Building Committee

Building Coordinating Committee By-law

እናስተዋውቃችሁ

የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የህንጻ ግንባታ ኮሚቴ

ኮሚቴው የቤተክርስቲያኑ አባላት በሆኑ ፈቃደኛ ግላሰቦች የተደራጀ ሲሆን 28 የሚሆኑ አባላትን አቅፏል።
ዓላማው:  አዲሱን የደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ህንጻ አሰርቶ ማስረከብ ነው።
ኮሚቴው ከተዋቀረበት ጉዜ አንስቶ ብዙ ነገሮችን የልዑል እግዚአብሄር ፈቃድ ታክሎበት አክናውሏል።
በመጀመሪያ የመተዳደረያ ደንብ አርቅቆ ተወያይቶበትና ተከራከሮበት ለቤተክርስቲያኑ የአስተዳደር ቦርድ አቅርቦ ካጸደቀ በኋላ በደንቡ መሠረት እራሱን አደራጀቶ ሥራዉን ጀምሯል።
መዋቅሩ: 7 አባላት ያሉት የሥራ አስፈፃሚ (Executive Committee) እና 4 ንዑሳን ኮሚቴዎችን  የያዘ ነዉ።  ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ።

 

Based on the mission for BCC and Medhane Alem, here’s a breakdown of our plan to raise funds for the construction of a new church building.

Mission Summary:
Goal: Strengthen bonds between BCC (a committee concept) and Medhane Alem (a congregation).
Action: Form an alliance and engage with the Twin Cities population through volunteering.
Purpose: Raise funds for a new building.
The First Step in the fundraising effort was to launch the initial fundraising phase by volunteering at concession stands at the Target Field, Minneapolis, Minnesota (see photo below)

ትላንትና እና ዛሬ!

ምስጋና ለነሱ ለጠንሳሾቹ
ለአባቶች ለእናቶች ለተላሚዎቹ
ደብረሰላምን መስራቾቹ ።
በአገልግሎት የተባረከዉ
በወገን ብዛት የታደለው
ምስጋና አዲሱን ለሚያንፀው።
የጀመሩትን እያሥታወሥን
ልፋታቸውን እየመረቅን
አገልግሎታቸዉን በፀጋ ተቀብለን
ለተተኪው እንሠራለን።
የሕንፃው ጅማሮ እያሽቀበ
ከእለት እለት ደሥታን እየካበ።
መሠረቱ ነው ለደብረ ሠላም
ተደጋግፎ መተለም
ልጆቻችንን ለማሥቀደም።
ክብር ለጌታ ለታደገን
በሥራችን ሁሉ ለባረከን
ልጆቻችንን ላበዛልን
የወደፊቱን ለሚረከቡን።
የወገን አደራን እናከብራለን
ለመድሐኒ ዓለም ቃል እንገባለን
ልጆቻችንም እንዳያፍሩብን።
መልካሙ ጅማሮ እንዲቀጥል
ትምህርቱ በጥራት እንዲገለገል።
ተማሪዎቹ ተመራቂዎቹ ሁሉም በያሉበት
መጪውን ዘመን እሚያስቡት
ለትምህርት ለሥራ ለሚዘጋጁት
ያባቶች ፀሎት ይጨመርበት።

ወሥበሃት ለእግዚአብሔር
ከሕንፃ ኮሚቴ የህዝብ ግንኙነት ክፍል

ከህንፃ ኮሚቴ ለበጎ ፈቃደኞች የበአል ምስጋና (October 5, 2025)

የህንፃ ኮሚቴ በጎ ፈቃደኞች
የሁላችንም ተገኖች

ይድረሳችሁ ውዳሴ ሰላምታ
ለልፋታችሁ ጠዋት እና ማታ

የቡድን መሪ ምሳሌዎች
ሰርታችሁ የምታሰሩ መሪዎች

ብርዱ ፀሀዩ ሳይበግራችሁ
ለአመታት የለፋችሁ
ድርሻሁን የተወጣችሁ

ባለመሰልቸት በትጋት
ከጅምሩ ጀምሮ ለተሳተፉት
ነፃ አገልግሎት ላበረከቱት
ይድረሳቸው ምስጋናችን በየአሉበት

ቃል ኪዳኑን ስንገባ ስንወጥን
የውዴታ ግዴታ ስለአለብን
አንዘናጋ መሳተፍን
ያጠንክርልን ያበርታልን
ሌሎችንም በተራ ያሳትፍልን
የህብረቱን ውጤት ያጎናፅፈን

ከዘመን ዘመን ላሸጋገረን
በአለ መስቀሉን ለታደገን
ለተግባራችሁ ጌታ ይባርክልን::

ወስብሃት ለእግዚአብሄር::
ከሕንፃ ኮሚቴ የህዝብ ግንኙነት ክፍል!

Screenshot
Screenshot