በአብይ ጾም ውስጥ ያሉ ሳምንታት ስያሜ

የተከበራችሁ የቤተክርስትያናችን አባላት እና ቤተሰቦች በሙሉ፤
እንኳን ለ2016 ዐብይ ጾም አደረሰን!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለጾም ሥርዓት እና ደንብ አውጥታ በዓመት ውስጥ ሰባት የአዋጅ አጽዋማት እንዳሉና ማንኛውም ክርስቲያን እነኝህን አጽዋማት እንዲጾሙ ታዛለች። ከነዚህም አንዱ እና ታላቁ ጾም ዛሬ ሰኞ መጋቢት 2/2016 (March 11, 2024) የጀመርነው የአብይ ጾም ነው:: ለዚህም ቤተክርስቲያናችን እንኳን አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቷን ትገልጻለች።

ዐቢይ ጾም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለእኛ የጾመው ጾም እና ለእኛ አራያ የሆነበት ጾም ነው። እኛም እንድንጾማቸው በቤተ ክርስቲያናችን ከታዘዝናቸው ሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት አንዱ ነው። እኛ ምእመናን ጌታችን ያደረገውን ምሳሌ ተከትለን ጾሙን በየዓመቱ እንጾመዋለን። ዐቢይ ጾም ስምንት ሳምንታት (፶፭ ቀኖች) ሲኖሩት በውስጡ ስምንት ቅዳሜዎች፣ ሰባት እሑዶች ይገኛሉ።እነዚህም ዐሥራ አምስት ቀናት ሲሆኑ በእነዚህ ቀናት ከጥሉላት እንጂ ከእህል ውኃ ስለማይጦሙ እነዚህ ቀናት ሲቀነሱ የጦሙ ወራት ዐርባ ቀን ብቻ ይሆናል።

ዓብይ ጾም የተባለበት ምክንያት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው ስለሆነና ታላላቅ የሰይጣን ፈተናዎችን ድል የተነሱበት በመሆኑ ዛሬም ክርስቲያኖች የአምላካችንን አርአያ ተከትለን ሰይጣንን ድል የምንነሳበት ጾም ስለሆነ ነው።

የዐብይ ጾም በተለያዩ ስሞችም ይጠራል

  • ሁዳዴ ጾም ይባላል። ይህም የመንግሥት እርሻ ወይም ማንኛውም የሕዝብ ብዛት ያለበት ሥፍራ ሁዳድ ይባላል። በመሆኑም ዐቢይ ጾምም ከአጽዋማት ሁሉ ብዙ ቀናት ስለሚጾምና ክርስቲያኖች የሆኑ ምዕመናን ሁሉ ስለሚጾሙት የሁዳዴ ጾም ተባለ።
  • ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው ፵ ቀን ስለሆነ ጾመ ዐርባ ም ይባላል /ማቴ.፬፥፩/

በአብይ ጾም ውስጥ ያሉ ሳምንታት ስያሜ

  • ዘወረደ
  • ቅድስት
  • ምኵራብ
  • መጻጕዕ
  • ደብረዘይት
  • ገብርኄር
  • ኒቆዲሞስ
  • ሆሳዕና
  • ትንሳኤ ናቸው ::

የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በአብይ ጾም ያላት የአገልግሎት መርኃ ግብር

  • ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋቱ 6 ኤ.ኤም እስከ 10 ኤ.ኤም የኪዳን ፀሎት አገልግሎት ይሰጣል።
  • ዘወትር ቅዳሜ ከጠዋቱ 6 ኤ.ኤም እስከ 8 ኤ.ኤም የኪዳን ፀሎት ይደርሳል።
  • ዘወትር እሁድ ከንጋቱ 3 ኤ.ኤም ጀምሮ የፀሎት፣ የክርስትና፣ የቅዳሴ አገልግሎቶች ይሰጣል::

ከዘመድ እና ከወዳጅ ጋር በመምጣት የበረከቱ ተካፊይ እንዲሆኑ የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የአገልግሎት ቀን መቁጠሪያ ::

  • የዓብይ ጾም (የሁዳዴ ጾም) :- ከመጋቢት 2 አስከ ሚያዝያ 27 (Monday March 11, 2024 – Sunday May 5, 2024)
  • መጋቢት መድሐኔዓለም :- በዓለ ንግሱ መርኃ ግብር የሚከናወንበት ትክክለኛ ቀን : መጋቢት 29, 2016 (Sunday Apr. 7, 2024) / Megabit Medhanealem / The original Crucifixion.
  • ደብረ ዘይት :- መጋቢት 29, 2016 (Sunday April 7, 2024) / Debrezeit
  • ሀሳዕና :- ሚያዝያ 20, 2016 (Sunday April 28, 2024) / Hosanna
  • ሰሙነ ሕማማት :- ሚያዝያ 21, 2016 እስከ ሚያዝያ 26, 2016 (Monday April 29, 2024 to Friday May 3, 2024) / Holy/Passion week.
  • ጸሎተ ሐሙስ :- ሚያዝያ 25, 2016 (Thursday May 2, 2024) / Maundy Thursday
  • ስቅለት :- ሚያዝያ 26, 2016 (Friday May 3, 2024) / Good Friday (Crucifixion)
  • ትንሣኤ :- ሚያዝያ 27, 2016 (Sunday May 5, 2024) / Easter Sunday

በዚህ አብይ ጾም ሁላችም ስለሀገራችን እና ስለ ቅድስት ቤተክርስትያናችን አብዝተን የምንጸልይበት እኛም በረከት የምናገኝበት በስጋ ወደሙ የምንከብርበት ያድርግልን::

ጽሁፉን ያዘጋጀችው ወይዘሮ ሐና ስዩም ነች::

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/

የየካቲት ኪዳነምሕረትን የዋዜማ አገልግሎት እና በዓለ ንግስ በሚኒሶታ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ያክብሩ!

በሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን እንኳን ለየካቲት ኪዳነምሕረት በዓለ ንግስ በስላም አደረሳችሁ እያለች፣ የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 16, 2016 ከቀኑ 4:00ፒ.ኤም. ጀምሮ (Saturday Feb. 24, 2024 from 4:00 pm) በዋዜማ፣ ቀጥሎም እሁድ የካቲት 17, 2016 ከ2:00 ኤ.ኤም. ጀምሮ (Sunday Feb. 25, 2024 from 2:00 am) በማህሌት የየካቲት ኪዳነምሕረትን በዓለ ንግስ በደመቀ ሁኔታ ታከብራለች:: በእለቱም ከቤተሰብ፣ ከዘመድ እና ከወዳጅ ጋር በመምጣት የበረከቱ ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ ቤተክርስቲያናችን ጥሪዋን ታቀርባለች::

መቼ? / When?
የዋዜማ አገልግሎት፣
ቅዳሜ የካቲት 16, 2016 ከ4:00 ፒ.ኤም. ጀምሮ (Saturday Feb. 24, 2024 from 4:00 pm)
በዓለ ንግስ
እሁድ የካቲት 17, 2016 ከ2:00 ኤ.ኤም. ጀምሮ (Sunday Feb. 25, 2024 from 2:00 am)

ፎቶግራፉ የሚያሳየዉ በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የቤዛ ኩሉ የሰንበት ት/ቤት ታዳጊና ወጣቶች በዚህ አመት የጥምቀት በአል አከባበር መርኃግብር ላይ ነዉ::

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net

በፌስቡክ እንዲከተሉን ይህን ይጫኑ

Click Here to Follow Us On Facebook

የስባተኛው አመት የበጎፈቃደኝነት የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ በሰላም ተጠናቀቀ!

የተከበራችሁ የቤተክርስትያናችን አባላት እና ቤተሰቦች በሙሉ፤

እንደወትሮው ሁሉ የሚኒሶታ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አባላት እና ቤተሰቦቻቸው አዲስ የቤተክርስቲያን ሕንፃ ለመገንባት የሚያስፈልገውን የገንዘብ ወጪ በከፊል ለመሸፈን ያስችል ዘንድ ከኪሳችን ከምናዋጣው በተጨማሪ በ2023 ዓ.ም. የበጎፈቃደኝነት የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ላይ በዩኤስ ባንክ ስታዲየም እና በሚኔሶታ ስቴት ፌር ተስማርተን ነበር :: እንደምታስታውሱት ሁሉ የመጨረሻው የበጎአድራጎት የስራ ቀን የተጠናቀቀው ያለፈዉ ወር እሁድ December 31, 2023 በዩኤስ ባንክ ስታዲየም ውስጥ በተደረገው የቫይኪንግ እና የግሪን ቤይ ፓከርስ ቡድኖች ጨዋታ ቀን ነበር:: ይህን የስራ ዘርፍ ከጀመርን እነሆ ሰባት አመታትን አአስቆጥረናል! ስለሆነም ባለፈው አመት ውስጥ ስለተከናወኑት የበጎአአድራጎት ስራዎች እና ስለተስበስበው የገንዘብ መጠን ለግንዛቤ ይረዳል ተብሎ በበጎአድራጎት ስራ አስተባባሪዎቹ በኩል የተዘጋጀ አጭር ሪፖርት ከዚህ በታች ባለው መልኩ ቀርቧል::

በ2023 ዓ.ም. ስንት የበጎፈቃድ አገልግሎት ሰራ ቀኖች ነበሩ?

