All posts by Admin

የሕማማት እና የትንሣኤ አገልግሎት በደብራችን

 

 

 

 

 

ከሰኞ – ረቡዕ  –> ከጠዋቱ 12 – ቀኑ 7 ሰዓት (6AM – 1 PM)
ሐሙስ  –>  ከጠዋቱ 11 – ቀኑ 8 ሰዓት (5AM – 2 PM)
አርብ  –>  ከጠዋቱ 11 – 12 ሰዓት (5AM – 6 PM)
ቅዳሜ  –> ጠዋት ከ12 – 2 ሰዓት
የትንሳኤ አገልግሎት
ቅዳሜ ከሰዓት 11  – ሌሊቱ 8 ሰዓት (ከ5PM – 2AM)

በዓለ ጥምቀት

ጥምቀት በጽርዕ ቋንቋ ኤጲፋኒያ በግእዝ አስተርዮ በአማርኛ መገለጥ ይባላል፡፡ ቃሉ በቀጥታ ሲተረጎም በውኃ ውስጥ ገብቶ መውጣት፣ መነከር፣ መዘፈቅ፣ መጥለቅ ማለት ነው፡፡ ጥምቀት ከሰባቱ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን (ምሥጢረ ጥምቀት፣ ምሥጢረ ሜሮን፣ ምሥጢረ ቁርባን፣ ምሥጢረ ንስሐ፣ ምሥጢረ ክህነት፣ ምሥጢረ ተክሊል፣ ምሥጢረ ቀንዲል) አንዱና ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለኒቆዲሞስ በዮሐ. 3፥5 ላይ ‹‹እውነት እውነት እልሀለሁ፤ ዳግመኛ ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ ያልተወለደ ሰው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም፡፡›› ብሎ እንደተናገረው ከውኃና ከመንፈስ ተወልደን የሥላሴን ልጅነት የምናገኝበት መንግሥተ ሰማያት የምንገባበት ኃጢአታችን የሚደመሰስበት ድኅነትን የምናገኝበት ዐቢይ ምሥጢር ነው፡፡ ጥምቀት በምሥጢረ ሥላሴና በምሥጢረ ሥጋዌ አምኖ ለሚፈጽመው ሰው ሁሉ ለኃጢአት መደምሰሻ ከሥላሴ የጸጋ ልጅነት ለመቀበልና የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመውረስ የተሰጠ ልዩ የሕይወት መንገድ ነው፡፡

to read more

Revised Bylaw (የተሻሻለው ህገ ደንብ)

Section 1 – Name The official name of the church shall be DEBRE SELAM MEDHANEALEM ETHIOPIAN ORTHODOX TEWAHEDO CHURCH in Minnesota, hereinafter referred to as “The Church”, which has been duly incorporated, AS A CONGREGATIONAL CHURCH, under Article 10, Section 191 and 193 of the Religious Incorporation Law of the State of Minnesota. English Version  የአማርኛ ቅጂ

English –  new Bylaw by SubCommittee

Orginal Posted on Aug 21, 2016 @ 07:57

የመድኃኔዓለም ንግስ እና የመሰረት ድንጋይ ማኖር በደብረ ሰላም መድኃኔዓለም

የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ብፁፅ አቡነ ዳንኤል በተገኙበት የጥቅምት መድኃኔዓለምን ጥቅምት 27 2009 (Nov 6, 2006) በደመቀ መልኩ ያከብራል በዕለቱም አዲስ በተገዛው ቦታ ላይ ብፁፅ አባታችን የመሰረት ድንጋይ ያኖራሉ።

ወስብሃት ለእግዚአብሔር!

መጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ በደብረ ሰላም

conferenceorginalበስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን!

መጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ ከፊታችን ሐሙስ ማለትም Oct 13 ጀምሮ በደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢ/ኦ/ተ ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው ስብከተ ወንጌልን ይሳጣሉ፤ እርሶም የዚሁ በረከት ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን ታቀርባለች።

መጋቢ ሐዲስ እሸቱ በቅርቡ ከተናገሯቸው ሁለቱን ጥቅሶች ልናጋራችሁ ወደድን

“እንደኔ እንደኔ የዚህ ሀገር ችግር ከፖለቲከኞቹ በላይ ሃይማኖቶቹ ናቸው ብዬ አስባለሁ፡፡ የእምነት ተቋማት መስራት ያለባቸውን ስራ አልሠሩም፡፡ መንግስት ልማት ሲል እኛም ልማት እያልን ነው የምናስተጋባው፡፡ ሃይማኖቶች ለአገሪቱ የለማ ጭንቅላት ነው ማፍራት ያለባቸው እንጂ መንግስት ዶማ ሲያነሳ ዶማ እያነሱ፣ ህንጻ መገንባት አይደለም ድርሻቸው፡፡ ሁሉም ሃይማኖቶች ድህነትን ከመቀነስ ይልቅ ሃጢአትን መቀነስ ላይ ቢተጉ መልካም ነው፡፡ እነሱ የሃይማኖት ስራቸውን አለመሥራታቸው ነው ይህችን ሀገር ለችግር ያጋለጧት።”

