All posts by Admin

ትላንትና እና ዛሬ!

ምስጋና ለነሱ ለጠንሳሾቹ
ለአባቶች ለእናቶች ለተላሚዎቹ
ደብረሰላምን መስራቾቹ ።
በአገልግሎት የተባረከዉ
በወገን ብዛት የታደለው
ምስጋና አዲሱን ለሚያንፀው።
የጀመሩትን እያሥታወሥን
ልፋታቸውን እየመረቅን
አገልግሎታቸዉን በፀጋ ተቀብለን
ለተተኪው እንሠራለን።
የሕንፃው ጅማሮ እያሽቀበ
ከእለት እለት ደሥታን እየካበ።
መሠረቱ ነው ለደብረ ሠላም
ተደጋግፎ መተለም
ልጆቻችንን ለማሥቀደም።
ክብር ለጌታ ለታደገን
በሥራችን ሁሉ ለባረከን
ልጆቻችንን ላበዛልን
የወደፊቱን ለሚረከቡን።
የወገን አደራን እናከብራለን
ለመድሐኒ ዓለም ቃል እንገባለን
ልጆቻችንም እንዳያፍሩብን።
መልካሙ ጅማሮ እንዲቀጥል
ትምህርቱ በጥራት እንዲገለገል።
ተማሪዎቹ ተመራቂዎቹ ሁሉም በያሉበት
መጪውን ዘመን እሚያስቡት
ለትምህርት ለሥራ ለሚዘጋጁት
ያባቶች ፀሎት ይጨመርበት።

Pictures were taken in 2002 (left) and August 2025 (Right)

ወሥበሃት ለእግዚአብሔር
ከሕንፃ ኮሚቴ የህዝብ ግንኙነት ክፍል

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net