በአመቱ በጠቅላላው 27 የበጎፈቃድ አገልግሎት ሰራ ቀኖች ነበሩ:: እነሱም 11 የቫይኪንግ ጨዋታዎች  ፣ 10 በሚኒሶታ ስቴት ፌር የመክና ማቆሚያ ማስተናገድ ስራ እና 6 በዩእስ ባንክ ስታዲየም በተደረጉ የሙዚቃ ኮንስርቶች እና ሞንስተር ጃም ትእይንቶች ነበሩ:: በ2023 በተደረጉት ስራዎች አንድ የበጎአድራጎት የስራ ቀን በአማካይ ከ 7 እስክ 9 ሰአቶች ይፈጅ ነበር::

በ2023 ዓ.ም. የበጎፈቃድ አገልግሎት ሰራ ላይ ስንት አባላት ቤተስቦችና ወዳጆች ነበሩ?

በዚህ አመት በጠቅላላው 111 የደብራችን አባላት ቤተስቦችና ወዳጆች በበጎአድራጎት ሰራ ላይ ተስማርተው ነበር:: ከ 7-14 ቀኖች የስሩ 10 እባላት  ፣ ከ4-5 ቀኖች የሰሩ ሌሎች 10 እባላት  ፣ ከ 2-3 ቀኖች የስሩ 36 አ ባላት  ፣ እንዲሁም አንድ ቀን ብቻ የስሩ 55 አባላት ነበሩ::

የስሩበት ቀኖች ብዛት የስሩ አባላት ብዛት%
7 – 14109%
4 – 5109%
2 – 3 3632%
15550%
ጠቅላላ 111100%

በ2023 ዓ.ም. የበጎፈቃድ አገልግሎት ሰራ ላይ እነማን ነበሩ?

በ2023ዓ.ም በተደረገው የበጎአድራጎት ስራ ወቅት ከ4 እስከ 14 ቀኖች ያገለገሉ 20 አባላት ስም ዝርዝር እና የስሩባቸው ቀኖች ብዛት በሚከተለው ሰንጠረዥ ላይ ተቀምጧል:: በዚህ አመት ብቻ 14 የበጎአድራጎት የስራ ቀኖችን በመስራት ከፍተኛውን ደረጃ የወሰደው የፕሮግራሙ አስተባባሪ ዶ/ር አሻርግሬ አትሬ ነው::

አባል ስም የስሩበት ቀኖች ብዛት
ዶ/ር አሻግሬ አትሬ14
ወ/ሮ በስልፍዋ መንገሻ11
ወ/ሮ አባይነሽ ደበላ10
ዶ/ር ብርሀኑ በለጠ10
አቶ ዳንኤል ከህሉ9
ዶ/ር መስፍን ተስፋዬ ገባያው9
አቶ አለምሰገድ ተስፋዬ8
አቶ እሸቱ ባዱንጋ8
አቶ ኤልያስ ጥላሁን7
አቶ ግርማ መኮንን7
አቶ አማረ በርሄ5
አቶ አሸናፊ ቡልቶ5
አቶ ፀጋ በዛብህ5
አቶ አበራ በርጃ4
አቶ ደረጀ አለሙ4
አቶ ደረስ ገ /ጊዬርጊስ4
ወ/ሮ እጅጋየሁ ይርጉ4
አቶ ገዛኸኝ ዳምጤ4
ወ/ሮ ራሄል ባልቻ4
ወ/ሮ ትእግስት መለሴ4

በ2021ዓ.ም. ፣ በ2022 ዓ.ም.  እንዲሁም በ2023 ዓ.ም. የበጎአድራጎት ስራ የስሩትን አባላት ስም ዝርዝር እና የስሩባቸውን ቀኖች ብዛት ለማየት የሚከተለዉን ሊንክ ይጫኑ! https://mesfinbcc.pythonanywhere.com/

በ2023 ዓ.ም. የበጎአድራጎት ስራ ምን ያህል ገንዘብ ተስበስበ?

በዚህ 2023 ዓ.ም. በበጎአድራጎት ስራ ለቤተክርስቲያን ማስሪያ የተስበስበው $56,166 ነበር :: በዚህ አመት በበጎአድራጎት ስራ ያስገባነው የገንዘብ መጠን ካለፉት ሁለት አመታት ስርተን ካገኘነው ጋር ሲነጻጸር እጅግ ያንሳል:: ክዚህ በታች ያለው ግራፍ እንደሚያሳየው በ2022 ዓ.ም. $199,950 እና በ2021 ዓ.ም. $223,558 አስባስበን ነበር::

በሰባት አመታት የበጎአድራጎት ስራ ለቤተክርስቲያን ማስሪያ የተስበስበው ጠቅላላ የገንዘብ መጠን ስንት ደረስ?

እስከአሁን ድረስ ለቤተክርስቲያን ማስሪያ በበጎአድራጎት ስራ የተስበስበው ጠቅላላ የገንዘብ መጠን $811,312 ነው:: ዝርዝሩ ከዚህ በታች ተቀምጧል::

እንደምታዉቁት ሁሉ ትልቁ ጉልበታችንና እቅማችን በሁሉም መስክ የተጠናከረ እና የተሳተፈ የአባላት ጥንካሬ ሲኖረን ነው:: ስለዚህም 2024ዓ.ም. ሁላችንም በምንችለው እውቀት ጊዜ ጉልበት እና ገንዘብ በመረባረብና በመደጋገፍ አዲሱን ቤተክርስትያን አስርተን ለመገኘት ያበቃን ዘንድ እንትጋ: : በዚህ አጋጣሚ ሁላችሁም እከአሁን እና ወደፊትም ለምታደርጉት ትብብርና እርዳታ ሁሉ በረከቱ ይብዛላችሁ::

በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን
January 30, 2024
Minneapolis, Minnesota, U.S.A.

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/

የዘንድሮው የከተራ እና ጥምቀት በዓል አከባበር እና የሃያ ሰባት አመቱ ቤዛኩሉ

በዚህ አመት የከተራ እና ጥምቀት በዓላት  ቅዳሜ ጥር 11, 2016 (Saturday Jan 20, 2016) እና እሁድ ጥር 12, 2016 (Sunday Jan 21, 2016) Bloomington Road, Fort Snelling, St. Paul, MN 55111 በሚገኘው ቦታ እንደወትሮው በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል:: የዘንድሮውን የጥምቀት በአል አከባበር ደማቅ እና ልዩ ያደረገው ነገር ቢኖር የሀገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ለመጀመሪያ ጊዜ በመሀከላችን ተገኝተው ቡራኬ መስጠታቸው እንዲሁም የቤዛ ኩሉ የሰንበት ት/ቤት ታዳጊና ወጣቶች በብዛት ሆኖ በመሳተፍና ያቀረቧቸው ልዩ ልዩ መዝሙራት እና ሌሎች መንፈሳዊ ዝግጅቶች በልዩ ሁኔታ የሚጠቀሱ ናቸው ::

በተለያዩ ምክንያቶች የበዓሉን አከባበር መርኃግብር በቦታው በመገኘት የበረከቱ ተሳታፊ ለመሆን ላልቻላችሁ ሁሉ ይጠቅማል በማለት የቤዛ ኩሉ ሰንበት ት/ቤት ታዳጊና ወጣቶች የሚዲያ ዝግጅት ክፍል ያካፈለንን ፎቶግራፎች ከዚህ በታች አቅርበናል::

የደብራችንን ታላቅነት ባገናዘበ መልኩ የቤዛ ኩሉ የሰንበት ት/ቤት ታዳጊና ወጣቶችም ላቀረቧቸው መዝሙራት ፣ ልዩ መንፈሳዊ እና ትምህርታዊ ዝግጅቶች በተጨማሪም ላሳያችሁት መልካም አርአያዊነት ተግባር እያመሰገንን የደከማችሁበት ሁሉ ስለተሳካላችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ እንላለን:: በዚህ አጋጣሚም  በደብራችን ውስጥ ለሚከናወኑት የሰንበ ት/ቤትና የልጆች ፕሮግራም ተሳታፊዎች: ካህናት: ፕሮግራም መሪዎች: አስተማሪዎች እና ወላጆች ሁሉ እንኳን ደስ ያላችሁ እንላለን። በተጨማሪም የቤዛ ኩሉ የሰንበት ት/ቤት ታዳጊና ወጣቶች የሚዲያ ዝግጅት ክፍልን ለፎቶግራፎቹ እጅግ በጣም እናመሰግናለን::

በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን
January 24, 2024
Minneapolis, Minnesota, U.S.A.

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/

እንኳን ለ2016 ዓ.ም. ከተራ እና ለብርሀነ ጥምቀቱ በስላም አደረሳችሁ!