“ሰው ራሱን መለወጥ ሲያቅተው ስረአት ለመለወጥ ይታገላል ራሱን ማደስ ሲያቅተው ሃይማኖትን ለማደስ ይታገላል።..የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ተሰርታ ያለቀች ናት ተሰርቶ ባለቀ ቤት ገብቶ መኖር እንጂ ይቀየር የማለት መብት የለህም በዝቷል ይቀነስ ረዝሟል ይጠር ተጣሟል ላቃና የሚባል ነገር የለም።ቤተ ክርስትያን ሰውን ታድሳለች እንጂ ሰው ሊያድሳት አይችልም”

ቸር ያቆየን

ወስበሃት ለእግዚአብሔር

በሚኒሶታ ለሚኖረው ኢትዮጵያዊው በሙሉ የቀረበ ጥሪ

demera2016_2

የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢ/ኦ/ተ ቤተ ክርስቲያን በ2629 30th Ave South, MPLS MN 55406 ላይ የ2.7 Acre መሬት መግዛቷ ይታወሳል፤ አነሆም የዘንድሮውን የደመራ በዓል በዚሁ በተንጣለለ የግላችን ቦታ ላይ በደመቀ መልኩ ስለምናከብር መጥተው የበረከቱ ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን እያስተላፈች ይህንንም የታሪክና የትውልድ ቅርስ የሆነውን ቦታ እንዲጐበኙ በመጋበዝም ጭምር ነው።

ዕለቱም በግፍ ለተገደሉት፣ ለቆሰሉት እና ለታሰሩት ወገኖቻችን ምህላና ፀሎት ይደረጋል።  እንደሚታወቀው በኢትዮጵያ የዘንድሮን የደመራ እና የመስቀል በዓል ህዝበ ክርስቲያኑ በሃዘን፣ ጥቁር በመልበስ ስለሚያስበው እና ስለሚያከብረው የኛም ቤተ ክርስቲያን ይህንኑ ታበረታታለች። 

ዕለቱ ቅዳሜ መስከረም 14, 2009 (Sep 24, 2016)

ቦታው 2629 30th Ave S. Minneapolis MN 55406
ሰዓት ከ1PM ጀምሮ

ወቅታዊ መግለጫ (Press Release)

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

ሁላችንም እንደምናውቀው እና በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን እንደምንሰማውና እንደምናየው በአሁኑ ጊዜ ቅድስት ሃገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላማዊ ጥያቄ ባቀረቡ ወገኖች እና በንጹሃን ዜጐች ላይ በመንግሥት የጸጥታ ሃይሎች እየተካሄደ ያለው ግድያ፣ እስራት፣ አፈና እና እንግልት ከምንግዜውም የከፋ ደረጃ ላይ ይገኛል። ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ 

የጾመ ፍልሰታ መርሃ ግብር

(Felista2016_2ከዋርካ የተወሰደ፦) <ፍልሰታ > የሚለው ቃል የሚገልጸው ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለቆ መሔድን መሰደድን መፍለስን ያመለክታል። ይህም የእመቤታችንን ሥጋ ከጌቴሴማኒ ወደ ገነት መፍለሱን በኋላም በገነት በዕፀ ሕይወት ስር ከነበረበት መነሳቱን ለማመልከት ይነገራል።

ጾመ ፍልሰታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፷፬ ዓመት በዚች ምድር ኖራ እንደ አንድ ልጇ መሞቷን መነሳቷንና ማረጓን ያዩ ዘንድ ሐዋርያት የጾሙት ጾም ነው። ጾሙ ከነሐሴ ፩ ቀን እስከ ነሐሴ ፲፮ ቀን ሲጾም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንበአዋጅ ከደነገገቻቸው ሰባቱ አጽዋማትም አንዱ ነው።

