የመድኃኔዓለም ጽዋ ማህበር (Our Savior Association)

አባቶቻችን፡ ሊቃውንተ፡ ቤተክርስቲያን፡ እንደሚተርኩት፡ ማህበር፡ የሚለው፡ ቃል፡ ሲተረጎም፡ በአንድነት፡ በመተባበር፡ መኖር፡ ማለት፡ ሲሆን፡ ቃሉ፡ የግዕዝ፡ ቃል፡ መሆኑን፡ ይነግሩናል። በማያያዝም፡ በምድራዊው፡ ዓለም፡ በማህበር፡ ወይም፡ በመተባበር፡ መኖር፡ የተጀመረው፡ ከቀዳሚዎቹ፡ ፍጥረታት፡ ከአባታችን፡ ከአዳምና፡ ከእናታችን፡ ከሔዋን፡ ጊዜ፡ ጀምሮ፡ እንደሆነ፡ እና፡ ከዚያም፡ በኋላ፡ ልጆቻቸውና፡ የልጅ፡ ልጆቻቸው፡ አሁን፡ እኛ፡ እስካለንበት፡ ዘመን፡ ድረስ፡ በተለያየ፡ መልኩ፡ ሲጠቀሙበት፡ እንደቆዩ፡ እና፡አሁንም፡ እየተጠቀሙበት፡ መሆኑን፡ ለቃውንተ፡ ቤተክርስቲያን፡ በሰፊው፡ ያስረዳሉ። እንዲሁም፡ ማህበር፡ ከምድራዊ፡ ሰዎች፡ ብቻ፡ ሣይሆን፡ በሠማያዊያን፡ መላዕክት፡ ዘንድም፡ በዓለመ፡ መላዕክት፡ ማህበር፡ መኖሩን፡ ይህም፡ ማህበር፡ በዘጠና፡ ዘጠኝ፡ ነገደ፡ መላዕክትና፡ በዘጠና፡ ዘጠኝ፡ የነገድ፡ አለቆች፡ የተከፋፈለና፡ የተመደበ፡ መሆኑን፡ መምህራንና፡ መጻህፍት፡ ይነግሩናል።

መተዳደሪያ ደንብ (Bylaw)