እንኳን ለ2016 ዓ.ም. ከተራ እና ለብርሀነ ጥምቀቱ በስላም አደረሳችሁ እያለች የፊታችን ቅዳሜ ጥር 11, 2016 (Saturday Jan 20, 2016) ከቀኑ 3 ፒኤም ጀምሮ የከተራ ጉዞ ወደ 6202 Bloomington Road, Fort Snelling, St. Paul, MN 55111 ይደረጋል:: ቀጥሎም እሁድ ጥር 12, 2016 (Sunday Jan 21, 2016) ከቀኑ 1 ኤኤም ጀምሮ በማህሌት: ከቀኑ 5 ኤኤም በቅዳሴ እና ቀጥሎም በታቦት ሽኝት የብርሀነ ጥምቀት በአልን በደመቀ ሁኔታ ቤተክርስቲያናችን ታከብራለች::

በእለቶቹም ከቤተሰብ፣ ከዘመድ እና ከወዳጅ ጋር በመምጣት የበረከቱ ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

የጥምቀት በአል የሚከበርበት አድራሻ: 6202 Bloomington Road, Fort Snelling, St. Paul, MN 55111
ስለ ከተራ እና ጥምቀት አከባበር መርኃ ግብር የሚከተለዉን ይመልከቱ!

የጥምቀት ጾም (የጋድ ጾም) :- ጥር 10, 2016 (Friday Jan 19, 2024)
ከተራ :- ጥር 11, 2016 (Saturday Jan 20, 2016)
ጥምቀት :- ጥር 12, 2016 (Sunday Jan 21, 2016) / The Baptism of Christ (Epiphany).

በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የአስተዳደር ቦርድ
January 14, 2024
Minneapolis, Minnesota, U.S.A.

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/

እንኳን ለብርሀነ ልደቱ በስላም አደረሳችሁ!

በሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን እንኳን ለብርሀነ ልደቱ በስላም አደረሳችሁ እያለች የፊታችን ቅዳሜ ታህሳስ 27, 2016 (Saturday January 6, 2024) ከቀኑ 5 ፒኤም ጀምሮ በማህሌት: ቀጥሎም ከምሽቱ 11 ፒኤም ጀምሮ በቅዳሴ የእየሱሰ ክርስቶስን የልደት በአል በደመቀ ሁኔታ ታከብራለች:: በእለቱም ከቤተሰብ፣ ከዘመድ እና ከወዳጅ ጋር በመምጣት የበረከቱ ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ ቤተክርስቲያናችን ጥሪዋን ታቀርባለች::

መቼ: ቅዳሜ ታህሳስ 27, 2016 ከ 5 ፒኤም ጀምሮ
When: Saturday January 6, 2014 from 5pm

ከዚህ በታች ያሉት ፎቶግራፎች የሚያሳዩት የቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች የ2016 ዓ.ም. የእየሱሰ ክርስቶስ የልደት በአልን በደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያናችን ውስጥ ሲያከብሩ ነዉ::

የቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት በሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ውስጥ ከተመሰረተ 27 አመት አስቆጥሯል::

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/

ጾመ ነቢያት (የገና ጾም): ቅዳሜ ኅዳር 15 ለሚጀመረው እና በረከት ለምናገኝበት ጾመ ነቢያት እንኳን አደረሰን!

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

የተከበራችሁ የቤተክርስትያናችን አባላት እና ቤተሰቦች በሙሉ፤
እንኳን ለጾመ ነቢያት (የገና ጾም) በሠላም አደረሳችሁ።

የኢትዮያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰባት የአዋጅ አጽዋማት ያሏት ሲሆን ከእነዚህ የአዋጅ አጽዋማት መካከል አንዱ የነቢያት ጾም ነው። ጾሙን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ ከመገለጡና ሰው ከመሆኑ በፊት ነቢያት የጌታን መምጣት በናፍቆት በጾምና በጸሎት ሲጠባበቁ ነበር። ስለዚህ የነቢያትን የጾም ድካም ለማሰብና እንደ ነቢያት መንፈስ ኃይልን ለመልበስ በእምነት ለመጽናት ኃጢአትን ለመዋጋት ሲባል ይህን ጾም እኛ እንጾመዋለን።

ይህንን ጾም በተመለከተ በፍትሐ ነገሥት (ፍትሕ መንፈሳዊ) አንቀጽ ፲፭፥፭፻፷፬ ጀምሮ ተጽፏል። በፍትሕ መንፈሳዊ በአንቀጽ ፲፭፥፭፻፷፰ ላይ እንደተገለጸው ከኅዳር እኩሌታ እስከ ልደት የሚጾመው ጾም ነው።
“መጀመርያው የኅዳር እኩሌታ፡ ፋሲካው፡ የልደት በዓል ነው።” ተብሎ የጾመ ነቢያት መነሻውና መድረሻውን ፍትሐ ነገስት ላይ ተገልጿል። ይህም ማለት በሦስቱ ወንጌላውያን ማለትም በዘመነ ማቴዎስ፣ በዘመነ ማርቆስና በዘመነ ሉቃስ የገና ጾም ከኅዳር ፲፭ ጀምሮ  በኅዳር ፳፱ ይፈሰካል። በዚህ በያዝነዉ በዘመነ ዮሐንስ ደግሞ የገና ጾም ቅዳሜ ኅዳር ፲፭  ተጀምሮ እሁድ ኅዳር ፳፰
ይፈሰካል።

ጾሙን የበረከት ያድርግልን!

ጾመ ነቢያት (የገና ጾም) :-
ከህዳር 15,2016 አስከ ታህሳስ 28, 2016
(Saturday Nov 25, 2023 – Sunday Jan 7, 2024)

ጽሁፉን ያዘጋጀችው ወይዘሮ ሐና ስዩም ነች::

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/

የኅዳር ሚካኤልን በዓለ ንግስ በሚኒሶታ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ያክብሩ!

የኅዳር ሚካኤል በዓለ ንግስ እሁድ ህዳር 9, 2016 በሚኒሶታ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በደመቀ ሁኔታ ይከበራል:: መጥተው የበረከቱ ተካፋይ እንዲሆኑ ቤተክርስቲያናችን ጥሪዋን ታስተላልፋለች::

መቼ? / When?
እሁድ ህዳር 9, 2016 ከ2:00 ኤ.ኤም. ጀምሮ
Sunday Nov. 19, 2023 from 2:00 am

በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የአስተዳደር ቦርድ

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406 ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
Website: https://www.debreselam.net

በፌስቡክ እንዲከተሉን ይህን ይጫኑ / Click Here to Follow Us On Facebook

የ2016 የአመታዊ፣ የንግሥ በዓላት እና የአጿማት ቀን መቁጠሪያ በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን

የተከበራችሁ የቤተክርስትያናችን አባላት እና ቤተሰቦች በሙሉ፤
የ2016 አ.ም. ከገባ የመጀመሪያውን ወር አገባድደናል:: አዲስ አመት እንደመሆኑም የአመታዊ፣ የንግሥ በዓላት እና የአጿማት ቀን አቆጣጠሩ ላይ ብዙ ማወቅ የምትፈልጉት እንዳሉ እንገነዘባለን:: ለምሳሌም ያህል የጾም ቀኖች እና ወራቶች የትኞቹ ናቸዉ? የአመታዊ እና የንግሥ በዓላት የሚዉሉባቸዉ ቀኖችስ የትኞቹ ናቸዉ? በዩኤስ ባንክ ስታዲየም ለአዲስ ቤተክርስቲያን ማሰሪያ የሚውል የበጎፈቃደኝነት የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ቀኖች እና ወራቶችስ የትኞቹ ናቸዉ? የቤዛ ኩሉ ስንበት ት/ቤት የህጻናት ታዳጊዎችና ወጣቶች አገልግሎት መርኃ ግብሮች መቼ መቼ ሊውሉ እንደሚችሉ እቅድ እና ፕሮግራም ወጥቶላቸዋል? ይህ
የቀን መቁጠሪያ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልሰ ይሰጣል:: ስለሆነም ከወዲሁ በመዘጋጀት ከመላዉ ቤተሰብ፣ ከዘመድ እና ከወዳጅ ጋር በመምጣት የበረከቱ ተካፊይ እንዲሆኑ የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