ሃይማኖታዊ መሠረት

እመቤታችን ከአባቷ ከኢያቄም እና ከናቷ ከሐና ነሐሴ ፯ ቀን ተጸንሳ ግንቦት ፩ ቀን በሊባኖስ ተወልዳለች። <እምሊባኖስ ትወጽዕ መርአት ፦ ከሊባኖስ ሙሽራ ትወጣለች > እንደተባለ ። እምቤታችን በእናት አባቷ ቤት ሦስት ዓመት፤ በቤተ መቅደስ አሥራ ሁለት ዓመት፤ ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ሠላሳ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ፡ ከዮሐንስ ወልደዘብዴዎስ ዘንድ አሥራ አራት ዓመት ከዘጠኝ ወር ቆይታ በ ፷፬ ዓመት ዕድሜዋ በ፵፱ ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች። የእመቤታችንን ስም የሚገልጹ የውዳሴ ጽሑፎችም በእድሜዋ ልክ ተደርሰዋል። ለምሳሌ የውዳሴ ማርያም ቁጥር ፷፬ ነው፤ የመልክአ ማርያም ቁጥርም ፷፬ ነው።

ባረፈች ጊዜ ቅዱሳን ሐዋርያት ተሰባስበው አስከሬኗን ይዘው ወደ ጌቴሴማኒ መቃብር ለማሳረፍ ሲሄዱ አይሁድ ለተንኮል አያርፉምና ተተናኮሏቸው። ቀድሞ ልጇ ሞቶ ተነሳ፣ አረገ እያሉ ሲያስቸግሩን ይኖራሉ: ደግሞ አሁን እሷም ተነሳች፣ አረገች ሊሉ አይደል በማለት አይሁድ ተሰባስበው አስከሬኗን ለማቃጠል ሲተናኮሉ እግዚአብሔር በተአምር ከነዚያ አይሁዶች አድኗቸዋል ። የእመቤታችንንም አስከሬን ነጥቆ ከሐዋርያው ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር በገነት በዕፀ ህይወት ስር አኑሯቸዋል ። ከዚያ በኋላ ሐዋርያት ሥጋዋን አግኝተው ይቀብሩት ዘንድ በአረፈች በስምንተኛው ወር ከነሐሴ ፩ ጀምሮ እስከ ነሐሴ ፲፬ ቀን ድረስ ሁለት ሱባዔ ይዘው በአሥራ አራተኛው ቀን ሥጋዋን ከጌታ ተቀብለው በጸሎትና በምህላ በፍጹም ደስታ በጌቴሰማኔ አሳረፉት ። በ ሦስተኛውም ቀን ተነስታ ስታርግ ከሰኡቃዊያን ወገን የሆነው ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ አያት። እርሱም በቀብር ስርዓቱ ጊዜም አልነበረም። ሀገረ ስብከቱ ህንድ ስለነበር ሊያስተምር ወደዛው ሂዶ ነበርና። በዚያም ሲያስተምር ሰንብቶ በደመና ተጭኖ ሲመጣ ያገኛታል። ትንሳኤዋን ከርሱ ሰውራ ያደረገች መስሎት አዝኖ «ቀድሞ የልጅሽን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁ አሁን ደግሞ ያንቺን ትንሳኤ ሳላይ ቀርቼ ነውን ?» ብሎ ቢያዝንባት እመቤታችንም ከርሱ በቀር ማንንም ትንሳኤዋን እንዳላየ ነግራ አጽናናችው። ለሌሎቹ ሐዋርያትም እንዲነግራቸው ለምልክትም /ለምስክርም እንዲሆነው ሰበኗን /መግነዟን ሰጥታው አረገች። ቶማስም ኢየሩሳሌም ደርሶ ሐዋርያትን «የእመቤታችን ነገርስ እንደምን ሆነ?» ሲል ቢጠይቅ «አግኝተን ቀበርናት እኮ» አሉት። እርሱ ምስጢሩን አዉቆ ደብቆ «ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር» እንዴት ይሆናል ? አይደረግም ይላቸዋል። ሊያሳያቸውም መቃብሩ ዘንድ ሂደው ቢከፍቱት አጧት። እርሱም «አታምኑኝም ብዬ እንጂ እርሷስ ተነስታ አርጋልች» በማለት ሁኔታውን ተረከላቸውና ለምስክር ይሁንህ ብላ የሰጠችውን ሰበኗን አሳያቸው። ከዚህ በኋላ ለበረከት ይሆናቸው ዘንድ ሰበኑን ተካፍለው ወደየአህገረ ስብከታቸው ሄዱ። ዛሬ በቅዳሴ ጊዜ ዲያቆኑ በሚይዘው የመጾር መስቀል ላይ በሁለት ቀዳዳዎች አልፎ ተጠምጥሞ የምናየው መቀነት መሰል ጨርቅ የዚያ ሰበን ምሳሌ ነው።

