ደመራ 2010 (Demera 2017)

የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የ2010 ዓ. ም. (2017) የደመራ በዓልን በደመቀ ሁኔታ መስከረም ፲፫, ፳፻፲ (September 23, 2017) በ2629 30th Ave South Minneapolis MN 55406 ስለሚያከብር ከቤተሰብ፣ ከዘመድ እና ከወዳጅ ጋር በመምጣት የበረከቱ ተካፊይ እንዲሆኑ ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

በእለቱም ለልጆችዎ መጫወቻ ያዘጋጀን ስለሆነ ከ12PM ጀምሮ መጥተው ልጆችዎን ያጫውቱ።

የመኪና ማቆሚያ የተንጣለለ የ2.7 Acre ቦታ ስላለን ማቆሚያ ቦታ አጥቼ እቸገራለሁ ብለው ኃሳብ እይግባዎት፣ እንደ በፊቱ ሩቅ አቁሞ የጐልፍ ሜዳ አቋረጡ ብሎ የሚወቅስዎ የለምና ዘና ብለው መኪናዎትን ያቆሙ ዘንድ የሚረዱዎት መዕመናን አዘጋጅተን እንጠብቆታለን።

ወስበሃት ለእግዚአብሔር