  • ማሕሌተ ጽጌ / ወርሃ ጽጌ (የፍቃድ ጾም ነው) : ከመስከረም 26, 2016 እሰከ ህዳር 6, 2016 (Sat Oct 7, 2023 – Thurs Nov 16, 2023)
  • የበጎፈቃደኝነት አገልግሎት በዩኤስ ባንክ ስታዲየም :- ጥቅምት 12, 2016 (Mon Oct 23, 2023) / U.S. Bank Stadium volunteer work
  • መንፈሳዊ ጉባኤ :- ጥቅምት 17, 2016 (Saturday Oct 28, 2023) ከ3:00 ፒ.ኤም. ጀምሮ. በጉባኤ አዳራሽ 1040 Osborne Road NE, Fridley MN 55432)
  • መንፈሳዊ ጉባኤ :- ጥቅምት 18, 2016 (Sunday Oct 29, 2023) ከ4:00 ኤ.ኤም. ጀምሮ በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን
  • መንፈሳዊ ጉባኤ :-ጥቅምት 22, 2016 (Thursday Nov 2, 2023) ከ5:00 ፒ.ኤም.. ጀምሮ በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን
  • መንፈሳዊ ጉባኤ ;_ ጥቅምት 24, 2016 (Saturday Nov 4, 2023) ከ4:00 ፒ.ኤም. ጀምሮ በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን
  • ጥቅምት መድሐኔዓለም :- በዓለ ንግሱ መርኃ ግብር የሚከናወንበት ትክክለኛ ቀን : ጥቅምት 25, 2016 (Sunday Nov 5, 2023)
  • የበጎፈቃደኝነት አገልግሎት በዩኤስ ባንክ ስታዲየም :- ኅዳር 2, 2016 (Sunday Nov 12, 2023) / U.S. Bank Stadium volunteer work 
  • ኅዳር ሚካኤል :- በዓለ ንግሱ መርኃ ግብር የሚከናወንበት ትክክለኛ ቀን : ህዳር 9, 2016 (Sunday Nov. 19, 2023) / Hidar St. Michael
  • ጾመ ነቢያት (የገና ጾም) :- ከህዳር 15,2016 አስከ ታህሳስ 28, 2016 (Saturday Nov 25, 2023 – Sunday Jan 7, 2024)
  • የበጎፈቃደኝነት አገልግሎት በዩኤስ ባንክ ስታዲየም :- ኅዳር 17, 2016 (Monday Nov 27, 2023) / U.S. Bank Stadium volunteer work
  • የበጎፈቃደኝነት አገልግሎት በዩኤስ ባንክ ስታዲየም :- ታኅሳስ 14, 2016 (Sunday Dec 24, 2023) / U.S. Bank Stadium volunteer work
  • ታኅሳስ ገብርኤል :- በዓለ ንግሱ መርኃ ግብር የሚከናወንበት ትክክለኛ ቀን : ታኅሳስ 21, 2016 (Sunday Dec. 31, 2023) / Tahisas St. Gabriel
  • የበጎፈቃደኝነት አገልግሎት በዩኤስ ባንክ ስታዲየም :- ታኅሳስ 21, 2016 (Sunday Dec 31, 2023) / U.S. Bank Stadium volunteer work
  • የቤዛ ኩሉ ስንበት ት/ቤት የልጆች የገና በዓል ዝግጅት :- ታኅሳስ 26, 2016 (Friday Jan 5, 2024)
  • ልደት (ገና) :- ታኅሳስ 28, 2016 (Monday Jan 7, 2024) / The Birth of Christ
  • የጥምቀት ጾም (የጋድ ጾም) :- ጥር 10, 2016 (Friday Jan 19, 2024)
  • ከተራ :- ጥር 11, 2016 (Saturday Jan 20, 2016)
  • ጥምቀት :- ጥር 12, 2016 (Sunday Jan 21, 2016) / The Baptism of Christ (Epiphany).
  • የካቲት ኪዳነምሕረት :- በዓለ ንግሱ መርኃ ግብር የሚከናወንበት ትክክለኛ ቀን : የካቲት 17, 2016 (Sunday Feb. 25, 2024) / The Covenant of Virgin Mary.
  • ጾመ ነነዌ :- የካቲት 18, 2016 (Monday Feb 26, 2024)
  • የዓብይ ጾም (የሁዳዴ ጾም) :- ከመጋቢት 2 አስከ ሚያዝያ 27 (Monday March 11, 2024 – Sunday May 5, 2024)
  • መጋቢት መድሐኔዓለም :- በዓለ ንግሱ መርኃ ግብር የሚከናወንበት ትክክለኛ ቀን : መጋቢት 29, 2016 (Sunday Apr. 7, 2024) / Megabit Medhanealem / The original Crucifixion.
  • ደብረ ዘይት :- መጋቢት 29, 2016 (Sunday April 7, 2024) / Debrezeit
  • ሀሳዕና :- ሚያዝያ 20, 2016 (Sunday April 28, 2024) / Hosanna
  • ሰሙነ ሕማማት :- ሚያዝያ 21, 2016 እስከ ሚያዝያ 26, 2016 (Monday April 29, 2024 to Friday May 3, 2024) / Holy/Passion week.
  • ጸሎተ ሐሙስ :- ሚያዝያ 25, 2016 (Thursday May 2, 2024) / Maundy Thursday
  • ስቅለት :- ሚያዝያ 26, 2016 (Friday May 3, 2024) / Good Friday (Crucifixion)
  • ትንሣኤ :- ሚያዝያ 27, 2016 (Sunday May 5, 2024) / Easter
  • የእመቤታችን ልደት በአል :- ግንቦትt 1, 2016 (Thursday May 9, 2024) / The Birthday of Virgin Mary
  • የቤዛ ኩሉ ስንበት ት/ቤት ለህጻናት ታዳጊዎችና ወጣቶች የሰመር ኮርስ :- ሰኔ 10,-ሰኔ 21 2016 (June 17, 2024 – June 28,2024) / Kids summer course
  • እርገት :- ሰኔ 6, 2016 (Thursday June 13, 2024) / Ascension. The day of Holy Spirit (Pentecost)
  • ሰኔ ሚካኤል :- በዓለ ንግሱ መርኃ ግብር የሚከናወንበት ትክክለኛ ቀን : ሰኔ 9, 2016 (Sunday June 16)/ Sene St. Michael.
  • ጴራቅሊጦስ :- ሰኔ 16, 2016 (Sunday June 23, 2024) / Peraklitos
  • ጾመ ሐዋርያት (የሰኔ ጾም) :- ከሰኔ 17, 2016 እሰከ ሀምሌ 5, 2016 (Monday June 24, 2024 – Friday July 12, 2024)
  • ጾመ ድህነት :- ሰኔ 19, 2016 (Wednesday June 26, 2024)
  • በአለ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ወገብረመንፈስ ቅዱስ (አቦ በአል) :- ሐምሌ 5, 2016 (Friday July 12, 2024) / The Martyrdom of Peter and Pau
  • የቤዛ ኩሉ ስንበት ት/ቤት የልጆች ሰመር ካምፕ :- ከሀምሌ 8, 2016 እስከ ሀምሌ 12, 2016 (Monday July 15, 2024 – July 19, 2024) / kids summer camp
  • የቤዛ ኩሉ ስንበት ት/ቤት የህፃናት ከ12 አመት በታች የመዝናኛ እና የሽርሽር ጉዞ :- ሐምሌ 18, 2016 (Thursday July 25,2024) / Field Trip for children under 12 years old
  • ሐምሌ ገብርኤል :- በዓለ ንግሱ መርኃ ግብር የሚከናወንበት ትክክለኛ ቀን : ሐምሌ 21, 2016 (Sunday July 28, 2024) /  Hamle St. Gabriel.
  • የቤዛ ኩሉ ስንበት ት/ቤት የታዳጊና የወጣቶች (teenagers ) ከ13 አመት በላይ የመዝናኛ እና የሽርሽር ጉዞ :- ሐምሌ 20, 2016 (Saturday July 27, 2024) / Field Trip for youth over 13 years old
  • ጾመ ፍልሰታ :- ከነሀሴ 1, 2016 እስከ ነሀሴ 16, 2016 (Wed August 7, 2024 – Thursday Aug 22, 2024)
  • ደብረ ታቦር :- ነሐሴ 13, 2016 (Monday August 19, 2024) / Transfiguration (Debre Tabor)
  • ነሐሴ ኪዳነምሕረት :- ነሐሴ 16, 2023 (Thursday August 22, 2024) / The assumption of Virgin Mary.

ለዚህ የቀን መቁጠሪያ ዝግጅት መሳካት የተባበሩኝን ወይዘሮ ሀና ስዩምን: አቶ ደረሰ ለማን እና አቶ ጌታቸው ደበበን አመስግኑልን:: እኛም እጅግ በጣም እናመሰግናለን::

በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የአስተዳደር ቦርድ
October 15, 2023
Minneapolis, Minnesota, U.S.A.

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ኢሜይል: membersservice@dsmachurch.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/

ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ይደረጋል!

  • መንፈሳዊ ጉባኤ :- ጥቅምት 17, 2016 (Saturday Oct 28, 2023) ከ3:00 ፒ.ኤም. ጀምሮ. በጉባኤ አዳራሽ 1040 Osborne Road NE, Fridley MN 55432
  • መንፈሳዊ ጉባኤ :- ጥቅምት 18, 2016 (Sunday Oct 29, 2023) ከ4:00 ኤ.ኤም. ጀምሮ በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን
  • መንፈሳዊ ጉባኤ :-ጥቅምት 22, 2016 (Thursday Nov 2, 2023) ከ5:00 ፒ.ኤም.. ጀምሮ በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን
  • መንፈሳዊ ጉባኤ ;_ ጥቅምት 24, 2016 (Saturday Nov 4, 2023) ከ4:00 ፒ.ኤም. ጀምሮ በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን
  • ጥቅምት መድሐኔዓለም :- ጥቅምት 25, 2016 (Sunday Nov 5, 2023) ከ2:00 ኤ.ኤም. ጀምሮ በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን

ከዘመድ እና ከወዳጅ ጋር በመምጣት የበረከቱ ተካፊይ እንዲሆኑ የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የአስተዳደር ቦርድ
October 15, 2023
Minneapolis, Minnesota, U.S.A.