በዓመቱ ሐዋርያት ከያሉበት ተሰባስበው ቶማስ ትንሳኤሽን አይቶ እኛስ እንዴት ይቀርብናል ብለው ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምርው ሱባዔ ቢይዙ ከሁለት ሱባዔ በኋላ እንደገና ትንሳኤዋንና እርገቷን ለማየት በቅተዋል። ሐዋርያዊት የሆነች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናም ምእመኖቿ ከእመቤታችን በረከትን እንዲያገኙ ይጾሙ ዘንድ ይህን ሐዋርያት የጾሙትን ጾም እንዲጾሙ አዉጃለች። ምእመናንም በተለየ መልኩ በጾም በጸሎት በሱባዔ ጽሙድ ሆነው ይህን ወቅት ያሳልፋሉ።

የእመቤታችን ትንሳኤ ድንገት እንደእንግዳ ደራሽ እንደ ዉሀ ፈሳሽ የተደረገ ሳይሆን በቅዱሳት መጻሕፍት በትንቢተ ነቢያት የተገለጸ ነው። ነቢዩ ዳዊት በመዝሙር ፻፴፩ ቁጥር ፲ ላይ «አቤቱ ወደ እረፍትህ ተነስ አንተና የመቅደስህ ታቦትም» ይላል። በዚህም ምዕመናንን ወደ ምታሳርፍበት ወደ መንግሥተ ሰማያት የመቅደስህ ታቦት ድንግል ማርያምን ይዘህ ተነስ አለ። ታቦት የጽላት ማደርያ እንደሆነ ሁሉ እምቤታችንም ለክርስቶስ ማደርያ በመሆኗ አማናዊት ታቦት ትባላለች።

ንጉስ ሰሎሞንም በመኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ምዕራፍ ፪ ቁጥር ፲ ላይ «ውዴ እንዲህ ብሎ ተናገረኝ፤ ወዳጄ ሆይ ተነሽ፡ ውበቴ ሆይ ነይ» ብሏል። እዚህ ላይ «ወዳጄ …ዉበቴ»” የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት ። ክቡር ዳዊት መዝሙር ፵፬ ቁጥር ፱ ላይ «በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች» እንደሚል ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛነቱን ከፈጸመ በኋላ ወደ ቀደመ ክብሩ እንዳረገ እመቤታችን ቅድስት ድንገል ማርያምም በቀኙ ትቀመጥ ዘንድ «ተነሽ ነይ» አላት ። እንግዲህ ይህንና የመሰለዉን ሁሉ ይዘን የእናታችንን እረፍቷን ትንሳኤዋን እንዘክራለን እንመሰክራለንም።

ደብረ ሰላም 2.7 Acres (1.1 ሔክታር ወይንም 10927 ካሬ ሜትር) ቦታ ገዛች

2016-06-20 08_32_31-New notification በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን።

“የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል እኛም ባሪያዎቹ ተነስተን እንሰራለን” ነህምያ 2፥20

ከሁሉ አስቀድሞ ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ለሰራ ለልዑል እግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ይሁን።

ቤተክርስቲያናችን ሚኒሶታ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በርካታ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶች የሚሰጡባት ንጽሕት እና ቅድስት የሆነች የእግዚአብሔር ማደሪያ ናት። ይህች ቤተክርስቲያን በፈቃደ እግዚአብሔር ከተመሰረተች ጊዜ ጀምሮ እዚህ ለምንገኝ አባላትም ሆነ በተለያዩ ምክንያቶች አሁን በዚህ ከእኛ ጋር ለሌሉም ብዙ ወገኖቻችን ሁሉ በርካታ አገልግሎቶችን ያበረከተች ቤተክርስቲያን ናት። ብዙዎች ልጆቻቸውን ያስጠመቁባት ቅዱስ ጋብቻን የመሰረቱባት ለቅዱስ ሥጋውና ለክቡር ደሙ የበቁባት በርካቶችም ከጭንቀት ከሃዘንና ከችግራቸው የተጽናኑባት የሰማይ ደጅ ናት።

በእውነተኛው አምላካችን ደም የተመሰረተችው ይህች ቤተክርስቲያናችን የንጽህት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን ቤተክርስቲያንን እምነት ሥርዓትና ትውፊት ጠብቃ ያለች በዓመት ውስጥ 365 ቀናት ክፍት ሆና በርካታ መንፈሳዊ አገልግሎቶችን ትሰጣለች። በኪዳን፣ በቅዳሴና በሰዓታት ጸሎታት፤ እንዲሁም በተለያዩ ክብረ በአላት፦ ለማስታወስም በአመት ውስጥ 14 ጊዜ ያህል በማኅሌት፣ ጥምቀትን ጨምሮ ዘጠኝ ጊዜ ያህል በንግሥ፣ 16 ቀን በሰሙነ ፍልሰታ፣ 6ሳምንታት በጽጌ ማኅሌት፣ 5 ቀን በሰሙነ ሕማማት እንዲሁም በመስቀል ደመራ ልዩ ዝግጅት ያላሰለሰ አገልግሎት የሚሰጠባት ታላቅ ደብር ናት።

