶት አምሽቷል። Continue reading የጌታችን እና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደተ በዓል አከባበር በሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