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ኢሜይል: membersservice@dsmachurch.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/

እንኳን ለ፳፻፲፮ ጽጌ ማሕሌት በሠላም አደረሳችሁ። /October 7, 2023 – November 16, 2023/

የተከበራችሁ የቤተክርስትያናችን አባላት እና ቤተሰቦች በሙሉ፤
እንኳን ለማሕሌተ ጽጌ በሠላም አደረሳችሁ።
ፅጌ ማለት አበባ ማለት ሲሆን ፀገየ ከሚለው የግዕዝ ቃል የመጣ ነው። ጽጌ ማሕሌት በየአመቱ ከመስከረም ፳፮ እስከ ህዳር ፮ (Oct 7, 2023 – Nov 16, 2023)
፵ ቀናት ወይም ፩ ወር ከ ፲ ቀን የሚቆይ ነው። ጽጌ ማሕሌት እመቤታችን ጌታችንን ይዛ መሰደዷን መራቧን መጠማቷን በማሰብ ነው

በማሕሌተ ጽጌ ወቅት ያሉት ሳምንታት ውብ ናቸው ምክንያቱም :-
☞እማምላክን ከነልጇ እንለምንበታለን ስደቷን እናስብበታለን፣
☞ የእመቤታችንን ፍቅሯን እናትነቷን አማላጅነቷን ከሊቃውንቱ ጋር ሆነን በዝማሬ እናወድስበታለን ፣

ጽጌ ማሕሌት የፈቃድ ፆም ስትሆን ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎች ብቻ ይፆሟታል። ምንም እንኳን ፆመ ፅጌ ከ ፯ ቱ የአዋጅ አፅዋማት መካከል ባትሆንም እና እንድንፆማት በአዋጅ ባንታዘዝም በፈቃዳችን በመፆማችን ከፆሟ ረድኤት በረከት የምናገኝባት ነች።

ሰንበትን ከጌታ ከኢየሱስ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋር ሌሊቱን በምስጋና በያሬዳዊ ዜማ ሳምንቱን ደግሞ በፈቃዳችን ማንም ሳያዘን የድንግል ማርያም ፍቅሯ አክብረን እንጾማለን።

እንኳን ለዚህ ጊዜ አደረሰን አደረሳችሁ !!!
የእመቤታችን ፍቅሯ ይብዛልን::

ጽሁፉን ያጠናቀረዉ አቶ ኤልያስ ወርቅህ ነዉ::

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ኢሜይል: membersservice@dsmachurch.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/

የቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ለአዲስ ቤተክርስቲያን ማሰሪያ የሚውል $15,490 አሰባስቡ!

ቀደም ብሎ እንደተገለፀው በቅርቡ ተከብረው ያለፉትን የደብረታቦር እና የአዲስ እመት በአላትን ምክንያት በማድረግ የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤዛ ኩሉ ሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ሆያ ሆዬ እና አበባይሆሽ ፈቃደኛ በሆኑ ምእመናን መኖሪያ ቤቶች እና በቤተክርስቲያናችን ዉስጥ ዘምረዋል:: እቅዳቸው ሁለት መልኮች ነበሩት::

አንደኛው እቅድ ሃይማኖታዊ ይዘቱን እንደያዘ ፣ ወግና ስርአቱን ለትውልድ ለማስተላለፍ ሲሆን ሁለተኛው እቅድ ደግሞ ለለአዲስ ቤተክርስቲያን ሕንጻ ማሰሪያ የሚሆን ገንዘብ ለማሰባሰብ የበኩላቸዉን ጥረት ለማድረግ ነበር:: በጥረታቸው የተስበስበውም የገንዘብ መጠንን በሚመለከት፣ ከሆያ ሆዬ መርኃ ግብር $4,439 ሲሆን ከ አበባይሆሽ ወይም እንቁጣጣሽ መርኃ ግብር ደግሞ $11,0051 ነው:: ከሁለቱ ዝግጅቶች የተስበስበው ጠቅላላ የገንዘብ መጠን በድምሩ $15,490 ደርሷል::

የቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች የሰበሰቡትን $15,490 በሙሉ ለአዲስ የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ማሰሪያ አገልግሎት ይውል ዘንድ በህንፃ አሰሪ ኮሚቴ በኩል ደረስኝ ተቆርጦለት ለቤተክርስቲያናችን ገቢ አድርገዋል::

ከዚህ በታች ያለዉ የሚያሳየዉ የቤዛ ኩሉ ስንበት ት/ቤት ነሐሴ 13 የደብረ ታቦርን በዓል በማስመልከት ፈቃደኛ በሆኑ ምእመናን መኖሪያ ቤቶች ድረስ በመሄድ ሆያ ሆዬ በመዘመር ለአዲስ ቤተክርስቲያን ሕንጻ ማሰሪያ የሚሆን የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ላይ ነዉ።

ከዚህ በታች ያለዉ የሚያሳየዉ የቤዛ ኵሉ ሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች ፈቃደኛ በሆኑ ምእመናን መኖሪያ ቤቶች ድረስ በመሄድ አበባይሆሽ በመዘመር ለአዲስ ቤተክርስቲያን ሕንጻ ማሰሪያ የሚሆን የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ላይ ነዉ።

ከዚህ በታች ያለዉ የሚያሳየዉ የቤዛ ኵሉ ሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች በቤተክርስቲያናችን ዉስጥ አበባይሆሽ በመዘመር ለአዲስ ቤተክርስቲያን ሕንጻ ማሰሪያ የሚሆን የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ላይ ነዉ።

የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችን እናመሰግናለን ! በረከቱን አብዝቶ ይስጥልን !

መረጃው የተገኘው ከደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የአዲስ ህንፃ አሰሪ ኮሚቴ ነዉ::

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ኢሜይል: membersservice@dsmachurch.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/

እናስተዋዉቅዎት! የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት የ፪ሺ፲፭ ዓ.ም. መርኃ ግብር

በቸርነትህ ዓመታትን ታቀዳጃለህ መዝ.64፥11

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

እግዚአብሔር አምላካችን በቸርነቱ ዓመታትን ለሁሉም ያቀዳጃል ከዓመት ወደ ዓመት በቸርነቱ ያሸጋግረናል። ያለፈው ዓመትን አሳልፎ አዲሱን ዓመት ስንቀበል ለሰራናቸው መልካም ስራዎች እውቅና ሰጥተን ጀምረን ያልጨረስናቸውን ደግሞ ለከርሞ ጨርሰን ልንሰራ ያሰብናቸውን ደግሞ እግዚአብሔርን አጋዥ አርገን እንሰራለን።

ከተመሰረተ 27 አመት ያስቆጠረዉ የቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት በደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያናችን ውስጥ ዓመት በዓመት ብዙ እንቅሳቃሴ እያደረገ እንዳለ የሚታወቅ ነዉ:: የቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት በውስጡ ታዳጊ እና ወጣቶችን አቅፎ የሚንቀሳቀስ ለቤተክርስቲያናች ተጠሪ ተቋም ነው። ሰንበት ትምህርት ቤታችን 9 የአገልግሎቶች ክፍሎች አሉት:: ከነዚህም ዉስጥ የልጆች ትምህርት ክፍል አገልግሎት ዘርፈ ብዙ የሆኑ ልዩ ልዩ ትምህርታዊ እና ማህበራዊ አገልግሎቶች ይሰጡበታል:: የደብረሰላም መድኃኔአለም የልጆች ክፍል አገልግሎቶችን በዝርዝር የሚገልፅ ፅሑፍ ከዚህ ቀደም አቅረበናል:: ለማንበብ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ::

የቤዛ ኩሉ ስንበት ት/ቤት መርኃ ግብር እና እንቅስቃሴ ሃይማኖታዊ የበጎ አድራጎት እና ማህበራዊ አገልግሎቶችን ይጨምራል::

  1. በ፪ሺ፲፭ ዓ.ም. በኢትዮጵያ የሚገኘው ሜሪጆይ በሚባል የእርዳታ ድርጅት ስር ካሉ ልጆች መካከል የቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት 20 ልጆችን ይረዳል::
  2. የሰንበት ትምህርት ቤት አባላትን በማስተባበር በካሊፎርኒያ ለሚገኘው ኆኅተ ሰማይ መጥምቀ መለኮት ዮሐንስ ወቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም የ $3000 ዶላር እርዳታ አበርክቷል።
  3. የቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት አባላት በማህሌት አገልግሎት ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ::
  4. የቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት አባላት በዓመቱ መጀመሪያ ላይ በቤተክርስቲያናችን ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6 ለ6 ሳምንታት በሚደረገው ጽጌ ማህሌት ላይ በመገኘት አገልግሎቱ እንዲጠነክር ጉልህ አስተዋጾ ያደርጋሉ::
  5. የቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት አባላት በበዓለ ንግስ ላይ በዝማሬ ያገለግላሉ::
  6. የደብረ ታቦር በዓልን የኢትዮጵያን ቱፊት ሳይለቅ፣ ሃይማኖታዊ ይዘቱን እንደያዘ፣ ለትውልድ ለማስተላለፍ ሆያ ሆዬ በመዘመር እና የችቦ ማብራት መርኃ ግብር በማዘጋጀትና በመምራት የቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት የበኩሉን አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል።
  7. አዲስ ዓመትን የኢትዮጵያን ቱፊት ለቅ፣ ሃይማኖታዊ ይዘቱን እንደያዘ፣ እንኳን አደረሳችሁ በማለት እና አበባይሆሽ በመዘመር ወግና ስርአቱን ለትውልድ ለማስተላለፍ የቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት የበኩሉን አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል።
  8. በተለያዩ ጊዜያት ከሌሎች የደብራችን አባላትና ቤተሰቦች ጋር በመሆን በዩኤስ ባንክ ስታዲየም ለአዲስ ቤተክርስቲያን ማሰሪያ የሚውል የበጎፈቃደኝነት የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ላይ የቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት አባላት አስተዋጽኦ ሲያደርጉ ቆይቷል።