በደብራችን የሚሰጡት መንፈሳዊ አገልግሎቶች እየተስፋፉ ከመምጣታቸው በተጨማሪ የተገልጋዩም ምእምን ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ እያደገ በመምጣቱ፤ ይበልጡንም ደግሞ በዚህ ሃገር የተወለዱ ልጆች ሃይማኖታቸውን ተምረው ቤተክርስቲያንን ለመረከብና ለማገልገል ይችሉ ዘንድ የተመቻቸ ሁኔታን ማዘጋጀት የግድ አስፈላጊ በመሆኑ በተጨማሪም ሌሎች ችግሮችን ማቃለል ይቻል ዘንድ በስፋትና በይዘት አሁን ካለንበት ቤተክርስቲያን ሰፋ ያለና ምቹ የሆነ ሁሉን የሚያሟላ አዲስ ሕንጻ ቤተክርስቲያን መስራት አማራጭ የሌለው መሆኑ ታምኖበት እንቅስቃሴ ተጀምሮ የነበረ መሆኑ የሚታወስ ነው። ይሁን እንጂ መልካም ሥራን ለመስራት ሲነሳሱ ሁል ጊዜም ፈተና በመኖሩ ያሰብነው እቅድ ቤተክርስቲያናችን በገጠማት ፈተና ለጊዜው ተጓቶ የነበረ ቢመስልም የቤተክርስቲያናችን የአስተዳደር ቦርድ ለዚህ ታላቅ ውጥን ቅድሚያ በመስጠት በተለያዩ ጊዜያትም ከአባላት ጋር በመወያየት እና የአባላትን ይሁኝታ በማግኘት ለጉዳዩ የበለጠ ትኩረት ሰጥቶ እንቅስቃሴውን አጠናክሮ ሲሰራ ቆይቷል።

በእኛ በኩል ላለፈው አንድ አመት ተኩል ያህል ነገሮች አንድ ጊዜ ተስፋ የሚያስቆርጡ ሌላ ጊዜ ደግሞ ተስፋ የሚሰጡ መስለው ሲቀጠሉ ቆይተዋል። ነገር ግን እግዚአብሔር አምላክ ፈቅዶ ይኸው ለዛሬዋ የምስራች እለት አድርሶናል።

የምሰራቹም አንድ ዓመት ከአምስት ወራት ብዙ ውጣ ውረድ ያየንበት ለቤተክርስቲያን እና ለልዩ ልዩ ተቋማት መስሪያ የሚሆነውን 2.7 ኤከር ስፋት ወይንም ወደ 11 ሺህ ካሬ ሜትር ስፋት ያለውን 2629 30th Ave S Minneapolis, 55406 ላይ የሚገኘውን ቦታ ገዝተን የቦታውን ባለቤትነት ሰነድ ከትናንት በስቲያ አርብ ጁን 17/2016 ዓ.ም ተረክበናል።

ለዚህም አባታችን መድኃኔዓለም ክብርና ምስጋና ለስሙ ይሁን እንላለን።

የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢ/ኦ/ተ ቤተ ክርስቲያን

 

በዓለ ስቅለት እና በዓለ እግዝእትነ ሲገጣጠሙ ይሰገዳል ወይስ አይሰገድም?

IMG_1421ምንም እንኳ ይህ ጥያቄ በብዙ ሰዎች ዘንድ የተመለሰ ቢሆንም ተደጋጋሚ ጥያቄዎች መምጣታቸው ሁለት ነገሮችን ስላመለከተኝ እኔም እንደገና በአጭሩ ለመመለስ ጥረት አደርጋለሁ፡፡ የመጀመሪያው የተሰጠው መልስ ለሁሉም እኩል አለመድረሱ ሲሆን በሁለተኛነት ደግሞ አንዳንዶቻችንም ተደጋሞ አንድ ዓይነት መልስ በማየት የማረጋገጥ ፍላጎት ያለን ይመስላል፡፡
ይህን የመሰሉ ተደጋጋሚ ጥቄዎች ሲገጥሙን ነገሩን ማየት ያለብን ከመሠረታዊው የቤተ ክርስቲያን ትውፊትና አስተምህሮ መሆን አለበት፡፡ ለምሳሌ ይህ ጥያቄ የበዓሉን አከባበር የሚመለከት ስለሆነ በቤተ ክርስቲያናችን የበዓላት ቀኖናም ሆነ ትውፊት መሠረት በዓላት የሚበላለጡ ከሆነ የሚበልጠው የትኛው ነው ከሚለው ቀላል ጥያቄ ልንነሣ እንችላለን፡፡ በዚሁ መሠረት የመጀመሪያውን ደረጃ የሚይዙት የጌታችን ዐበይት በዓላት ቀጥሎም የጌታችን ንዑሳት በዓላት መሆናቸውን ለመረዳት አያስቸግርም፡፡ Continue reading በዓለ ስቅለት እና በዓለ እግዝእትነ ሲገጣጠሙ ይሰገዳል ወይስ አይሰገድም?

