About Debreselam

ታሪካዊ አመጣጥ(አጀማመር)

በኢትዮጵያ  ዘመን  አቆጣጠር 1986 . ወይም  በፈረንጆች ዘመን አቆጣጠር  1994 .  በጥቂት ሰዎች መልካም ጥረት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዎህዶ ቤተክርስቲያን ስም  መሰባሰብ ተጀመረ። ይህም ጅምር በቀድሞው አባ ፍቅረማርያም አሁን ብጹዕ አቡነ ዳንኤልና  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ  ተዋህዶ  ቤተክርስቲያን  ተከታዮች የላሰለሰ  ጥረትና  እገዛ በሁለቱ መንትዮች ከተማ ሚኒያፖሊስና ሴንት ፖል እንዲሁም በአካባቢው ነዋሪዎች የበለጠ  እየተጠናከረ መጣ። ለዚህ ጅምር ስኬታማነት ምክንያት የሆኑ በርካታ ኢትዮጵያውያን ባደረጉት የገንዘብ፤ የዕውቀትና  የጉልበት  አስተዋጽኦ ዛሬ  ቤተክርስቲያናችን  ወደ  ደረሰችበት የእድገት ደረጃ መድረስ ተችሏል።

ለእምነትና  ለሃይማኖታቸው ቀናኢ በሆኑ ካሃናት አባቶች፤ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፤ ዲያቆናት፤ ዘማሪያን፤ አንባቢያን፤ መንፈሳዊና አሳተዳደራዊ  ችሎታ  ያላቸው አባላት፤ የተለያየ ሙያና  እውቀት ያላቸው ምእመናን፤ የነገ ቤተክርስቲያን ተረካቢ ህጻናትና በተለያየ ጊዜ የቤተክርስቲያኒቱ  የአስተዳደር ቦርድ አባላት በመሆን ቅን አገላግሎት የሰጡ እናቶችና አባቶች፤ ወንድሞችና እኅቶች ባበረከቱት በጎ ተሳትፎ የደብረ ሰላም መድኃኔአለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ  ቤተክርስቲያን  በሚኒያፖሊስ ሚኒሶታ ተመስርቶ ሊስተዋል  የሚገባውን ታላቅ ግብር አከናውኗል በማከናወንም ላይ ይገኛል።

ሁሉ ለእናንተ ሰጥቼአለሁ። (ኢያሱ 15) ተብሎ በተጻፈው ቃል መሰረት እዳ አልባ በሆነ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሥርአተ  አምልኮታችንን እንድናደርግ አብቅቶናል።  የአገራችን የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ በሚውለበለብበትና የኛ በምንለው ቤተክርስቲያን አኩሪ ታሪክ ሠርተው በአካለ ሥጋ ያለፉ፤  በሥራና በትምህርት እንዲሁም በተለያየ  ምክንያት በስደት ምድር በጽናት የቆዩበትን ቤተክርስቲያን ለቀው የሄዱ ሁሉ ለምሥረታው ባለውለታዎች ናቸው። 

መጠሪያ  ሥም

ቤተክርስቲያናችንደብረ ሰላም  መድኃኔአለም  የኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ  ተዋህዶ  ቤተክርስቲያን   በመባል  ይታወቃል።  ይህም  ማለት የሰላም  ቦታና  የኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ  ተዋሕዶ  ቤተክርስቲያን  የእምነት  መገለጫ  ማለት  ነው።

ዓላማ፤

  1. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ  ተዋህዶ  ቤተክርስቲያንን  ሃይማኖት፤  ትምህርት፤  ዶግማ፤  ዶክትሪን፤ ሥርአት፤  ትውፊት፤  ቋንቋና  ሌሎችንም  ኦርቶዶክሳዊና  መንፈሳዊ  የሆኑ ሥርአቶችን  ማስጠበቅ
  2. የኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ  ተዋህዶ  ቤተክርስቲያንን  ሃይማኖት፤  ትማህርት፤  ዶግማ፤  ዶክትሪን፤ ሥርዓት፤ ትውፊት፤  ቋንቋና  ሌሎችንም  ኦርቶዶክሳዊና  መንፈሳዊ  የሆኑ  ሣርዓቶችን  ለተተኪው  ትውልድ  በጽሁፍ፤  በመቅረጸ  ድምጽ (ቴፕሪኮርደር በመቅረጸ  ሥዕልቪዲዮ  ካሜራ) በጥብጣብ (ቴፕ)  በኅዋ  አዋታር (ኢንተርኔት)  እና  በመሳሰሉት  የትምህርት  ማስተላለፊያ  መንገዶች  ተጠቅሞ  ማስተማርና  ማሳወቅ
  3. የኢትዮጵያ ኦርቶክስ  ተዋህዶ  ቤተክርስቲያንን  ሃይማኖት፤  ትምህርት፤  ዶግማ፤  ዶክትሪን፤  ሥርዓት፤  ትውፊት፤  ቋንቋና  ሌሎችንም  ኦርቶዶክሳዊና  መንፈሳዊ  የሆኑ  ሥርዓቶችን  ጠብቀው  ያደረጉትን  ተተኪ  አባላት  ቤተክርስቲያንን  በተራቸው  ማሳደግ  የሚችሉበትን  መንገድ  መቀየስና  ማንነታቸውን  ጭምር  በሚገባ  መግለጽ