የ፪ሺ፲፭ ዓ.ም. ልዩ ልዩ ተጨማሪ ክንዋኔዎችን በሚመለከት:-

ከዚህ በታች ያለዉ የሚያሳየዉ የቤዛ ኵሉ ሰንበት ተማሪዎች በማህሌት አገልግሎት ላይ ነዉ::

ከዚህ በታች ያለዉ የሚያሳየዉ የቤዛ ኵሉ ሰንበት ተማሪዎች በኪዳነ ምህረት በዓለ ንግስ ላይ በዝማሬ ሲያገለግሉ ነዉ::

ከዚህ በታች ያለዉ የሚያሳየዉ የቤዛ ኵሉ ሰንበት ተማሪዎች በበገና ምሽት መርኃ ግብር ላይ በበገና ዝማሬ ሲያቀርቡ ነዉ::

በ፪ሺ፲፭ ዓ.ም. ከተዘጋጁት እና ስኬታማ ከሚባሉት መርኃ ግብር መካከል አንዱ የቤዛ ኩሉ ስንበት ትምህርት ቤታችን የ27ተኛ ዓመት የምስረታ በዓል ነበር። ክብረ በዓሉ በተጋባዥ መምህራን ቃለ እግዚአብሔር የተሰጠበት ደማቅ እና የማይረሳ ነበር። በዚህ መርኃግብር ላይ የቤዛ ኩሉ ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ሆነው 2ተኛ ክፍልን ላጠናቀቁ ልጆች የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል።

ከዚህ በታች ያለዉ የሚያሳየዉ የቤዛ ኩሉ ስንበት ት/ቤት ነሐሴ 13 የደብረ ታቦርን በዓል በማስመልከት ፈቃደኛ በሆኑ ምእመናን መኖሪያ ቤቶች ድረስ በመሄድ ሆያ ሆዬ በመዘመር ለአዲስ ቤተክርስቲያን ሕንጻ ማሰሪያ የሚሆን የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ላይ ነዉ።

የደብረ ታቦር በዓልን የኢትዮጵያን ቱፊት ሳይለቅ፣ ሃይማኖታዊ ይዘቱን እንደያዘ፣ ለትውልድ ለማስተላለፍ ሆያ ሆዬ በመዘመር እና የችቦ ማብራት መርኃ ግብር በማዘጋጀትና በመምራት የቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት የበኩሉን አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል:: ከዚህ በታች ያለዉ የሚያሳየዉ የቤዛ ኩሉ ስንበት ት/ቤት ተማሪዎች የደብረ ታቦር (ቡሔ) የችቦ ማብራት መርኃ ግብር ላይ ሲዘምሩ ነዉ ::

የቤዛ ኵሉ ሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች አዲስ ዓመትን እንኳን አደረሳችሁ በማለት የኢትዮጵያን ቱፊት ስይለቅ፣ ሃይማኖታዊ ይዘቱን እንደያዘ ለትውልድ ለማስተላለፍ የበኩሉን አስተዋጾ እያደረገ ይገኛል። በመሆኑም ከዚህ በታች ያለዉ የሚያሳየዉ የቤዛ ኵሉ ሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች ፈቃደኛ በሆኑ ምእመናን መኖሪያ ቤቶች ድረስ በመሄድ አበባይሆሽ በመዘመር ለአዲስ ቤተክርስቲያን ሕንጻ ማሰሪያ የሚሆን የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ተከናውኗል።

አዲሱ ዘመን የደስታ የሰላም የፍቅር የይቅርታ የንስሀ ይሁንልን
የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት ዘወትር እሁድ ከቅዳሴ በኋላ 11፡30 AM ጀምሮ እስከ 1 PM ተከታታይ ትምህርት እንዲሁም በአባታችን በሊቀ ጠበብት መራዊ እና በወንድማችን አጋፋሪ ብርሃኑ ያሬዳዊ ዜማ እና ልዩ ልዩ መርኃግብሮች ይሰጣሉ:: መጥተው አብረን በአገልግሎት እንጠንክር።

እንድናገለግለው የፈቀደልን እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን
የእመቤታችን የድንግል ማርያም ምልጃ አይለየን

ይህን ጽሁፍ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ያዘጋጀችው እህታችን ወይዘሮ ሐና ስዩም ነች:: እባካችሁ አመሰግኑልኝ!

ለተጨማሪ ማብራሪያ?
• አቶ ዮሐንስ ከበደ 612-707-5212
• ወ/ት ማርታ 952-437-4312
• ወ/ት ማህሌት ተፈራ 651-442-3738
• አቶ ይገርማል ፈጠነ 651-332-6098
• አቶ እርስት መኮንን 952-221-6668
• አቶ ደባልቄ ገበየሁ 612-203-7745

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ኢሜይል: membersservice@dsmachurch.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
Facebook: https://www.facebook.com/Debreselameotc/

የደመራ በዓል ቅዳሜ መስከረም ፲፱, ፳፻፲፮ /September 30, 2023!

የ፳፻፲፮ ዓ.ም. የደመራ በዓል ቅዳሜ መስከረም ፲፱, ፳፻፲፮ (September 30, 2023) ከ 3 ፒ.ኤም. ጀምሮ በፌለን መናፈሻ በደመቀ ሁኔታ ስለሚከበር ከመላዉ ቤተሰብ፣ ከዘመድ እና ከወዳጅ ጋር በመምጣት የበረከቱ ተካፊይ እንዲሆኑ የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

አድራሻ? / Venue?
1600 Phalen Drive
St. Paul, MN 55106

ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ኢሜይል: membersservice@dsmachurch.com
Website: https://www.debreselam.net
Facebook: https://www.facebook.com/Debreselameotc/

እንኳን ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ!

በሥመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱሥ አሀዱ አምላክ አሜን!!!

በቸርነትህ ዓመታትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል። የምድረ በዳ ተራሮች ይረካሉ፥ ኮረብቶችም በደስታ ይታጠቃሉ። መዝ ፷፬፥፲፩

የተከበራችሁ የቤተክርስትያችንና አባላት እና ቤተሰቦች በሙሉ፤
እንኳን ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ እያልን መጭው ዓመት የሰላም ፣ የጤና እንዲሁም የፍቅር ዓመት እንዲሆንላችሁ በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የአስተዳደር ቦርድ እየተመኘን እንደወትሮዉ ሁሉ በዚህ ባጠናቀቅነዉ የ፪ሺ፲፭ ዓ.ም የሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዓመቱን በሙሉ ክፍት ሆና ዘወትር በየአዘቦት ቀናቶች የኪዳን አገልግሎት፣ ዘወትር እሁድ የኪዳን ፀሎት፣ ቅዳሴ እና ማህሌት፣ እንዲሁም የንግሥ በአላት ፀሎት እና የቅዳሴ አገልግሎቶች፣ የክርስትና፣ ቅዱስ ጋብቻ፣ ፀሎተ ፍታት አገልግሎቶችን ሰጥታለች::

እንደሚታወቀው ሁሉ ደብራችን የሚንቀሳቀስው ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በበጎፈቃደኞች ግልጋሎት እና እገዛ ነው:: እንደወትሮው ሁሉ በዚህ አመትም ብዙ የደብራችን አባላት በተለያዩ የስራ ዘርፎች በፈቃደኝነት በመሳተፍ ውድ ጊዜአቸውን ጉልበታቸውን እውቀታቸውን እና ገንዘባቸውን በተለያዮ ጊዜእት ለቤተክርስቲያናችን አበርክተዋል:: ለመጥቀስም ያህል በቤተክርስታያን ጽዳት ምግብ ሻይና ቡና በማቅረብና በማዘጋጀት በአባላት ማህበራት ውስጥ በአመራርነት በመሳተፍ ህጻናትን እና ወጣቶችን በመንፈሳዊ እውቀት እና በግብረገብነት በማነጽና በመምራት ህንጻ ኮሚቴ የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ላይ በበጎፈቃድ የስራ ቦታዎች በመሳተፍ በመንፈሳዊ አገልግሎቱም በኩል በበጎፈቃደኝነት በመሳተፍና በሌሎችም እዚህ ባልተጠቀሱ ግልጋሎቶች ሁሉ በመሳተፍ:: በዚህ አጋጣሚ የአስተዳደር ቦርዱ ለደብራችን በጎፈቃደኞች ሁሉ የከበረ ምስጋናውን ያቀርባል:: መድሀኔአለም በበረከቱ ይጎብኛችሁ::

በተጨማሪም በ፪ሺ፲፭ ዓ.ም. ዘርፈ ብዙ የሆኑ ልዩ ልዩ ማህበራዊ እና ትምህርታዊ አገልግሎቶች ተሰጥተዋል:: ለመጥቀሰም ያህል:-
1. ወጣቶች ስርዓተ ቤተክርስቲያንን በጠበቀ መልኩ በሊቃውንት አባቶች የድቁና ትምህርት ተሰጧቸው ድቁንና ተቀብለዋል::
2. በበጎፈቃደኞች
እርዳታ ለልጆችና ወጣቶች መንፈሳዊ የበገና ትምህርት ተሰጧቸዋል።
3. በበጎፈቃደኞች እና በወላጆች እርዳታ ልጆችና ወጣቶች መንፈሳዊ እና የአማርኛ ቋንቋ ትምህርትን ይከታተሉባታል::