Volunteers Needed

TaxLearn to Prepare Taxes and Make a Difference at the same time.  How can you make a difference? Simple.  Help your community in preparing taxes free of charge or for a voluntary contribution to building funds by becoming a volunteer with the Free Income Tax Preparation Service Initiative.

Be a Volunteer.  This Free Income Tax Preparation Initiative is a partnership between Amare Berhie and your church, Debreselam Medhanealem Church.

Volunteers typically start training in January. They are expected to provide two to three hours (Sunday) of service per week between the beginning of February to the middle of April. The time commitment will vary depending on individual responsibilities as well as the number of volunteers working at a site and the number of people being served by the site.

 • Currently we are seeking volunteers for the following positions: 
  Administrative assistants to process tax returns, make copies, keep track of data, check taxpayers in, and make sure taxpayers are being served in the order they arrived
 • Interpreters assist taxpayers who have limited English proficiency. We are currently seeking Tigrigna and Oromia interpreters.

Volunteer Requirements:

 • Sign a confidentiality agreement;
 • Seniors in high school or university students planning to major in accounting, finance, marketing, business, etc.
 • Excellent typing speed.

Why Volunteer?

 • Learn something new and exciting.
 • Make an impact on the lives of others.
 • Improve language skills.
 • Meet and interact with new and diverse people
 • Give back to your community.
 • Gain valuable work and business experience to better compete in today’s job market.
 • Utilize your professional/technical skills.

Great volunteers are the key to our success. Join this year’s effort and help make a difference in our community.

Want More Information?
Call 651-235-5341     

Free Income Tax Preparation Service Initiative!

Get Your Tax Refund Fast!!!

Combining e-file with direct deposit is the fastest and safest way to get your refund. Amare Berhie, an IRS licensed Enrolled Agent and an Authorized e-file Provider, is providing free tax preparation services in hopes of raising funds for Debreselam Medhanealem EOTC building. You are welcome to make donations of any amount. Please come and take advantage of this offer to have your taxes completed by an experienced professional and your voluntary contribution will go to a good cause.

                           ነጻ የገቢ ታክስ ዝግጅት አገልግሎት
ከገቢ ታክስ ተመላሽ ክፍያ በተፋጠነ መንገድ ለማግኘት ሰነዱን በአሌክትሮኒክስ ገቢ በማድረግና ተመላሹ ገንዘብ ለባንክ በቀጥታ ገቢ እንዲሆን የሚያስችል የታክስ ዝግጅት አገልግሎት ባሁኑ ወቅት በቤተክርስትያናችን ይሰጣል።
ለቤተክርስትያን ህንጻ ግንባታ ገንዘብ ለማሰባሰብ እንዲረዳ በማቀድ ለዚሁ ሙያ ህጋዊ ፈቃድና የምስክር ወረቀት ያላቸው ባለሙያ አቶ አማረ በርሄ ለግል ድካማቸው ክፍያ ሳይጠይቁ አገልግሎቱን ለመስጠት ተዘጋጅተዋል። ለዚህም በጎ ተግባር አቅማችሁ የቻለውን ያህል በመለገስ ሰፊ የሥራ ልምድ ባለው ባለሙያ በአገልግሎቱ እንድትጠቀሙ ቤተክርስትያናችን ትጋብዛለች።

 Get Your Federal, State & Property Tax Refund Fast!!!

 Free Income Tax Preparation Service Initiative – we offer Federal and State tax preparation with secure electronic filing and direct deposit. 

Get Your Taxes Done For Free Or Voluntary Contribution To The DSMA EOTC Building Fund.

 • Federal, State & Property Tax Refund
 • Electronic, Secure Tax Filing
 • Fast Refunds,
 • Authorized IRS E-file Provider

Get your refund the fastest way possible using e-file and direct deposit. We’ll help you get all the credits you qualify for and file your return electronically, so you’ll get your refund fast.

What Should I Bring?

 • Proof of identification (photo ID)
 • Social Security cards for you, your spouse and dependents
 • An Individual Taxpayer Identification Number (ITIN) assignment letter may be substituted for you, your spouse and your dependents if you do not have a Social Security number
 • Proof of foreign status, if applying for an ITIN
 • Birth dates for you, your spouse and dependents on the tax return
 • Wage and earning statements (Form W-2, W-2G, 1099-R,1099-Misc) from all employers
 • Interest and dividend statements from banks (Forms 1099)
 • All Forms 1095, Health Insurance Statements
 • Health Insurance Exemption Certificate, if received
 • A copy of last year’s federal and state returns, if available
 • Proof of bank account routing and account numbers for direct deposit such as a blank check
 • To file taxes electronically on a married-filing-joint tax return, both spouses must be present to sign the required forms
 • Total paid for daycare provider and the daycare provider’s tax identifying number such as their Social Security number or business Employer Identification Number
 • Forms 1095-A, B or C, Affordable Health Care Statements

Additional Tax Information/Forms

 • If you paid student loans: 1098-E
 • If you attended a higher-education institution: 1098-T, documentation of tuition
 • If you owned a home: 1098, documentation of mortgage interest and property taxes paid
 • If you owned your own business: documentation of business income, business expenses and mileage
 • CPR – 2015 Certificate of rent paid
 • 2016 Property Tax Statement

Do I Need To Make An Appointment?

Appointments are appreciated but walk-ins are welcome! Our Program runs from January to April 15, 2016, Sunday 9:00 to 11:30pm.

About Our Program:

This Tax Preparation Volunteers program is a partnership between Amare Berhie & Debreselam Medhaniealem EOT Church and is operated by volunteers.

About Amare Berhie:

Amare Berhie, Enrolled Agent, founder & CEO of ABA Tax Accounting, a public accounting firm and AB Tax Online, FREE e-Filing Tax Service is a Tax & Accounting professional and real estate investment consultant. IRS licensed and authorized by the United States Department of Treasury to appear on taxpayers behalf at all levels of the IRS, in ALL States and an Authorized IRS e-file Service Provider.

What are the limitations to services?

We can help most people with their tax returns, but some returns are too complex for this engagement. Here are services we do NOT provide:

 • Prior Year and Amended Returns
 • Schedule C with losses
 • Complicated & advanced Schedule D (capital gains and losses)
 • Form SS-5 (request for Social Security Number)
 • Form 8606 (non-deductible IRA)
 • Form 8615 (minor’s investment income)
 • If you have a 1099-B (proceeds from a brokerage, if you bought/sold stock)
 • If you sold your home or if it went into foreclosure
 • If you moved for your job and would like to claim the moving expenses adjustment
 • If you received rental income
 • If you are an international student/teacher on a J,Q, F or M Visa
 • If you are a non-resident alien who needs to complete a 1040NR form
 • If you are self-employed and had expenses above $10,000, had a net loss, or want to deduct the use of your home as a business expense.
 • If you are a registered domestic partnership (This is not the same as a same-sex marriage. We can file those returns.)
 • Form SS-8 (determination of worker status for purposes of federal employment taxes and income tax withholding)

Note:  For complex or out of scope returns, you may contact Amare Berhie at ABA Tax Accounting or other professional preparers for assistance.

What If I want To File For Free On My Own?

If you’d prefer to file online on your own, you may visit AB Tax Online. Federal tax is free for those who made less than $100,000 in 2015, single or married filing joint.

ዜና እረፍት

Taye-Reta

የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመስራቾቹ አንዱ እና ታላቅ አባት የነበሩት አቶ ታዬ ረታ ባደረባቸው ህመም ሲረዱ ቆይተው በትላንትናው እለት በፌርቪው ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል አርፈዋል።

ቤተ ክርስቲያናችን የተሰማትን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸች ለልጆቻቸው፣ ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጆቻቸው ሁሉ መጽናናት ትመኛለች።  እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ከደጋጎቹ አባቶች ጎን ያሳርፍልን።

የእዝኑ ቦታ: Lao Community Center 320 University Ave W Saint Paul MN, Thursday and Friday from 2 PM
ሥርዓተ ፍትሃት: ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም 4401 Minnehaha Ave S MPLS MN 55406 -Saturday @10AM
ስርዓተ ቀብሩ:
 Sunset Funeral Chapel – 2250 St Anthony Blvd, Minneapolis, MN 55418