የ፪ሺ፲፭ ዓ.ም. ልዩ ልዩ ተጨማሪ ክንዋኔወችን በሚመለከት:-
4.
ደብራችን ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ የአስተዳደር ቦርድ አባላት ምርጫ ለ12ኛ ጊዜ ተካሂዶ አዲስ የተመረጡት የአስተዳደር ቦርድ አባላት የሶሰት አመት የስራ ዘመናቸውን ቃለ መሀላ በመፈፀም ጀምረዋል::
5. በዚህ በጨረስነው አመት 68 ቤተስቦች ደብራችንን በአዲስ አባልነት ተቀላቅለዋል:: እንኳን ደህና መጣችሁ እንላቸዋለን::
6. ቤተክርስቲያናችን
12 ክፍል እና ከኮሌጅ ትምህርታቸዉን ላጠናቀቁ 12 የቤተክርስቲያናችን ወጣቶች የእንኳን ደስ ያላችሁ የምስክር ወረቀት አበርክታለች::
7. አዲሱን የቤተክርስቲያናችንን ሕንፃ ለመገንባት የሚያስፈልገንን ገንዘብ ለማሰባሰብ ከኪሳችን ከምናዋጣው ገንዘብ በተጨማሪ ነፃ የበጎፈቃደኝነት የገንዘብ ማሰባስቡን ስራ እንደወትሮዉ ሁሉ በዩኤስ ባንክ ስታዲየም ቀጥለንበት እንገኛለን:: በዚሁ በተጠናቀቀው የ፪ሺ፲፭ ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ በሚኒሶታ ስቴት ፌር የስራ መስክ ተቀይሶ በበጎፈቃደኝነት
አገልግሎት የገንዘብ ማሰባስቡ ስራ በጥሩ ውጤት ተጠናቋል::

8. አባላት እና ቤተሰቦቻቸው በፌለን መናፈሻ ውስጥ ለዘጠነኛ ጊዜ የተዘጋጀውን የ5,000 ሜትር ሩጫና እርምጃ መርኃ ግብር በደመቀ መልኩ ተሳትፈው መርኃ ግብሩ በሰላም ተጠናቋል:: በእለቱም አሸናፊዎች የተዘጋጀላቸውን ሜዳልያና ምስክር ወረቀት ከደብራችን አስተዳዳሪ ከመልአከ ጽዮን ቀሲስ አዲስ ሞላው እና ከመርኃ ግብሩ አዘጋጆች ተቀብለዋል::

9. በዚሁ በተጠናቀቀው በ፪ሺ፲፭ ዓ.ም. የቤዛ ኩሉ ሰንበት ትምህርት ቤት የ27ኛ ዓመት ምስረታ በዓል በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ውስጥ በድምቀት ተከብሯል።

10. በዚሁ በተጠናቀቀው በ፪ሺ፲፭ ዓ.ም. ለህጻናት ታዳጊዎችና ወጣቶች ለአንድ ሳምንት የቆዬ የሰመር ካምፕ ዝግጅቶች በጥሩ ውጤት እና በሰላም ተጠናቋል:: የሰመር ካምፑ የተለያዩ ልጆችን የሚስተምሩ እና የሚያዝናኑ ዝግጅቶች ነበሩት::

11. በዚሁ በተጠናቀቀው በ፪ሺ፲፭ ዓ.ም. ለሁለት ሳምንት የቆዬ የልጆች ሰመር ኮርስ (summer courses) በሰላም ተጠናቋል::

12. በዚሁ በተጠናቀቀው በ፪ሺ፲፭ ዓ.ም. ከዶ/ር ሲራክ በተገኘ የበጎፈቃደኝነት የገንዘብ እርዳታ ህጻናት ታዳጊዎችና ወጣቶችን ያሳተፈ በበንከር የውሀ ዳርቻ (Bunker beach) እና Valley Fair የመዝናኛ እና የሽርሽር ጉዞ (field Trip) በደመቀ መልኩ ተጠናቋል::

አዲሱ ዘመንም የሰላም እና የጤና እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን:: በ፪ሺ፲፮ዓ.ም ቃለ እግዚአብሔር ለመማር፣ ንስሐ ለመግባት፣ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለመቀበል ያብቃን።

ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ብለን የምናመሰግነው፣ ዘመናትን የሚያስረጃቸው፣ ዘመናትን የፈጠረ እና ሰፍሮ ለሰው ልጅ የሰጠ ልዑል እግዚአብሔር መጨው ፪ሺ፲፮ ዓመተ ምህረትን ባርኮ ለቤተክርስቲያን ይስጥልን፤ የመከራውን ዘመንም በቃ ይበለን፤ የእመአምላክ እናትነቷ ምልጃና ርህራሄ አይለየን ፤ አስራት ሀገሯን ኢትዮጵያም በቀደመ ክብሯ ታስብልን አሜን!!!

በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የአስተዳደር ቦርድ
መስከረም ፩ ፪ሺ፲፮ ዓ.ም
ሚኒአፖልስ ሚኒሶታ
September 12, 2023, Minneapolis, Minnesota, U.S.A.

ለተጨማሪ ማብራሪያ ጥያቄ ካለዎት?
እርስት መኮንን 952-221-6668
ደባልቄ ገበየሁ 612-203-7745

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
Website: https://www.debreselam.net
Facebook: https://www.facebook.com/Debreselameotc/

በ፪ሺ፲፭ ዓ.ም. የልጆች ትምህርት አገልግሎት በሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን

በሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የሰንበት ት/ቤት የልጆች ትምህርት ክፍል አገልግሎት ዘርፈ ብዙ የሆኑ ልዩ ልዩ ትምህርታዊ እና ማህበራዊ አገልግሎቶች ይሰጣሉ:: ለመጥቀሰም ያህል:-
ዘወትር ቅዳሜ ከ1.00pm-6.00pm ለልጆች የበገና ትምህርት፣ የወንጌል ትምህርት፣ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት እና የአብነት (የድቁና) ትምህርት ይሰጣል።

የቅዳሜ ክፍለ ግዜ በአራት የትምህርት ዘርፍ አገልግሎት ያተኩራል::
1.00pm-3.00pm የበገና ትምህርት
1.00pm-3.00pm የወንጌል ትምህርት ልጆች በየእድድሜያቸው በሁለት ክፍሎች::
4.00pm-5.00pm የአማርኛ ቋንቋ ማንበብ: የአማርኛ ቋንቋ መፃፍ: የአማርኛ ቋንቋ መስማትና መናገርን ያካተተ ትምህርት ይሰጣል::
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርቱም ለጀማሪ የሀሁ ፊደል ትምህርት, ለመሀከለኛ የቃላት ምስረታ ትምህርት, የመጨረሻ የንባብ እና የዓረፍተ ነገር ትምህርት::
5.00pm-6.00pm የአብነት (የድቁና ) ትምህርት

ዘወትር እሁድ ከቅዱስ ቁርባን በኋላ ለሕፃናትና ወጣቶች በ3 የእድሜ ክፍል (ከ5 እስከ 7 ዓመት፣ ከ8 እስከ 12 ዓመት፣ ከ13 ዓመት በላይ) መንፈሳዊ እና የመዝሙር ትምህርት ይሰጣል።
10.00am-10.30am የመፅሀፍ ቅዱስ ትምህርት
10.30am-11.00am የመዝሙር ትምህርት

ዘወትር እሁድ ከሰንበት አገልግሎት በኋላ ማኅበረ ካህናት እና የሰንበት ት/ቤት መዘምራን የየሰንበቱን እና የየበአላቱን ወረቦት/መዝሙሮች የማኅበር ቀለም ይሰማሉ/ያጠናሉ::

ሰመር ኮርስ:- ከሰኞ እስከ አርብ ለሁለት ተከታታይ ሳምንት የሚቆይ ሰመር ኮርስ ሰለ መሰረታዊ የሀይማኖት (የዶግማ) ትምህርት ይሰጣል:: ተማሪዎቹም በሶስት የዕድሜ ክፍል (ከ5ዓመት እስከ 8 ዓመት፣ ከ9 ዓመት እስከ 12 ዓመት፣ እና ከ13 ዓመት በላይ) ተመድበዉ ትምህርቱ ሙሉ ለሙሉ በእንግሊዘኛ ቋንቋ የሚሰጥ ፕሮግራም ነዉ::
በዚሁ በተጠናቀቀው በ፪ሺ፲፭ ዓ.ም. ለሁለት ሳምንት የቆዬ (June 12 – June 23) የልጆች ሰመር ኮርስ (summer courses) በሰላም ተጠናቋል::

ሰመር ካምፕ:- በዚሁ በተጠናቀቀው በ፪ሺ፲፭ ዓ.ም. ለህጻናት ታዳጊዎችና ወጣቶች ለአንድ ሳምንት የቆዬ የሰመር ካምፕ (ከJuly 17- July 21 ከጠሗት 9:00am – 2:30pm) ዝግጅ በጥሩ ውጤት እና በሰላም ተጠናቋል:: የሰመር ካምፑ የተለያዩ ልጆችን የሚያስተምሩ እና የሚያዝናኑ ዝግጅቶች ነበሩት::

የመዝናኛ እና የሽርሽር ጉዞ (field Trip):- በዚሁ በተጠናቀቀው በ፪ሺ፲፭ ዓ.ም. ለታዳጊ ወጣቶች ከዶ/ር ሲራክ በተገኘ የበጎፈቃደኝነት የገንዘብ እርዳታ ታዳጊዎችና ወጣቶችን ያሳተፈ የመዝናኛ አገልግሎት በ Valley Fair እንዲያገኙ ተደርጓል።

የመዝናኛ እና የሽርሽር ጉዞ (field Trip):- በዚሁ በተጠናቀቀው በ፪ሺ፲፭ ዓ.ም. ከዶ/ር ሲራክ በተገኘ የበጎፈቃደኝነት የገንዘብ እርዳታ ህጻናት ታዳጊዎችና ወጣቶችን ያሳተፈ በበንከር የውሀ ዳርቻ (Bunker beach) የመዝናኛ እና የሽርሽር ጉዞ (field Trip) በደመቀ መልኩ ተጠናቋል::

በዚሁ በተጠናቀቀው በ፪ሺ፲፭ ዓ.ም. የቤዛ ኩሉ ሰንበት ትምህርት ቤት የ27ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ውስጥ በድምቀት ተከብሯል።

አዲሱ ዘመንም የሰላም እና የጤና እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን:: በ፪ሺ፲፮ዓ.ም ቃለ እግዚአብሔር ለመማር፣ ንስሐ ለመግባት፣ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለመቀበል ያብቃን።

ለተጨማሪ ማብራሪያ ጥያቄ ካለዎት?
• ወ/ሮ ቀለም ደጀኔ 651-332-1544
• አቶ ጌታቸው ደበበ 651-366-1650
• ወ/ት ማህሌት ተፈራ 651-442-3738
• አቶ ይገርማል ፈጠነ 651-332-6098
• አቶ ዮሐንስ ከበደ 612-707-5212
• ወ/ት ማርታ 952-437-4312

የነሐሴ ኪዳነ ምህረት በዓለ ንግስን በሚኒሶታ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ያክብሩ

የዘንድሮዉ የነሐሴ ኪዳነ ምህረት በዓለ ንግስ በደመቀ ሁኔታ በሚኒሶታ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ይከበራል:: መጥተው የበረከቱ ተካፋይ እንዲሆኑ ቤተክርስቲያናችን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

መቼ? / When?
ማነክሰኞ ነሐሴ 16, 2015 ከ2:00 ኤ.ኤም. ጀምሮ
Tuesday August 22, 2023 from 2:00 pm

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406

በፌስቡክ እንዲከተሉን ይህን ይጫኑ / Click Here to Follow Us On Facebook

የደብረ ታቦር ክብረ በዓልን በሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ያክብሩ

መቼ? / When?
ቅዳሜ ነሐሴ 13, 2015 ከ4:00 ፒ.ኤም. ጀምሮ
Saturday August 19, 2023 from 4:00 pm

የዚህ ዓመት የደብረ ታቦር ክብረ በዓል የፊታችን ቅዳሜ ነሐሴ 13, 2015 (Saturday August 19, 2023) ከ4:00 ፒ.ኤም. ጀምሮ በሚኒሶታ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በታላቅ ዝግጅትይከበራል። እርስዎም መጥተው የበረከቱ ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ የቤዛ ኩሉ የሰንበት ትምህርት ቤት ጥሪውን ያቀርባል።

ደብረ ታቦር (Transfiguration- Debre Tabor)

ነሐሴንና ጳጉሜን የአዲስ የቤተክርስቲያን አባላት የትውውቅ ጊዜ እና የነባር የደብራችን አባላት የእንቅስቃሴ ወሮች እንዲሆኑ ስለማቀድ

በኢትዮጵያ አቆጣጠር የ2015 ዓ.ም.ን መገባደጃ በመንተራስ በቀሪዎቹ የነሐሴና ጳጉሜ ወሮች የአዲስ የቤተክርስቲያን አባላት የትውውቅ ጊዜ እና የነባር የቤተክርስቲያን አባላት እንቅስቃሴ መርኅግብሮች እንዲታቀዱ የአስተዳደር ቦርዱ ወስኖ የሚከተሉት መርኅግብሮች እንዲከናወኑ ይሆናል:: አዲስ የቤተክርስቲያን አባል ማለት በኢትዮጵያ አቆጣጠር የ2015 ዓ.ም የደብራችን አባል የሆኑ ማለት ነው::

የአዲስ አባላት የትውውቅ መርኅግብር:-

  1. እሁድ እሁድ ከቅዳሴ አገልሎት ፍፃሜ በሗላ እታች አዳራሽ ውስጥ አዲስ የቤተክርስቲያን አባሎቻችንን የእንኳን የደብራችን አባል ሆናችሁ በማለት የካህናት የአስተዳደር ቦርድ እና የአባላት ማኅበራት ተወካዮች ጋር ትዉዉቅ ይደረጋል::
  2. የእዲስ አባላት ስም ዝርርዝም እታች አዳራሽ ውስጥ በሚገኘው ቴሌቪዥን ስኪሪን ላይ ይተላለፋል::
  3. የቤተክርስቲያን አባልነት መታወቂያ ካርድ ላልወስዱ በእለቱ የቤተክርስቲያን አባልነት መታወቂያ ካርድ እንዲያወጡ ይደረጋል::
  4. በእለቱም ለ ዲስ አባላት ቡና ሻይና ዳቦ ካለ ይቀርባል::

የነባር የደብራችን አባላት እንቅስቃሴ መርኅግብር:-

  1. ነባር የቤተክርስቲያን አባሎች እሁድ እሁድ አታች አዳራሽ ውስጥ በሚገኘው የቦርድ አባላት የጠረጴዛ ቢሮ ድረስ በመሄድ የአባላት መዝገብ ላይ ያለው አድራሻችሁ ስልክ ቁጥራችሁና ኢሜል ትክክል እንደሆነ እንድታረጋግጡልን በአክብሮት እንጠይቃለን::
  2. የደብራችን አባልነት አዲስ መታወቂያ ካርድ ያላወጡ በእለቱ የቤተክርስቲያን አባልነት መታወቂያ ካርድ እንዲያወጡ ይደረጋል::
  3. የየደብራችን አባልነት የወርሀዊ መዋጮአችሁ መጠናቀቁን የቦርድ አባላትን መጠየቅና ውዝፍ ካለ በወቅቱ እንዲጠናቀቅ መሞከር
  4. የደብራችን አባል ያልህኑ ዘመዶች ጏደኞች እና ወዳጆችን የቤተክርስቲያኗ አባል እንዲሆኑ ማነቃቃትና ማበረታታት
  5. የቤተክርስቲያናችን የመረዳጃ ማህበር አባል ለመሆን መሞከር
  6. ገቢው ለአዲስ ቤ.ክ. ማስሪያ የሚውል የበጎፍቃድ ስራ አገልግሎት ላይ ለመሳተፍ ከፕሮግራሙ እስተባባሪ ከዶ/ር አሻግሬ መረጃ መጠየቅ

መርኅግብሮቹ ከመጪው እሁድ የቅዳሴ አገልሎት ፍፃሜ በሗላ ለአምስት ተከታታይ እሁዶች የምንከታተላቸው ይሆናል:: ቀኖቹም ነሐሴ7(Sug 13), ነሐሴ14(Aug 20), ነሐሴ21(Aug 27), ነሐሴ28(Sep 3), ጳጉሜ5(Sep 10) ናቸው::

ያቀድናቸውና ያሰብናቸው እንዲሳኩ ውድ የደብራችን ነባርና አዲስ የቤተክርስቲያን አባላት ከምንጊዜውም በበለጠ ሁኔታ የሰበካ ጉባዔውን እንድትተባበሩት በትህትና እንጠይቃለን:: በፅሁፍም ሆነ የመረጡትን የሰበካ ጉባዔ አባል በግል በመቅረብ አዳዲስ የአሰራር ሃሳቦችን እንድታካፍሉን ይሁን::

የደብራችን 2023 ተመራቂ ተማሪዎች እና ቤተሰቦች እንኳን ደስ ያላችሁ ! / Congratulations to 2023 Grads & Families!

“ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናችሁ” መዝ.118:26

በዘንድሮው የ2023 ዓ.ም. የ12ኛ ክፍልን እና የከፍተኛ ትምህርትን ላጠናቀቁ የቤተክርስቲያናችን ወጣቶች የእንኳን ደስ ያላችሁ የምስክር ወረቀት ቤተክርስቲያናችን ባለፈው እሁድ ሐምሌ 30 (Aug 6, 2023) አበርክታለች:: የሚቀጥለው የትምህርትና የመደበኛ ስራ ዘመናቸውም የተቃና እንዲሆንላቸውም ከእግዚያብሔር ቤት ተመርቀዋል::

Congratulations to 2023 grads and families. Graduates were handed out congratulating certificates by our church during the Sunday church services on Aug 6, 2023.

የደብራችን 2023 ተመራቂ ተማሪዎች እና ቤተሰቦች በድጋሚ እንኳን ደስ ያላችሁ !