ዜና ቤተክርስቲያን

dsma3rdgubeበታላቁና በአንጋፋው በሚኒሶታ ደብረ ሰላም መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያ 3ኛው ዙር የመጀመሪያው ቀን መንፈሳዊ ጉባዔ ልዩ መንፈሳዊነት በያዘ መልኩ ትላንት በደብሩ ካህናቶች በጸሎት ተከፍቷል። ይህ ለ3 ተከታታይ ቀን የሚቆየው ጉባዔ ላይ ቤተክርስቲያን ካፈራቻቸው የወንጌል ሰባክያን መሀከል ለመናፍቃን በቂ መልስ በመስጠት የሚታወቀው መምህር ምሕረተአብ አሰፋ የወንጌል አገልግሎት ሰጥተዋል። መምህር ምሕረተአብ መቀመጫቸውን በሚኒሶታ ደብረ ሰላም መድኃኒዓለም በማድረግ በተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች በሲያትል፣ በዳላስ ፣ በአትላንታ፣ በዴንቨር  ያደረጉት አገልግሎት በእግዚአብሔር ፈቃድ የተሳካ ሆኗል። በትላንትናው እለት በደብራችን የተጀመረው የሶስተኛውን ዙር ጉባዔ በመምህር ምሕረተአብ የስብከተ ወንጌል እና የዝማሬ አገልግሎት የተሰጠ ሲሆን  በዚህ ጉባዔ ላይ ተጋባዥ እንግዳ የሆኑት  ወንድማችን ጥላሁን (ከዲሲ) ዝማሬውን በክራር በማጀብ ጉባዔውን ልዩ እንዲሆን አድርገውታል። በመጨረሻም ስለ ሀገራችን ኢትዮጵያ ጸሎተ ምህላ ተደርጎ የትላንትናው መርሃ ግብር በጸሎት ተዘግቷል። ይህ ጉባዔ ቅዳሜና እሁድ የሚቀጥል ሲሆን በዚህ አጋጣሚ አገልግሎቱ ላይ ተገኝተሁ የበረከቱ ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን ታቀርባለች።

ክብር እና ምስጋና ለድንግል ማርያም ልጅ ለእርሱ ለሀያሉ አምላካችን ይሁን።

ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ

የማይቀርበት ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ በአናጋፋውና በታላቁ ደብር በሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መቀመጫውን ሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አድርጎ የሥብከተ ወንጌልን እሳት በዚህ ታላቅ ደብር ለኩሶ በምድረ አሜሪካ እያቀጣጠለ ያለው ታላቁ የተዋህዶ የወንጌል ገበሬ በመምህር ምህረተዓብ አሰፋ December 18, 19 and 20 ከ5 pm  እስከ 8pm።

የቅዱስ ሚካኤል ንግስ በትላንትናው ዕለት በታላቅ ድምቀት ተከበረ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን!

በትላንትናው ዕለት  በደብራችን በደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የአምላክ ባለሟል የቅዱስ ሚካኤል በዓል ብፁዕ አቡነ አትናቲዎስ የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል የድሬደዋና አካባቢዋ  ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣ እንዲሁም ቤተክርስቲያን ካፈራቻቸው የወንጌል አርብኞች መካከል አንዱ መምህር ምሕረተአብ አሰፋ በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ውሏል። ከትላንት በስቲያ ከዋዜማ ፕሮግራም ጀምሮ ለሊት በማህሌት ከ2AM ጀምሮ በማህሌት፣ በቅዳሴ፣ በወንጌል ትምህርት፣ በኋላም ታቦቱ በብፁዐን አባቶች፣ በደብሩ ካህናት፣ ዲያቆናት፣ መዘምራን እና ከሩቅም ከቅርብም ከመጡ ምእመናን ጋር በመሆን በዝማሬና በእልልታ  እየታጀበ ዑደት ካደረገ በኋላ በታላቁ አባት በአቡነ አትናቴዎስ ቃለ ምእዳንና ቡርኬ ተሰጥቶ ታቦቱ ወደመንበሩ ባማረ እና በደመቀ ሁኔታ ተመልሷል። ይህን በዓል ለየት የሚያደርገው የህዳር ሚካኤል ታቦተ ንግስ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በአውደ ምህረቱ ላይ ሆኖ ነበር የሚባርከው ነገር ግን ትላንት በእግዚአብሔር ቸርነት አየሩ ጥሩ ስለነበር ታቦቱ  ወጥቶ ዑደት ተደርጓል። እግዚአብሔር አምላክ የከበረበት ጠላት ዲያቢሎስ ያፈረበት ሆኖ ተጠናቋል ክብር ለድንግል ማርያም ልጅ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር !